Sunday, August 19, 2012

ጋዜጦች እና መጽሔቶቻችን ከሰኞ እስከ ሰኞ (አሥራአንድ)


(ከነሐሴ 7 እስከ ነሐሴ 14፤ 2004)

የኛ ፕሬስ ጋዜጣ ሲፒጄ የሙስሊሞች ጉዳይ መጽሄት አዘጋጅ የሱፍ ጌታቸው ይፈታ ማለቱን እና የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እና መምህራን የዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎች ድንጋይ ይጥረቡ መባሉ እንዳሳዘናቸው ዘግቧል፡፡

ፍኖተ ነፃነት በቃለ መጠይቅ አምዱ (/) ክቡር ገናን ይዞ ወጥቷል፡፡ ስለ ኢትዮጵያ ሲቪክ ማህበራት ተግዳሮቶች እና እንቅስቃሴዎች አወያይቶዋቸዋል፡፡ አቶ ክቡር ገናም ‹አንድ ህዝብ ዝም ብሎ ተኝቶ ሲረገጥ አይውልም፤ ድንገት ይነሳል› ማለታቸውን በፊት ገጹ አስፍሯል፡፡

በዚህ ሳምንት አቶ ክቡር ገና ከሰንደቅ ጋዜጣም ጋር ቆይታ ነበራቸው፡፡ በተመሳሳይ የሲቪል ማህበራት ጉዳዮች ዙሪያ ለሰንደቅ ቃለ መጠይቅ ሰጥተዋል፡፡

የጠ/ መለስ ነገር
ከፓትሪያርኩ ዜና እረፍት በፊት የወጡት ጋዜጦች  ሁሉም በፊት ገጻቸው የጠ/ሚኒስትሩን መጥፋት ሽፋን ሰጥተውታል፡፡

የኛ ፕሬስ በፊት ገጹ የጠ/ሚኒስተር መለስ ጉዳይ እያወዛገበ ነው ሲል የተለያዩ ተቋማት ጉዳዩን አስመልክቶ ያወጡትን ዘገባ አስነብቧል፡፡

መለስ ወደ ስልጣናቸው አይመለሱም - ዘጋርዲያን
ከአዲስ አመት በፊት ስራቸውን ይጀምራሉ - አቶ በረከት
የጠ/ሚሩ የግል ተተኪ አለመኖር አሳስቦናል - የኬንያው /ሚኒስተር
ከታቦ ኢንቤኪ ጋር በጉዳዩ እተማከሩ ነው - ፋይናንሺያል ታይምስ
ከአሁኑ ስልጣን ለመያዝ እርስበርስ እየተሻኮቱ ነው - ሀይሉ ሻውል

ሰንደቅ በፊት ገጹ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አነጋጋሪነት ቀጥሏል ያለው ሰንደቅ ድንገት መሰወራቸው ግብጾችን አሳስቧል ሲል የአሜሪካንን ዝምታ አሳሳቢነት እና የእንግሊዝ ጋዜጦችን ተደጋጋሚ የዜና ሽፋን በጠ/ሚው የትካዜ ፎቶግራፍ አጅቦ አውጥቶአል፡፡

ፍኖተ ነፃነት በበኩሉ አቶ መለስ ከያራ የማዳበሪያ አምራች ፋውንዴሽን ያገኙት ሽልማት በሙስና የተገኘ ነው መባሉን በፊት ገጹ አስፍሯል፡፡ በተያያዘ ዜና የአቶ መለስ ጉዳይ አለየለትም በማለት የአቶ መለስን አለመኖር አስመልክቶ የተለያ አካላትን ሃሳብ ይዞ ወጥቷል፡፡

የፓትሪያርኩ ህልፈት
አዲስ ጉዳይ እና እንቁ መጽሄቶች በፊት ገጻቸው የፓትሪያርኩን ፎቶግራፍ ይዘው የወጡ ሲሆን አዲስ ጉዳይ በፓትሪያርኩ ሕይወት ላይ ያተኮረ ረዥም ጽሁፍ አስነብቧል፡፡ እንቁ በበኩሉ የሞታቸው ምክንያት ከእግራቸው ህመም ጋር የተያያዘ ነው ሲል አዲስ አድማስ ጋዜጣ ደግሞ የህልፈታቸው ምክንያት ስኳር በሽታ መሆኑን ገልጧል፡፡

ሌላም፣ ሌላም
 • ለምግብ እጥረት የተጋለጡ ተጎጂዎች ቁጥር አሻቀበ - ሰንደቅ እና አዲስ አድማስ
 • የኢትዮጵያ መንግስት የትጥቅ ትግል ከሚያደርግ ድርጅት ጋር ዛሬ ይፈራረማል/ተፈራረመ - ሰንደቅ እና አዲስ አድማስ
 • ተመስገን ደሳለኝ ፍርድ ቤት ሊቀርብ ነው - ፍኖተ ነፃነት
 • የታሰሩ ኮሚቴዎቻቸው እንዲለቀቁ ሙስሊሞች ጠየቁ - ፍኖተ ነፃነት
 • ከሚስቱ የተጣላው አትሌት ውሎው ሺሻ ቤት ሆኖዋል፡፡ ፊቱ ላይ ተስፋ መቁረጥ እና ራስን መጥላት ታይቶበታል - የኛ ፕሬስ ተባራሪ ወሬ
 • የወረዳው ስራ አስፈጻሚ ስልጣናቸውን ለሚስታቸው አደራ ሰጡ - የኛ ፕሬስ ተባራሪ ወሬ
 • ሚኒስትር ጂነዲን ማንን ምይቅርታ አልጠይቅም አሉ - ቆንጆ መጽሄት

ርእሰ አንቀጾች
 • ከአፍንጫ አርቆ ማሰብ የተሳነው አትሌቲክስ ፊዴሬሽን - የኛ ፕሬስ
 • በጥቂት አትሌቶች ዋጋ የተሸፈነ አስተዳደር ሊፈርስ ይገባዋል - ሰንደቅ
 • ኢህአዴግ ነጻውን ፕሬስ ለማጥፋት የጀመረውን ዘመቻ ባስቸኳይ ያቁም - ፍኖተ ነፃነት
 • ሜዳው ላይ እንተያይ!” አትሌት ጥሩዬ - አዲስ አድማስ

የሳምንቱ ምርጥ ንግግር
‹‹አስራ አምስት አመት የሚያሳስረኝ ከሆነማ ይህች ሃገር የኔ አይደለችም ማለት ነው፡፡››
(ሳምሶን ማሞ
ለየኛ ፕሬስ ጋዜጣ በክሱ ዙሪያ ከተናገረው)

No comments:

Post a Comment