Sunday, August 12, 2012

ጋዜጦች እና መጽሔቶቻችን ከሰኞ እስከ ሰኞ - አሥር


(ከሐምሌ 30 እስከ ነሐሴ 6፣ 2004)

Capital ጋዜጣ “Golden Girls” በሚል ርዕስ በፊት ገጹ ላይ ባስነበበው ዜና ኤድናሞል ላይ በተሰቀለው ስክሪን የዓርብ ዕለቱን ሩጫ ሲመለከቱ የነበሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን መሰረት ደፋር በሚበሩት እግሮቿ የመጨረሻውን መስመር ስትረግጥ በሐሴት እንደተጥለቀለቁ ጽፏል፡፡ Fortune ጋዜጣም በተመሳሳይ ዜና ኢትዮጵያውያን በሙሉ ወርቁ የኢትዮጵያ እንደሆነ በርግጠኝነት ተማምነው፣ ሲጠብቁ የነበሩት ከመሰረት እና ከጥሩነሽ ማን ያመጣዋል በሚል እንደሆነ ዘግቧል፡፡

** ** **

‹‹ዳግም የተወለደችው መሠረት ደፋር›› የሚል ዜና ያስነበበን ደግሞ ሪፖርተር ጋዜጣ ነው፡፡ ‹‹“የአምስት ዓመት ልጄን በስልክ አግኝቻት ነበር፡፡ እርሷም ‹ማሚ እባክሽ የወርቅ ሜዳሊያውያን አሸንፊ› ስትል ጠየቀችኝ፡፡ ቃል ገብቼላት ነበር፤ ቃሏን በመጠበቄ ኮርቻለሁ በቃ፣ ዛሬ እንደገና የተወለድሁ ያህል ከፍተኛ ደስታ ተሰምቶኛል፤” …››

** ** **

‹‹…አቃቤ ሕግ በተመስገን ደሳለኝ ላይ ሦስት ክሶችን የመሰረተ ሲሆን ፥ ክሶቹም 1ኛ ወጣቶች በአገሪቱ መንግስትና ሕገ መንግሥታዊ ሥርአቱ ላይ እንዲያምጹ የመገፋፋትና ግዙፍ ያልሆነ የማሰናዳት ተግባር፣ 2ኛ የሀገሪቱን መንግስት ስም ማጥፋት እና የሀሰት ውንጀላ እንዲሁም 3ኛ የሀሰት ወሬዎችን በማውራት ሕዝብን በማነሳሳት ወይም አስተሳሰባቸውን ማናወጥ የሚሉ ናቸው። …››

 ** ** **

‹‹…በተለይ የአገሪቱ ትልቁ የንግድ ባንክ የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለደንበኞቹ ሌተር ኦፍ ክሬዲት መክፈት ሲያቆም፣ ባንኩ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው የአገሪቱ የሦስት ወራት የውጪ ንግድ ከመቀነሱ ጋር በተያያዘ ነው የሚል መልስ እየሰጠ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል፡፡ …››

** ** **

አዲስጉዳይ መጽሔት ‹‹ጋዜጠኛ ሳምሶን ማሞ የሰብአዊ መብት ጥሰት ተፈጽሞብኛል አለ›› የሚል ዜና አስነብቧል፡፡ ‹‹በዜድ ፕሬስ ፕሮሞሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ሥር እየታተመ በየሳምንቱ ለንባብ ይቀርብ የነበረው ኢትዮ ቻናል ጋዜጣ ንግድ ፈቃድ ባለማደስ ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ ከህትመት ውጪ እንደምትሆን የኢትዮቻናል ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ሳምሶን ማሞ ለአዲስጉዳይ ተናግሯል፡፡…››

** ** **

ሌላም፣ ሌላም

ርዕሰ አንቀጾች

የሳምንቱ ጥቅስ
‹‹15 አመት እንደምታሰር እያሰብኩ ጋዜጣ ልሠራ አልችልም›› - ሳምሶን ማሞ (ለአዲስ አድማስ ጋዜጣ በሰጠው ቃለ ምልልስ)

No comments:

Post a Comment