Monday, April 28, 2014

የታሰሩ የዞን9 አባላትና ጋዜጠኞች ትላንትና እሁድ ሚያዝያ 19 አራዳ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው እነደነበር ታወቀ

የታሰሩ የዞን9 አባላትና ጋዜጠኞች ትላንትና እሁድ ሚያዝያ 19 አራዳ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው እነደነበር ታወቀ

አርብ አመሻሹን እና ቅዳሜ ጠዋት የታሰሩት የዞን9 አባላትና ጋዜጠኞች ትላንትና (እሁድ ጠዋት) ፍርድ ቤት መቅረባቸው ታወቀ፡፡ ቤተሰብም ሆነ የህግ ባለሞያ ባላወቀበት ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን የጊዜ ቀጠሮ የተጠየቀባቸው ክስ ላይ 

"ውጨ ሃገር ከሚገኙ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ነን ከሚሉ ጋር በገንዘብና በሃሳብ በመተባበር በማህበረሰብ ሚዲያ ሃገርን ማሸበር" ወንጀል መጠርጠራቸው የተገለጸ ሲሆን 

1. ማህሌት ፋንታሁን አቤል ዋበላ እና በፍቃዱ ሃይሉ ለሚያዚያ 30
2. ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ጋዜጠኛ አስማማው ሃይለግዮርጊስ ዘላለም ክብረት ለሚያዝያ 29
3. አጥናፍ ብርሃኔ ኤዶም ካሳየ ናትናኤል ፈለቀ ሚያዝያ 30 ተቀጥረዋል፡፡


The journalists and bloggers are charged of "Working with foreign human right activist organizations agreeing with idea, finance and inciting violence through social media to create instability in the country" with three different files.

Hence;
1. Mahlet Fantahun
2. Abel Wabela
3. Befeqadu Hailu are appointed for May 8 2014 

1. Tesfalem Weldyes 
2. Asmamaw W/Giorigis
3. Zelalem Kebret are appointed for May 7 2014

1. Atenaf Berahene
2. Edom Kassaye
3. Natnael Feleke are appointed for May 8 2014

#FreeZone9bloggers #FreeEdom #FreeTesfalem#FreeAsemamaw #Ethiopia

Saturday, April 26, 2014

የዞን ዘጠኝ የቅርብ ወዳጅና ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳየ ታሰረች

 ዞን ዘጠኝ  አሁን  በደረሰው መረጃ መሰረት ጋዜጠኛ እና የዞን9 ዘመቻዎች ንቁ ተሳታፌ የነበረችው የቅርብ ጓደኛ ኤዶም ካሳዪ በፀጥታ ሃይሎች ቤቷ ተፈትሾ ወደ ማእከላዊ ምርመራ ትወስዳለች ! ዞንዘጠኝ የኤዶም ካሳየ በምንም አይነት ህገወጥ ተግባር ውስጥ ተሳትፋ እንደማታውቅ ነገር ግን ከደህንነት ሃይሎች ከፍተኛ ወከባ ሲደርስባት እንደቆየች እያረጋገጠ መንግስት እሷንም ሆነ ሌሎች አባላትን በአስቸኳይ እንዲፈታ በድጋሚ ጥሪውን ያስተላልፋል!

According to the latest information we got, Journalist, campaigner and close friend of Zone9 have been arrested and her house was searched this late morning. For the last few months Edom had been in serious interrogation and surveillance from "Intelligence officers" questioning her details on the activities of the Zone9. Zone Nine again wants to confirm that Edom and other Bloggers has never been a part of any illegal activity and we request the government to release all immediately.


 

የታሰሩ የዞን9 ጦማርያንና ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ማእከላዊ ምርመራ እነደሚገኙ ተረጋገጠ

ትላንትና ማምሻውን በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች በቁጥጥር ስር ዋሉት 6 የዞን 9 አባላትና ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ማእከላዊ ምርመራ እንደሚገኙ ተረጋግጧል፡፡ ታሳሪዎቹን ቤተሰብ ማየት የማይችል ሲሆን ስንቅ በማቀበል ብቻ ተመልሰዋል፡፡ በተያዙበት ሰአት ቤታቸውና ቢሮአቸው የተፈተሸ ሲሆን መጽሃፍት ጋዜጦች እና ላፕፖቻቸውም ጭምር እነደተወሰዱ ማወቅ ችለናል፡፡ 

በድጋሚ የዞኑ አባላትና ወዳጆች ምንም አይነት ህገ ወጥ ስራ ላይ ያልተሰማሩ በመሆናቸው መንግስት እርምት ወስዶ በአስቸኳይ አንዲፈታቸው እንጠይቃለን! 

Zone9 has confirmed that Six Zone9 bloggers and journalist Tesfalem Woldeyes are in Addis Ababa central investigation center (meakelawi) since their arrest last night. during the arrest their house was searched and police took laptops, Newspapers and books from their home. Families were not allowed to meet them.We believe members and friends of Zone Nine have nothing to do with any illegal activities and we again request the government to release them immediately. 

#FreeZone9bloggers #FreeTesfalem #Ethiopia

Friday, April 25, 2014

ስድስት የዞን 9 ጦማርያን በመንግሥት ተያዙ፣ በአስቸኳይ እንዲፈቱ እንጠይቃለን

ዛሬ አርብ ሚያዝያ 17 ቀን 2006 አመሻሹ ላይ 11፡20 ገደማ ስድስት የዞን ዘጠኝ ጦማርያን አባላት የሆኑት ጓደኞቻችን በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች ከያሉበት ተይዘዋል፡፡ እነርሱም ናትናኤል ፈለቀ፣ በፍቃዱ ሀይሉ፣ አጥናፍ ብረሀነ፣ ማህሌት ፋንታሁን፣ ዘላለም ክብረት እና አቤል ዋበላ ናቸው፡፡ ጦማርያኑን ጓደኞቻችን ለማሰር የመጡት አካላት የማሰሪያና የመፈተሻ የፍርድ ቤት ፈቃድ የያዙ መሆናቸውን ሰምተናልአ መደበኛ የሆነው “ዞን 9” የጦማርያን ስብስብ አባላት ሚያዚያ 15፣2006 በዋጣነው መግለጫ ላለፉት ሰባት ወራት የዞኑ አባላት ከፍተኛ የሆነ ክትትል ሲደረግባቸው እንደነበር በጠቅላላው የተጠቆመ ሲሆን ክትትሉ የተወሰኑ የቡድኑን አባላትና የቅርብ ወዳጆችን ጭምር ያካተተ ነበር፡፡ አሁን በመንግስት የተወሰደው እርምጃ የዞኑን ተመልሶ ወደ ስራ መግባት ተከትሎ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል ሆኖም የዞን 9 አባላትና ወዳጆች በምንም አይነት ህገ ወጥ ተግባር ላይ ተሰማርተው እነዳልነበር ለማረጋገጥ እንወዳለ፡፡ በመሆኑም የታሰሩ የዞኑ አባላትና ወዳጆች በአስቸኳይ እንዲለቀቁ እንጠይቃለን፡

Six members of Zone Nine, group of bloggers and activists are arrested today late in the afternoon at 5:20 pm by security. Team members Befeqadu Hailu, Atnaf Berahane, Mahlet Fantahun, Zelalem Kiberet, Natnael Feleke and Abel Wabela are all under custody on arrest warrant.
The arrest comes immediately after the bloggers and activists notified their return to their usual activism on April 23, 2014 after their inactivity for the past seven months. On their return note the group has indicated that they have sustained a considerable amount of surveillance and harassment. They have indicated that one of their reasons for their disappearance from activism is the harassment they have been receiving from government security agents.
We believe members and friends of Zone Nine have nothing to do with illegal activities and we request the government to release them immediately.

Zone9.

አለም አቀፍ ሰብአዊ መብት መሳሪያዎችና ኢትዮጵያ

በሶልያና ሽመልስ

በኢህአዴግ መንግስት የመሪነት ሰልጣኑን ከያዘ ከዛሬ 22 አመት ግድም ጀምሮ ቃል ገብቶ ተግባራዊ ባለማድረግ ከሚወቀስባቸው ጉዳየች አንዱ የአገሪትዋ የሰብአዊ መብት አያያዝ ነው፡፡ ሁሉንም አለም አቀፉን የመብቶችን አለማቀፋዊነት የሚያረጋግጡ ጠንካራ እና ግልጽ የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎችን የያዘ ህገ መንግስት በመጀመሪያዎቹ የስልጣን አመታት መጽደቁም ይታወቃል፡፡

በመጀመሪያዎቹ አስር አመታት የነበረው የሰብአዊ መብት አያያዝ በጣም በአስጊ ሁኔታ ከፍተኛ ቅሬታ የቀረበበት ቢሆንም የቀጣዩ አስር አመታት አፈጻጸምም ከትችት አላመለጠም፡፡ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሰብአዊ መብት ሪፓርቶችን የሚያወጡ አገር በቀል የማህበረሰብ ድርጅቶች በበጎ አድራጎትና ማህበራት አዋጅ የተነሳ ሽባ በመሆናቸው የሰብአዊ መብት ሁኔታውን ለመገምገም አስቸጋሪ ስለሆነ የአገሪትዋ ሰብአዊ መብት ሁኔታ ” የውጪ ሃይሎች” ድምጽ ብቻ የሚሰማበት ምድረ በዳ ሆኗል፡፡ በአገሪትዋ የተለያዬ ክፍሎች የሚከናወኑ የመብት ጥሰቶችን ለእርምት የሚያቀርብ የአገር ውስጥ ተቋም በሌለበት ሁኔታ በቀጣዩ የፈረንጆች ወር መጀመሪያ የኢትዮጰያ የሰብአዊ መብት ግምገማ (universal periodic review ) ለሁለተኛ ጊዜ በተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ይካሄዳል፡፡

አለማቀፍ የሰብአዊ መብት ግምገማ (United Nations Human Rights Council Universal Periodic Review)

አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ግምገማ ሁሉም የተባበሩት መንግስታት አገራት በየ4 አመት ተኩል የሚያደርጉት የሰብአዊ መብት ግምገማ ሂደት ነው፡፡ይህ የግምገማ ሂደት አገሮች ያላቸውን የሰብአዊ መብት ችግሮች ለመፍታት እና ችግሮቻቸውን በማስታወስ እነዲያሻሽሉ እንደያግዝ የታሰበ ስርአት ሲሆን እኤአ ከ20006 ጀምሮ ተግባራዊ መሆን ጀምሯል፡፡ በዚህ ግምገማ የተገምጋሚው አገር መንግስት የሰብአዊ መብት ስራውን አስመልክቶ ሪፓርት ያቀርባል፡፡ መንግሰታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና የሰብአዊ መብት ተቋማትም በተመሳሳይ ተገምጋሚው አገር የሰብአዊ መብት ሁኔታ ላይ ሪፓርታቸውን ለተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ያስገባሉ፡፡ እነዚህ የመንግሰትም መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ሪፓርቶችም ተሰብስበው ለአባል አገራት አንዲደርሱ የማድረግ ሃላፌነቱን የተባበሩት መንግስታት ይወስዳል ፡፡ ይህ የግምገማ ሂደት በአጠቃላይ ለ3 ሰአት ከሰላሳ የሚቆይ ሲሆን ተገምጋሚው አገር የራሱን የሰብአዊ መብት ሁኔታ የሚገልጽ ሪፓርት ካቀረበ በሁዋላ የተለያዩ አገራት ጥያቄ ለማቅረብና የማሻሻያ ነጥባቸውን ( recommandations) ለመናገር ቦታ ይይዛሉ ፡፡ በዚህ የግምገማ ሂደት ተገምጋሚ አገር አስፈላጊ ሆኖ ካገኘው የሚቀበለውን የማሻሻያ ነጥብ ተቀብያለው ሲል የማይቀበላቸውን ነጥቦች አልቀበልም በማለት እዚያው መልስ መስጠት ይችላል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን አጠቃሎ የተቀበላቸውንና ያልተቀበላቸውን ማሻሻያ ሃሳቦች በሶስት ወራት ገደማ ውስጥ በይፋ ያሳውቃል፡፡ ይህ ሂደት ከተጠናቀቀ በሁዋላ እነዚህን የማሻሻያ ሃሳቦች መተግበር የተገምጋሚው አገር ሃላፊነት ነው፡፡ይህ ሂደት የመጀመሪያው ከሆነ የሰብአዊ መብት ሪፓርትና ጥያቄዎችን የመመለስ ሂደት ሲሆን ለሁለተኛ ዙር ከሆነ ግን ተገምጋሚው አገር በመጀመሪያው ግምገማና በሁለተኛው ግምገማ መካከል ያለውን አፈጻጸምና መሻሻል የማሻሻያ ነጥቦቹ ላይ ያደረገውን ተግባራዊ ለውጥ አብሮ ያቀርባል፡፡ በዚህ መሰረት የኢትየጵያ መጀመሪያው ግምገማ እኤአ በ2009 የተካሄደ ሲሆን ከተለያዩ አገራት 160 የማሻሻያ ነጥቦች አቅርበው ነበር፡፡

አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ግምገማና ኢትዮጲያ

ይህ በየ4 አመቱ የሚካሄድ ግምገማ ላይ አገራችን ከፍተኛ ቁጥር ያለው የማሻሻያ ነጥቦች ከተሰጣቸው አገራት አንዷ ስትሆን በ2009 አ.ም ከተሰጠት የማሻሻያ ነጥቦች መካከል አብዛኛውን ከሲቪክና ፓለቲካዊ መብቶች ጋር የተያያዙ ማሻሻያዎችን ባለመቀበል መንግስት ውድቅ አድርጎአቸዋል፡፡ በወቅቱ ገና በመጽደቅ ላይ የነበሩትን የበጎአድራጉት ድርጅቶች እና የጸረ ሽብር ህግ አዋጆች በተገቢው የአለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ደረጃ መሰረት እንድታሻሽል የሚሉ ማሻሻዎች ቢገኘበትም ህጎቹ ምንም መሻሻል ሳይደረግባቸው ሁለተኛው ዙር ግምገማው ከሳምንት በሁዋላ ይደረጋል፡። በመጀመሪያው ግምገማ ወቅት ማሻሻያ ቀርቦባቸው መንግስት ያልተቀበላቸው ጉዳዩች በጥቂቱ የጸረ ሽብር ህጉን ማሻሻል ፣የበጎ አድራጎትና ማህበራት ህጉን መሰረዝ ፣የመንግሰት አስተዳደር አመራር ውስጥ የሚገኘውን የብሄር ተዋእጾ መገምገምና የፌደራሊዝም ስርአቱ መሰረት ሁሉንም ብሄሮች ያማከለ እነዲሆን ማሻሻል፣ኦጋዴን እና ሶማሊያ ክልልን ለሰብአዊ እርዳታ ስራዎች ክፍት ማድረግ፣ የታሰሩ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችን መፍታት ፣በሶማሌ ክልል የሚገኝ የሰብአዊ መብት ሁኔታን በገለልተኛ ወገን ማጣራትና የአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አባልነት የመሳሰሉት ሲገኙበት ተቀባይነት ካገኙት ማሻሻያ ዎች መካከል የ እኤአ 2010ምርጫን ነጻና ፍትሃዊ ማድረግ፣የገለልተኛ ሚዲያ እድገትን መደገፍ፣ የሴቶችና ህጻናት መብቶች አጠባበቅን ማገዝ የሴት ልጅ ግርዛትና አለእድሜ ጋብቻን ማስወገድ እነዲሁም አገር አቀፍ የሰብአዊ መብት እቅድ ማዘጋጀት ይጠቀሳሉ፡፡

በዚህ የመጀመሪያ ዙር ግምገማ የኢትዮጲያ መንግስት አንዳንድ ጠቅላላ ማሻሻያዎችን ሲቀበል ከነዚህም ውስጥ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ግለሰቦችን ደህንነት መጠበቅ ጠቅላላ የሲቪል ማህበረሰቡ የስራ ከባቢን ምቹ ማድረግ፣ የሚዲያ እድገትን መደገፍ ደረጃውን የጠበቀ ምርጫ ማድረግ የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡

በሁለቱ ግምገማዎች መሃል

ከአራት አመት በፌት የተሰጡ የማሻሻያ ሃሳቦች ያሉበትን ሁኔታ በማሳወቅ የሚጀምረው የአሁኑ የመንግስት ሪፓርት አገሪትዋ በሰብአዊ መብት ረገድ ከፍተኛ መሻሻል እያሳየች እነደሆነ ያትታል፡፡ በተጨማሪም የሰብአዊ መብት እቅድ መዘጋቱን እንደትልቅ ስኬት ያቀርበዋል ፡፡ በሌላ በኩል አገሪትዋ ውስጥ የቀሩት በጣት የሚቆጠሩ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች የእቅዱ ዝግጅት ላይም ሆነ አገራዊ ሪፓርቱ ላይ የነበራቸው ተሳትፎ በጣም ውስን የነበረ ሲሆን ከአራት አመት በፌት የታሰበው የእቅድ ዝግጅት ትግበራው መጀመር ከነበረበት ከሁለት አመት በላይ ዘግይቷል ሲሉ የመንግስትን ሪፓርት ይተቻሉ፡፡ባለፉት አራት አመታት ውስጥ የመንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት በፓሊሲ እና በማህበረሰባዊ ንቃተ ህሊና ላይ የሚሰሩት ስራ ተገድቦ ሙከራ የሚያደርጉትም ድርጅቶች ድርጅታዊ ህልውናቸውን በማስጠበቅ ላይ ሲገኙ የሰብአዊ መብት ሁኔታን አስመልክቶ አገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ተቋማትይህ ነው የሚባል ነገር ሲናገሩ አልተሰማም፡፡ይህ በህጉ የተነሳ በተግባር እየታየ ያለው የተቋማት በመብቶች ዙሪያ አለመስራት እግድ በሴቶች መብቶች፣ በህጻናት መብቶችና በአካል ጉዳተኝነት የሚሰሩ ድርጅቶችን ሳይቀር ስራቸውን እንዲቀይሩ አስገድዷቸዋል፡፡ በከፍተኛ ሁኔታ በአገሪቱ ብዙ ክፍሎች ይንቀሳቀሱ የነበሩ እንደ ህግ ባለሞያ ሴቶች ማህበር ያሉ ተቋማት ስራቸውን አዲስ አበባ ላይ ብቻ በማተኮር አንድ ቢሮ ውስጥ ካደረጉ ከራረሙ፡፡ በተጨማሪም ጸረ ሽብርተኛነት አዋጁ በተግባር በመዋል በመቶዎች የሚቆጠሩ የሽብር ክስ ሰለባዎች እነዲፈረድባቸው ያደረገ ሲሆን ጋዜጠኞች የመጀመሪያው ረድፍ ላይ ይገኛሉ፡፡

የጋዜጦች ቁጥርና ጥራት በወረደበት ፣ የእስረኞች አያያዝ ከቶርቸር ጋር መቀላቀሉን የተለያዩ የፓለቲካ ፓርቲ አመራር እና አራማጅ እስረኞች እየተናገሩ ባሉበት ፣ አሁንም አንድም የግል ቴሌቪዥን እና ገለልተኛ የሚዲያ ተቋም በሌለበት ፣ አሁንም ሰዎች በፓለቲካ አመለካከት ልዩነታቸው እስር ቤት እነደገቡ ብዙዎች እያመኑ፣ አፋኝ ህጎቹ ከስጋት በላይ በተግባር ተጽእኖአቸው በሚታይበትና መጪው ምርጫ አንድ አመት ሲቀረው ሁለተኛው ዙር የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ጉባኤ የኢትዮጲያ ግምገማ ይካሄዳል፡፡ መንግሰት ምን ያህሎቹን የማሻሻያ ሃሳቦች ይቀበል ይሆን ምን ያህሎቹንስ ይቃወም ይሆን ? በዝርዝር ለማየት ፍላጎት ላደረባችሁ ሚያዝያ 28 የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ጉባኤ ድረ ገጽ ላይ መመልከት በቀጥታ ሰርጭታቸው መመልከት ትችላላችሁ፡፡

Wednesday, April 23, 2014

በሕገመንግሥታዊ መብቶቻችንን ተጠቅመን ስለሕገመንግሥታዊነት መነጋገራችንን እንቀጥላለን!

ዞን ዘጠኝ ከተመሠረተ ድፍን ሁለት ዓመት ሊሞላው ከአንድ ወር ያነሰ ጊዜ ቀረ፡፡ ከዞን 9 ነዋሪዎች ለመጨረሻ ጊዜ ከዞኑ ጽሑፍ ያነበቡት ደሞ የዛሬ ስድስት ወራት ገደማ ነው፡። ዳግመኛ በብርታት መመለሳችንን ልናሳውቅ ስንነሳ ምነው ‹እስከዛሬ የት ነበራችሁ?› የሚል ጥያቄ መነሳቱ ስለማይቀር አጭር መልስ ለመስጠት መሞከራችን አግባብ ነው፡፡
የመጥፋታችን አንዱና ትንሹ ምክንያት የግል ቁርጠኝነታችንን በነበረበት ሁኔታ መቀጠል አለመቻሉ ነበር፡፡የቡድን አራማጅነት ሙሉ በሙሉ የበጎ ፍቃደኝነት ስራ እንደመሆኑ መጠን በግል ህይወታችንና በበጎ ፍቃደኝነት በምንሰራው የቡድን አራማጅነታችን መካከል ሚዛን መጠበቅ ከብዶን አንገዳግዶናል፡፡ ይህ ተግዳሮት ግን ብቻውን አልነበረም፡፡ አገራችን ኢትዮጵያ ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት በሚገባ የሚታፈንባቸው አገራት አንዷ መሆኗን ከዚህ ቀደም ከምናውቃቸው ምሳሌዎች በተጨማሪ በተለይ ባለፋት ስድስት ወራት በተግባር አይተነዋል፡፡
ለነገሩ የዜጎች ሐሳብን መግለጽ በገዢዎቻችን ዓይን የነውር ያክል እንደሚቆጠር የተረዳነው ገና ቡድናችን ሥራውን በይፋ የጀመረ ሰሞን አንድ ዞን ዘጠኛዊ ላይ በደረሰ ግልጽ ማስፈራሪያ ነበር፡፡ ከማኅበራዊ አውታሮች እምብዛም ያልወረዱ እንቅስቃሴዎችን ዝም ብለን ስንቀጥል፣ በከፊል የተረሳን መስሎንም ነበር፡፡ ከወራት በፊት መልሶ የት ወጡ፣ የት ገቡ፣ ምን አደረጉ የሚሉ ጥያቄዎች እና ክትትሎች በዙሪያችን እየተደረጉ እንደሆኑ እና በአንድም በሌላም መንገድ፣ ከዞኑ አባላቶችና ወዳጆችም ጭምር ከ‹‹ደኅንነቶች›› በመጡ መልዕክቶች የማናውቀው ስህተት እየተፈለገብን እንደሆነ አውቀናል፡፡
ይህም እስከዛሬ የምናወቀውን ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ አፈናን በተቋማትና በባለሞያዎቹ ላይ ብቻ ሳይሆን እንደ ዞን ዘጠኝ ባሉ እጅግ በጣም ኢመደበኛ በሆኑ የግለሰቦች ስብስቦችን ሰለባ የማድረግ አቅም እንዳለው እንድንረዳ እድል ሰጥቶናል፡፡ በዚህ እውነታውን የማየት፣ የማሰብና የሥራችንን ዓላማ በስህተት የተረዱ ናቸው ብለን ካሰብናቸው አካላት ጋር ካደረግነው ውይይት በመነሳት ‹ዝምታ ወርቅ› አለመሆኑን አውቀን ተመልሰናል፡። ከዚህ በኋላ የሚከሰቱ እና ከእንቅስቃሲያችን የሚያርቁንን የግል፣ የቡድን ወይም የውጪ ግፊት ጉዳዮችን በፍጥነት ለዞን ዘጠኝ ነዋሪያን ከነዝርዝር ምክንያቱ ለማቅረብ ቃል እንገባለን፡፡
ሁለቱ አመት ጉዞአችን እንዳደረግነው ሁሉ የተለያዩ ጽሁፎችን ማቅረብ ዘመቻዎችን በማዘጋጀት የተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች ላይ ማወያየታችንን እንቀጥላለን፡፡ በሚቀጥለው የሦስተኛ ዓመት የመነሻ ጉዞአችን የተለመዱ የዞኑን ስራዎች ጨምረን አዳዲስ እና ትኩረት የሚገባቸው ወቅታዊ ሥራዎችን ለውይይት ይዘን ለመቅረብ እንሞክራለን፡፡ ሦስተኛ ዓመታችን ከሚጀምርበት ጊዜ አንስቶ እንደተለመደው በወቅታዊ ጉዳዎች ላይ የሚያተኩሩ ሦስተ ዘመቻዎችን እና ተያያዥ ሥራዎችን ይኖሩናል። ዓመቱ በየአምስት ዓመቱ የሚካሄደው ብሔራዊ ምርጫ ዓመት በመሆኑም ጭምር የሥራዎቻችን ትኩረት ወደዚያ ቢሳብ ነዋሪዎች እንደሚረዱት ተስፋ እናደርጋለን፡፡ ብዙ የዞኑ ነዋሪያን እንደሚያስታውሱትና ዞኑ ዋና እሴት የሆነው የንግግርና ተዋስኦን ለማበረታታት እና ትውልዱ የራሱ ትርክት እንዲኖረው የበኩላችንን አስተዋእጾ ለማድረግ የምናደርገው ጥረትም ይቀጥላል፡፡ በዚህም መሠረት ጽሑፎቻችሁን ብታጋሩን ለነዋሪያን የመወያያ ርዕስ ለማድረግ መሞከሩን ሥራ አጠናክረን እንገፋበታለን ፡፡ ሁላችንም የዞን9 አባላት ሃሳብን በነጻነት ለመግለጽ መብት ፣ ለዴሞክራሲ ውይይትና ለሰብአዊ መብት አራማጅ መሆን ህገ ወጥና ሊደበቅ የሚገባው ተግባር ነው ብለን ስለማናምን የአራማጅነት ሚናችን በመጪው ሶስተኛ አመትም እንደበፌቱ ይቀጥላል፡።
መጥፋታችን ያሳሰባቸው፣ የዞን 9 አስተዋእጾን በበጎ የሚያስታውሱ ምክንያት እስከመጠየቅ ጀምሮ እስከማበረታቻ ድረስ ሲለግሱ የነበሩ ግለሰቦችን በማመስገን የምንጀምረው የእናንተ አስተያየት ለመመለስ ካሰብንበት ጊዜ ጀምሮ አንዱ ማበረታቻ መሆኑን ስለምናምን ነው፡፡ ጥያቄዎች ጠይቃችሁ ያልመለስንላችሁ፣ እንደተለመደው ጽሑፎቻችሁን ልካችሁ ያላስተናገድናቸው፣ ለኢሜይል መልእክቶቻችሁ ምላሽ ላልሰጠናችሁ ምናልባትም ብዙ ጠብቃችሁን በቦታው ላላገኛችሁን ሁሉ ይቅርታችሁ ይገባናል፡፡
አሁንም፤ ስለሚያገባን እንጦምራለን!!