Sunday, August 5, 2012

ጋዜጣና መጽሔቶቻችን ከሰኞ እስከ ሰኞ - ዘጠኝ


(ከሐምሌ 23 እስከ 29፣ 2004)

አቶ ጁነዲን ሳዶ ኢትዮ-ቻናል እና ለሰንደቅ ጋዜጣ ያወሩብኝ ‹‹ከሰሞ የሐይማኖት ችግሮ ጋር በፍፁም የማይያያዝና ተጣሞ የቀረበ ነው›› የሚል ደብዳቤ ለጋዜጦቹ ልከዋል፡፡ በደብዳቤያቸው ባለቤታቸው ይዘውት ተገኙ የተባለው ገንዘብ የሚኒስትሩ እናት ሲሞቱ በተናዘዙት መሰረት እንደግለሰብ ከሳዑዲ መንግስት ለማሰሪያ ድጋፍ ጠይቀው ላስጨረሱት መስጊድ የሰደቃ ፕሮግራም የታሰበ ነበር፡፡

** ** **

Capital ጋዜጣ “Hard currency shortage” በሚል ርዕስ ምንጮቹን ጠቅሶ ባስነበበው ዜና በተለይም የንግድ ሰዎች የውጭ ንግዳቸውን የሚያካሂዱበት የውጭ ምንዛሬ እጥረት እንደገጠማቸው አትቷል፡፡

** ** **

Fortune ጋዜጣም “Saudi Star begins to spit the advance for Abebo” የሚል ዜና በፊት ገጹ ይዞ ወጥቷል፡፡ በዝርዝሩም ሳውዲ ስታር Abeboን ለመግዛት ለፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ መክፈል ከሚጠበቅበት 40.5 ሚሊዮን ብር የቅድሚያ ክፍያ ውስጥ 32 ሚሊዮን ብሩን ጁላይ 18 ከፍሏል፡፡ Abebo በጋምቤላ 3000 ሄክታር መሬት ያለው ሲሆን 65000 ሜትር ስኩዌሩ የጥጥ ተክል ልማት ጀምሯል፡፡

** ** **


ሪፖርተር ጋዜጣ በእሁድ እትሙ ‹‹ጋምቤላ የመሸገውን የደቡብ ሱዳን አማፂ ኃይል ለመቆጣጠር ኢትዮጵያ ጦ አሰማራች›› ይላል፡፡ በዝርዝሩም ‹‹… አማፂ ቡድኑ ሰርጎ ገብቷል የተባለው በጋምቤላ ክልል ኑዌር ዞን ሲሆን፣ ቡድኑ የደቡብ ሱዳንን መንግሥት ለመውጋት የጋምቤላን ወጣቶች  እየመለመለ እንደሚገኝ ተጠቁሟል፡፡

ይህንን አማፂ ቡድን በቁጥጥር ሥር አውሎ ለደቡብ ሱዳን መንግሥት ለማስረከብ  የጋምቤላ ክልል ከፌደራል መንግሥት ጋር በጋራ  እየሠራ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል፡፡ …››

በተጨማሪም ሪፖርተር ‹‹የኢትዮጵያ ድል በንግሥቷ ወርቅ ተጀመረ›› ይለናል፡፡

ተመስገን ደሳለኝ ስለ ፍትሕ ጋዜጣ መታገድ
የፍትሕ ጋዜጣ መታገድን አስመልክቶ፣ የጋዜጣው ዋና አዘጋጅ አቶ ተመስገን ደሳለኝ ከተለያዩ የሚዲያ አካላት ጋር ቃለምልልሶችን አድርጓል፣
  • እኛ ሥራችንን ጨርሰናል፤ ከዚህ በኋላ ኃላፊነቱን መወጣት ያለበት ሕዝቡ ነው! - ፍኖተ ነፃነት
    ‹‹... እስከዛሬ 140 ክሶ በላይ ተከስሻለሁ፣ ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ ፀረ ሽብር ግብረኃይል ጠርተው ደብድበውኛል፣ በቪዲዮ ቀርፀውኛል፣ ከዚህ በኋላ በሚል ከፍተኛ ማስጠንቀቂያ ሰጥተውኛል፣ ይህን እስከዛሬ አልተናገርኩም፣….››
  • ጥያቄያችን መልስ እስኪያገኝ ድረስ ማንኛውንም ሕጋዊና ሰላማዊ መስመሮችን በመጠቀም እንታገላለን -  ዕንቁ መጽሔት
  • ፍትህ ጋዜጣ በመጪው አርብ ገበያ ላይ ትውላለች - አዲስጉዳይ መጽሔት
  • ጋዜጣ ላይ ብንጽፍም ባንጽፍም ስጋቱ አለ - አዲስ አድማስ
  • ፍትህ ጋዜጣ ወደህትመት እንዲመለስ መድረክ ጠየቀ - ሪፖርተር

ሌላም፣ ሌላም

ርዕሰ አንቀጾች

No comments:

Post a Comment