Friday, August 28, 2015

የኢትዮጵያ ‹የፀረ-ሽብርተኝነት› ሕግ ሲዘከር


ምክር ቤቱ ከሌሎች ጊዜያት የሚለየው በዛ ያሉ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትን የያዘ በመሆኑ ነው - የአወዛጋቢው ምርጫ 97 ውጤት የሆነው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፡፡ እናም ለዚህ ምክር ቤት ሲቀርቡ የነበሩ ብዙ ሕጎች በሚቀርቡበት ወቅት ውዝግብ ማስከተላቸው አልቀረም ነበር፡፡ ገዢው ፓርቲ ‹ሕጎቹ ዴሞክራሲን እና ልማትን የሚያሳልጡ ናቸው› እያለ ሲዘምር፤ በምክር ቤት የሚገኙ የተቃዋሚ አባላት ደግሞ ‹ሕጎቹ የገዢውን ፓርቲ ስልጣን ለማራዘም ዜጎችን ለማጥቃት የተዘጋጁ መሳሪያዎች ናቸው› በማለት በተገደበች ደቂቃቸው ይሟገቱ ነበር፡፡
የዚህ ማስታዎሻ መነሻ የሆነው ጉዳይም የተከሰተው አወዛጋቢው ምክር ቤት የአራተኛ ዓመት ስራውን ለማጠናቀቅ አምስት ቀናት ብቻ ሲቀሩት በሰኔ 25/2001 ነው፡፡  በዕለቱ ምክር ቤቱ ከተመሰረተበት 1987 ጀምሮ ካፀደቃቸው ስድስት መቶ ሃምሳ አንድ አዋጆች ጠንካራውን እና እጅግ አወዛጋቢ የሆነውን ሕግ ለማፅደቅ ኮረም ተሟልቶ ስራውን ጀመረ፡፡ ብዙም ሳይቆይ በተለመደው መልኩ በዘጠና አንድ ተቃውሞ፣ በአንድ ድምፀ ተዓቅቦ እና በሁለት መቶ ሰማኒያ ስድስት የድጋፍ ድምፅ አዋጅ ቁጥር 652/2001ን ‹የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ› በሚል ርዕስ አፀደቀ!  ነገር ግን አዋጁ ተግባራዊ የሚሆነው በፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ሲወጣ (አዋጅ ቁጥር 3/1987 እንደሚደነግገው) በመሆኑ ወደ ተግባር ለመሻጋገር ሁለት ወራት ገደማ ፈጅቶበት በነሃሴ 22/2001 በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ በመውጣት ስራውን ጀመረ!
እንግዲህ በዋናነት ስራውን ከምርጫ 2002 ማግስት ጀምሮ ያደረገው ይህ አዋጅ በነጋሪት ጋዜጣ ወጥቶ ተግባራዊ መሆን ከጀመረ ዛሬ ነሃሴ 22/2007 ድፍን ስድስት ዓመት ሞላው፡፡ አዋጁ በተለያዩ ዓለማቀፍ የመብት ተቋማት እና ምዕራባዊ መንግስታት እጅግ ከፍተኛ ተቃውሞ እየደረሰበት ይገኛል፡፡ ‹አዋጁ ከሕገ-መንግስቱ አንቀፆች ጋር ይጋጫል› ብለው ምሁራን እየተቹት ይገኛል፡፡ አዋጁ ‹ሽብርተኝነት›፣ ‹ጋዜጠኝነት›፣ ‹ተቃዋሚነት›፣ ‹ፋኖነት›፣ ‹ጦማሪነት› … የተባሉ ጉዳዮችን አንድ በማድረግ ሁሉንም በመደዳ እያጠቃ ይገኛል፡፡ በመንግስታዊ የመገናኛ ብዙሃን አዋጁን ‹ለመከላከል› ከየትኛውም ሕግ በላይ በዛ ያሉ ዶክመንታሪዎች ተሰርተውለታል (ለምሳሌ አዲስ ግንባር፤ ጀሃዳዊ ሃረካት፤ አዲስ አበባን እንደ ባግዳድ…)፣ አዋጁ ለፀጥታ ተቋማት (ለደህንነትና ለፖሊስ) ሰፊ መብት የሚሰጥ በመሆኑ አዋጁን መሰረት በማድረግ የሚያዙ ሰዎች እጅግ ከፍተኛ ማሰቃየትና ድብደባ (CITDs) እየደረሰባቸው ይገኛል፤ አዋጁን ለማስፈፀም በሚል ከአዋጁ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ብቻ ለማዬት ‹ልዩ የወንጀል ችሎት› ተቋቁሞለታል (የቀድሞው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት የአሁኑ 19ኛ ወንጀል ችሎት)፤ አዋጁ ይሻሻል/ይሰረዝ ዘንድ ከአንድ ሚሊዮን የሚበልጥ የሕዝብ ፊርማ ተሰባስቦ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን ጨምሮ ለተለያዩ የመንግስት አካላት ቀርቧል (እስከ አሁን ድረስ ምላሽ ባያገኝም)፤ አዋጁ ከመቶ በላይ የሚሆኑትን የኢፌደሪ የወንጀል ሕግ አንቀፆች (ከአንቀፅ 238 – 353) በተግባር ‹ጥቅም አልባ› አድርጓቸዋል … በአጠቃላይ የኢፌደሪ መንግስት ከተቋቋመበት 1987 ጀምሮ እስከ ሰኔ 30/2007 ድረስ ባሉት ሃያ ዓመታት ውስጥ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ካፀደቃቸው ወደ ዘጠኝ መቶ የሚጠጉ አዋጆች ውስጥ እንደ አዋጅ ቁጥር 652/2001 አስፈሪ አዋጅ አለ ማለት ይከብዳል፡፡
አዋጁ ያልነካው/የማይነካው የስራ ዘርፍም ሆነ ግለሰብ የለም፡፡

1.      ሕዛባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) በተመሰረተ በ10ኛው ወር (ጥቅምት 1968) ፓርቲውን ተቀላቅለው ደርግን ለመጣል የተደረገውን ትግል ዳር ያደረሱት የስልሳ ዓመቱ አቶ አማረ ተወልደ ዛሬ ‹አሸባሪ› ተብለው የአዋጁ ሰለባ በመሆን በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡

2.     በምርጫ 1997 ቅንጅትን በመወከል (የኢዴፓ-መድህን አባል የነበረ) ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ ተወዳድረው በማሸነፍ የምክር ቤት አባል የነበሩት አቶ አግባው ሰጠኝ የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጁ በፀደቀበት ወቅት አዋጁን አምርረው የተቃወሙ እና የተቃውሞ ድምፅ የሰጡ ሲሆን፤ ለዛ ተቃውሟቸው ምላሽ ይመስላል ዛሬ በአዋጁ መሰረት ክስ ተመስርቶባቸው በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡


3.     የጋምቤላ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጋሕዴን) አባል በመሆን የጋምቤላ ክልል የክልል ምክር ቤት አባል የነበሩት አቶ በኳች ማሞ ደርግን ለመጣል በተደረገው ትግል ውስጥ ተሳታፊ የነበረው እና በአሁኑ ወቅት በሽብርተኛ ድርጅትነት የተፈረጀው የጋምቤላ ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄ (ጋሕነን) አባል ነህ ተብለው ያለመከሰስ መብታቸው እንኳን ሳይነሳ በፀረ-ሽብርተኝነት አዋጁ መሰረት ተከሰው በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡


4.     የኦሮሞ ነፃ አውጭ ግንባርን (ኦነግ) በ1978 በመቀላቀል እስከ 1985 ድረስ አብሮ በመቀጠል ደርግን የጣሉት እና በ1985 ደግሞ ተሃድሶ በመግባት ወደ ግብርና ሙያጨው  የተመለሱት የሃምሳ ሁለት ዓመቱ ዳንኤል አኩማ አሁን በአዋጁ መሰረት ‹የኦነግ አባል ነህ› ተብለው በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡

5.     ወጣቱ ሃዊ ደላን የፎቶ ሾፕ ጥበብን የተካነ ሲሆን ‹We are Soldiers of the World› የተባለውን የሲሊቬስተር ስታሎንን የፊልም ፖስተር በመውሰድ ራሱን ከኦሳማ ቢንላደን ጋር አስቀምጦ ፎቶውን ኤዲት በማድረግ ፌስቡክ ላይ በመለጠፍ ከጓደኞቹ ጋር ለመቀላለድ ቢሞክርም ይህ ድርጊቱ ግን ከፀረ-ሽብርተኝነት አዋጁ ሊያመልጥ አልቻለም፡፡ ሃዊ በአሁኑ ወቅት ‹እኛ የአለም ወታደሮች ነን (We are Soldiers of the World) በማለት በፌስቡክ ዜጎችን ለሽብር ቀስቅሰሃል› ተብሎ በፀረ-ሽብርተኝነት አዋጁ አንቀፅ 6 መሰረት ተከሶ በእስር ላይ ይገኛል፤ ጉዳዩም ከባድ ነው በሚል በዝግ ችሎት እየታየ ይገኛል፡፡

6.     የሰባ አምስት ዓመቱ ሽማግሌ ፒሊማን ኩዎት የሃያ ስድስት ልጆች አባት ሲሆኑ ስራቸውም በዚህ እድሜያቸው የጋምቤላ ክልል ልዩ ሃይል ምክትል ሃላፊነት ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ‹የጋምቤላ ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄን (ጋሕነን) የተባለ የሽብርተኛ ድርጅትን ትረዳለህ› ተብለው በአዋጁ መሰረት ተከሰው በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡
7.      የአስራ ስድስት ዓመቱ አብዱ ሃሚዝ በአስራ አንድ ዓመቱ ሱዳን በቆሎ ቆረጣ ስራ በወጣበት በቤሕነን (የቢኒሻንጉል ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄ) ወታደሮች ተጠልፎ ወደ ኤርትራ በመሄድ ኤርትራ ከአምስት ዓመታት በላይ ቆይቶ ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት ሲሞክር ተያዞ (በዓለማቀፍ ሕግ Child Solider ቢሆንም) በአዋጁ አንቀፅ 7 (1) መሰረት ተከሶ የአራት ዓመት ፍርድ ተፈርዶበት አሁን በእስር ላይ ይገኛል፡፡ … እነዚህ ለምሳሌ ያህል ያነሳናቸው ጉዳዮች በሚዲያ ከሚዘገቡት የፖለቲከኞች፣ ፀሃፊዎችና ጋዜጠኞች ጉዳይ ባለፈ የምናገኛቸው እና ሕጉ እንዴት እየተገበረ ያለ እንደሆነ ለማሳየት ያህል ይረዱናል በሚል ነው፡፡ ነገር ግን እነዚህ ምሳሌዎች በጣም ትንሽ ሲሆኑ፤ ባለፉት ስድስት ዓመታት ውስጥ ሕጉ እጅግ ብዙ ዜጎችን ሰለባ አድርጓል፡፡ በዛሬው ዕለትም የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 ባለፉት ስድስት ዓመታት ውስጥ ሰለባ ያደረጋቸውን ግለሰቦች ስም ዝርዝር (ሙሉ ዝርዝሩ አልቀረበም)፣ ተያይዘው የተከሰሱበት ድርጅት/ቡድን እና የተከሰሱበትን የአዋጁን አንቀፆች በማስቀመጥ ስለሰለባዎቹ እንነጋገር ዘንድ እንዲህ አቅርበናቸዋል፡፡ የተለያዩ ‹የሽብር ቡድኖችን አቋቁማችኋል› በሚል በፀረ-ሽብርተኘነት አዋጁ መሰረት የተከሰሱ ሙስሊም ግለሰቦች፡


·         የፌ/ዓ/ሕ/መ/ቁ 122/05 ‹የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ› የሚል ‹የሽብርተኛ ድርጅት› በማቋቋም በሚል ክስ፡

1.      አቡበከር አህመድ ሙሐመድ
2.     አህመዲን ጀበል
3.     መከተ ሙሄ መኮንን
4.     ካሚል ሸምሱ ሲራጅ
5.     በድሩ ሁሴን ኑርሁሴን
6.     ያሲን ኑሩ ኢሳ
7.     ሳቢር ይርጉ ማንደፍሮ
8.     መሀመድ አባተ ተሰማ
9.     አህመድ ሙስጠፋ ሀቢብ
10.   ሙራድ ሽኩር ጀማል
11.     አቡበከር አለሙ ሙሔ (ጋዜጠኛ)
12.    ኑሩ ቱርኪ ኑሩ
13.    ባህሩ ዑመር ሽኩር
14.   ሙኒር ሁሴን ሀሰን
15.    ሰዒድ አሊ ጀውሀር
16.   ዩሱፍ ጌታቸው  (ጋዜጠኛ)
17.    ሙባረክ አደም ጌቱ
18.   ካሊድ ኢብራሒም ባልቻ
19.   አብዱረዛቅ አክመል ሀሰን
20.  አሊ መኪ በድሩ
21.    አብሩዱራህማን ኡስማን ከሊል
22.   ሐሰን አሊ ሹራብ
23.   ሱልጣን ሐጂ አማን
24.  ጀማል ያሲን ራጁ
25.   ጣሂር አብዱልከድር
26.  ሐሰን አቢ ሰይድ
27.   ሐጂ ኢብራሂም ቶይፋ
28.  ሀቢባ ሙሐመድ
29.  ከማል ሐጂ ገለቱ ማሜ
3 (1, 2, 4 እና 6)፣ አንቀፅ 4 እና 7 (1)
·         የፌ/ዓ/ሕ/መ/ቁ 225/06 ‹የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ› የተባለ ‹የሽብርተኛ ድርጅት› ጋር ግንኙነት በማድረግ በሚል ክስ፡

1.      ኤልያስ ከድር ሽኩር
2.     ሙባረክ ከድር ሀሰን
3.     ቶፊቅ መሀመድ ዑመር
4.     ፈይሰል አርጋው ኡመር
5.     አብዱልመጅድ አብዱልከሪም
6.     እስማኤል ሙስጠፋ ሀሰን
7.     ሬድዋን አብደላ አህመድ
8.     አንዋር ሱልጣን መሀመድ
9.     አብዱላዚዝ ፋቱደን በድሩደን
10.   ዳፋር ዲጋ ሀሰን
11.     ፋሩቅ ሰዒድ አብዶ
12.    መሪማ ሀያቱ ዑመር
13.    መሀመድ ዓሊ ሀሰን
14.   መሀመድ አይለየን ገማ
15.    አቡበክር ሰልማን ሙሳ
16.   ሙዓዝ ሙደስር አወል
አንቀፅ 7(1)

·         የ/ፌ/ዓ/ሕ/መ/ቁ 216/06  ‹የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ› የተባለ ‹የሽብርተኛ ድርጅት› ጋር ግንኙነት በማድረግ በሚል ክስ፡

1.      አብዱልአዚዝ ጀማል አብዱ
2.     ጅብሪል ይመር አበጋዝ
3.     ስዑድ ሙሳ ሁሴን
4.     ሀያት አህመድ ረዲ
5.     ሳላሀዲን ሙሀመድ አህመድ
አንቀፅ 7(1)


·         የፌ/ዓ/ሕ/መ/ቁ 666/07 ‹የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ› የተባለ ‹የሽብርተኛ ድርጅት› ጋር ግንኙነት በማድረግ በሚል ክስ፡

1.      ከድር መሃመድ ዩሱፍ
2.     ነዚፍ ተማም ሙስጠፋ
3.     ኽሊድ መሃመድ አህመድ
4.     ፉአድ አብዱልቃድር አሊ
5.     ኢብራሂም ከማል ኢሳ
6.     አብዱጀባር አብዱላ ኢብራሂም
7.     ሁሴን አህመድ አባደጋ
8.     ሃሚድ መሃመድ ሻፊ
9.     ቶፊቅ ሚስባህ ያሲን
10.   ዑስማን አብዲ መሃመድ
11.     መሃመድ ኑሪ ተሰሙ
12.    አብዱልሃፊዝ ሻፊ ሙቅተባ
13.    ዳርሰማ ሶሪ ባንቀሽ
14.   ፍፁም ቸርነት ኃ/ማሪያም
15.    ሀሩን ሃይረዱን ሃቢብ
16.   ሸህቡዱን ኑረዲን
17.    አያተልከብራ ነስረዲን
18.   ሃሺም አብደላ አወል
19.   ሙጂብ አሚኖ ሰኢድ
20.  መሃመድ ከማል አባመልካ
አንቀፅ 7(1)

·         የ/ፌ/ዓ/ሕ/መ/ቁ 164/06

1.      አህመድ ኢድሪስ ገበየሁ
2.     አንዋር ኡመር ሰዒድ
3.     ሷሊህ መሀመድ አብዱ
4.     አደም አራጋው አህመድ
5.     አብዱራህማን እሸቱ መሀመድ
6.     ኢብራሒም ሙሔ ይማም
7.     ዑመር ሁሴን አህመድ
8.     ይመር ሁሴን ሞላ
9.     ሙባረክ ይመር አየለ
10.   እስማኤል ሀሰን ይመር
11.     ከማል ሁሴን አህመድ
12.    አብዱ ሀሰን መሀመድ
13.    አህመድ ጀማል ሰይድ
14.   ሙሀመድ ዩሱፍ መሀመድ
አንቀፅ 3 (1 እና 2)

·         ‹አል -ኻዋሪጅ› የተባለ ‹የሽብርተኝነት ድርጅት› በማቋቋም በሚል ክስ፡

1.      ጃፋር መሀመድ አባረዳ
2.     መሀመድኑር ግዛው ሀ/ሚካኤል
3.     ሀጂ ሙሀመድ ሳኒ አባዋጂ
4.     ሙህዲን ጀሚል ያሲን
5.     አህመድ አባቢያ አባሪጉ
6.     አንዋር ትጃኔ አባጨብሳ
7.     ሼህ ጀሚል አባጨብሳ አባጎዱ
አንቀፅ 7(1)

·         ‹ፉርቀቱ ልናጀያ ሙስሊም ጀምዓ› የተባለ ‹የሽብርተኝነት ድርጅት› በማቋቋም በሚል ክስ፡ 

1.      ዙቤር ቢቂላ አባወጃ
2.     ተወከልዬ ግርማዬ ቡልቻ
3.     አወል አበፈጫ አባጨብሳ
አንቀፅ 3(1)(2) እና (4)

·         ‹ፈርቀቱ ልናጀያ ሙስሊም ጀምዓ› የተባለ ‹የሽብርተኝነት ድርጅት› በማቋቋም በሚል ክስ፡ 

1.      በድሩ አባቦር
2.     መሃመድ አሚን
3.     አወል አባሜጫ
4.     አብዱልአዚዝ አባዝናብ
5.     ጣሂር አባኑራ
6.     ሳቢት ከድር
7.     አወል ሱልጣን
8.     መሃመድ አባጋሮ
9.     አብዱ ሁሴን

አንቀፅ 7 (1) እና (2)

·         ‹አል ሸባብ› የተባለ ‹የሽብርተኛ ድርጅት› አባል በመሆን በሚል ክስ፡

1.      ሃሰን ጃርሶ ቆቶላ (ኬኒያዊ)
2.     መሃመድ ቃሲም
3.     ዑመር ሙሳ
4.     አብዲሽኩር ዳውድ
5.     በሽር ሃ
6.     ዩሱፍ ሃሰን
7.     መሐመድ ሳፊ
8.     ሙስጠፋ ዑመር
9.     አብድራህማን ሁሴ
10.   አብዱል ለጢፍ
11.     ከድር ሙስጠፋ
አንቀፅ 4 እና አንቀፅ 7 (1)

·         ‹አል ሸባብ› የተባለ ‹የሽብርተኛ ድርጅት› አባል በመሆን እና ሌሎች የሀገር ውስጥ የጅሃድ ቡድኖችን በማቋቋም በሚል ክስ፡

1.      አማን አሰፋ
2.     ኑሪ ሙዘይን አህመድ
3.     ሰለሞን ከበደ (ጋዜጠኛ)
4.     አብዱል ፈታህ ሸሪፍ
5.     ኑረዲን ሙሃመድ አብደላ
6.     ሙፍቲ ሙሃመድ
7.     አንዋር አደም (አሜሪካዊ)
8.     ጀማል ሀሰን አህመድ
9.     ኢብራሂም አብዱ
10.   አህመድ ማሞ
11.     ሙሃመድ አብዱልቃድር
12.    ሙሃመድ ኑር አብደላ
13.    ሰለሃዲን ሰኢድ የሱፍ
14.   ሳዳም አብዱረህማን
15.    ሁሴን ሮባ
16.   አብዱረዛቅ ሸህ አህመድ
17.    እንድሪስ አልይ
18.   እድሪስ አህመድ
19.   ኢብራሂም ኪያ
20.  ሙሃመድ አህመድ
21.    አጋሱ ሁሴን
22.   የዚድ ጀማል
23.   ኢብራሂም የሱፍ
24.  ጃእፈር
25.   አብዱ አሊ
26.  አብዱረህማን ቢላል
27.   ሙሃመድ አህመ

አንቀፅ 3 (1) (2) እና አንቀፅ 7 (1)
‹የኦሮሞ ነፃ አውጭ ግንባር› (ኦነግ) አባላት ናችሁ ተብለው በአዋጁ የተከሰሱ ግለሰቦች፡

·         በፌ/ዓ/ሕግ/መ/ቁ 376/06

1.      ጀልዴሳ ዋቆ ጃርሶ
2.     ገልገሎ ጉዮ ቦሩ
3.     ዋርዮ ጣጤሳ ጉዮ
አንቀፅ 3 (1 እና 2) እና 7 (1)

·         በእነ አብዲ ከማል የክስ መዝገብ

1.      አብዲ ከማል የሱፍ
2.     ቶፊቅ ረሽድ ዩያ
አንቀፅ 7 (1)

·         የፌ/ዓ/ሕ/መ/ቁ 106/07

1.      ዳንኤል አኩማ ፉፋ
2.     አስፋው ልሳና ናደው
አንቀፅ 3(1) እና (4)

·         የፌ/ዓ/ሕ/መ/ቁ 35/07

1.      አበበ ኡርጌሣ ፎከንሣ
2.     መገርሣ ወርቈ ፋይሳ
3.     አዱኛ ኬሳ አደሩ
4.     ቢሉሱማ ደመና ስዩም
5.     ተሻለ በቀለ ገርባ
6.     ሌንጅሳ አለማየሁ
አንቀፅ 7(1)፣ 3 (1) (4) እና (6)
‹የዴሞክራሲ ምንቅስቃስ ሕዝቢ ትግራይ› (ዴምሕት) አባላት ናችሁ ተብለው በአዋጁ የተከሰሱ ግለሰቦች፡

·         በእነታሪኩ በላይ ፍስሃ የክስ መዝገብ

1.      ታሪኩ በላይ ፍስሀ
2.     አማረ ተወልደ መነህ
አንቀፅ 7(1)

የቤኒሻንጉል ሕዝቦች ነፃ አውጭ ንቅናቄ (ቤሕነን) አባላት ናችሁ ተብለው በአዋጁ የተከሰሱ ግለሰቦች፡

·         በእነ አብዱልከሪም አብዱሰመድ የክስ መዝገብ

1.      አብዱልከሪም አብዱሰመድ አብዱልቃድር
2.     ሀዋጃ ሚነላ አጉር
3.     ኢሳቅ ኢብራሒም ዓሊ (ዕድሜ 17)
4.     አጄላ ጃባላ ንምር
5.     አብዱ ሀሚዝ ፈረንሳ (ዕድሜ 16)
6.     ፋተልሙላ አጣሂር አከሶ
አንቀፅ 7 (1)

·         የፌ/ዓ/ሕ/መ/ቁ 168/07

1.      አብዱልወሀብ መሃዲ ኢሳ
2.     አብዱረህማን ናስር አህመድ
3.     ኩርፊል ጀማ ናስር
4.     ያሲር ጀበል ነጉራ
5.     ኢማያ አብዱረዛቅ አብዱላሀ
6.     ደፋኢል መሀመድ አብዱልሃሰን
7.     አደም በዳዊ ባባክር
8.     ሙደወኪል ከሚል ሙባረክ

አንቀፅ 3(1) እና (2)


‹የግንቦት ሰባት ለፍትህና ለነፃነት ድርጅት› እና ‹የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር› አባላት ናችሁ ተብለው በአዋጁ የተከሰሱ ግለሰቦች፡

·         በእነ ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ የክስ መዝገብ

1.      ጄነራል ተፈራ ማሞ
2.     ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ
3.     አንዳርጋቸው ፅጌ
4.     መስፍን አማን
5.     ሙሉነህ እዩኤል
6.     መላኩ ተፈራ
7.     አሳምነው ፅጌ
8.     ሌ/ኮ ደምሰው አንተነህ
9.     ሻለቃ መኮንን ወርቁ
10.   አበረ አሰፋ
11.     ሌ/ኮ ዓለሙ ጌትነት
12.    ሌ/ኮ ሠለሞን አሻግሬ
13.    ሌ/ኮ ጌታቸው ብርሌ
14.   ሻምበል ተመስገን ባይለየኝ
15.    ሌ/ኮ ፋንታሁን ሙሃባ
16.   ሻለቃ መሰከረ ካሣ
17.    ሻምበል ምስጋናው ተሰማ
18.   ክፍሌ ስንሻው
19.   የሽዋስ መንገሻ
20.  መንግሥቱ አበበ
21.    እማዋይሽ ዓለሙ
22.   ጎሽይራድ ፀጋው
23.   ሳጅን አመራር ባያብል
24.  ምክትል ሳጅን ጎበና በላይ
25.   ረዳት ሳጅን ይበልጣል ብርሃኑ
26.  ምክትል ሳጅን የሺዋስ ምትኩ
27.   ውድነህ ተመስገን
28.  ጌቱ ወርቁ
29.  ፅጌ ኃብተማርያም  (ዕድሜ 80 ዓመት)
30.  ሌተናል ኮሎኔል አለበል አማረ
31.     ያረጋል ይማም
32.    ዳንኤል (ዳን)
33.    አወቀ አፈወርቅ
34.   ኤፍሬም ማንዴቦ
35.    ዳንኤል አሰፋ
36.   ቸኮል ጌታሁን
37.    ፋሲል የኔዓለም (ጋዜጠኛ)
38.   ደረጀ ሀብተወልድ (ጋዜጠኛ)
39.   አዱኛ ዓለማየሁ
40.  አደፍርስ አሳምነው
አንቀፅ 3 እና 4

·         የፌ/ዓ/ሕ/መ/ቁ 00180/04
1.      አንዱዓለም አራጌ ዋለ
2.     ናትናኤል መኮንን ገ/ኪዳን
3.     ዮሃንስ ተረፈ ከበደ
4.     ሻምበል የሽዋስ ይሁንዓለም
5.     ክንፈሚካኤል ደበበ በረደድ (አበበ ቀስቶ)
6.     ምትኩ ዳምጠው ውርቁ
7.     እስክንድር ነጋ ፈንታ (ጋዜጠኛ)
8.     አንዱዓለም አያሌው ገላው
9.     አንዳርጋቸው ፅጌ
10.   ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ቦንገር
11.     ውቤ ሮቤ
12.    ኤፍሬም ማዴቦ
13.    መስፍን አማን
14.   ዘለሌ ፀጋስላሴ
15.    ፋሲል የኔአለም (ጋዜጠኛ)
16.   አበበ በለው (ጋዜጠኛ)
17.    አበበ ገላው (ጋዜጠኛ)
18.   ንአምን ዘለቀ
19.   ኤልያስ ሞላ
20.  ደሳለኝ አራጌ ዋለ
21.    ኮ/ሌ አለበል አማረ
22.   ኦባንግ ሜቶ፣
23.   መስፍን ነጋሽ (ጋዜጠኛ)
24.  ዓብይ ተ/ማሪያም (ጋዜጠኛ)
አንቀፅ 3 (1) (2) (4) እና አንቀፅ 5 (1)

·         የፌ/ዓ/ህ/መ/ቁ 071/06 

1.      ማስረሻ ታፈረ ወ/ገብርኤል
2.     ሻለቃ አለምነው አየለ ነጋሽ
3.     ብርቁ አዲሱ ውቡ
4.     ታደሰ መንግስቱ በላይ
5.     የፀዳው ካሴ አሉላ
6.     አወቀ ደስታው ምህረቴ
7.     መሀመድ ግዛቸው ፋንታው
8.     ቴዎድሮስ ሀይሌ
9.     ታደሰ በለጠ
10.   ታደሰ ባዩ ገበየሁ
አንቀፅ 7(1)

·         የፌ/ዓ/ሕ/መ/ቁ 382/06

1.      መ/አ/ ጌታቸው መኮንን
2.     በላይነህ ሲሳይ ኮከቤ
3.     አለባቸው ማሞ መለሰ
4.     አወቀ ሞጃ ሆዴፈንታ
5.     ዘሪሁን በኔ ታረፋ
6.     ወርቅዬ ምስጋና ዋሴ
7.     አመረ መስፍን መለሰ
8.     ተስፋዬ ታሪኩ በዛብህ
9.     ቢሆነኝ አለነ ማረው
10.   ታፈረ ፋንታሁን አጉመሌ
11.     ፈጃ ሙሉ ዘገየ
12.    አትርሳው አስቻለው ተካ
13.    እንግዲያው ዋጀራ ወርቁ
14.   አንጋው ተገኝ አርጋው
15.    አግባው ሰጠኝ በሪሁን
16.   አባይ ዘውዴ በቀለ
አንቀፅ 7(1)

·         በእነ ዘመኑ ካሴ በእውቄ የክስ መዝገብ

1.      ዘመኑ ካሴ በእውቄ
2.     አሸናፊ አካሉ አበራ
3.     ደህናሁን ቤዛ ስመኝ
4.     ምንዳዬ ጥላሁን ለማ
5.     አንሙት የኔዋስ አለኸኝ
6.     ደሳለኝ አሰፋ ወንድማገኝ
7.     //ር ሙልየ ማናየ ረታ
8.     ጠጋው ካሳ እንየው
9.     ይህዓለም አካሉ አበራ
አንቀፅ 4፣ 5 እና 8·         የፌ/ዓ/ሕ/መ/ቁ 033/06

1.      ፀጋው አለሙ ተካ
2.     ዋሲሁን ንጉሱ ገብሬ
3.     ጎዳዳው ፈረደ ማሞ
4.     ማማይ ታከለ በየነ
5.     ተገኝ ሲሳይ መንገሻ
አንቀፅ 7 (1)

·         የፌ/ዓ/ሕ/መ/ቁ 174/06

1.      አስማማው ደሴ ጣሰው
2.     መብራታይ ይርጋ ተስፋዬ
አንቀፅ 7 (1)

·         የፌ/ዓ/ሕ/መ/ቁ 344/07

1.      መ/አ ማስረሻ ሰጤ ብሬ
2.     መ/አ ብሩክ አናዬ በሪ
3.     መ/አ ዳንኤል ግርማ ካሳ
4.     መ/አ ገዛኽኝ ድረስ ብዙነህ
5.     ተስፋዬ እሸቴ ውበት
6.     ሰይፉ ግርማ ተሰማ
አንቀፅ 7(1)

·         የፌ/ዓ/ሕ/መ/ቁ 26/07

1.      ብርሃኑ ተክለያሬድ አሰፋ
2.     እየሩሳሌም ተስፋው እንየው
3.     ፍቅረማሪያም አስማማው ዋለልኝ
4.     ደሴ ካህሳይ ቃልዬ

አንቀፅ 7(1)


·         የፌ/ዓ/ሕ/መ/ቁ 582/07

1.      ዘመነ ምህረት ታከለ
2.     ጌትነት ደርሶ አዱኛ
3.     መሰለ መሸሻ አናጋው
አንቀፅ 4 እና 7 (1) 
                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                          
·         የፌ/ዓ/ሕ/መ/ቁ 324/07

1.      አምሳሉ መስታየት ፀሃይ
2.     ኢሳያስ ማሩ ዓለሙ
3.     ጀጃው አለማየሁ ተፈራ
4.     ወርቁ ዳኘው ተዘራ
5.     አሳመረው አሰፋ እጅጉ
6.     አብነት ደሳለኝ ጫኔ
አንቀፅ 7(1)

·         የፌ/ዓ/ሕ/መ/ቁ 300/07

1.      ተረፈ ይታይህ ቢተው
2.     ሙሉጌታ ደምሴ አበበ
3.     ዘላለም እጅጉ ካሳ
4.     ታድለው ፈረደ
አንቀፅ 7(1)

·         የፌ/ዓ/ሕ/መ/ቁ 299/07

1.      ሃሰን ዳውድ
አንቀፅ 7(1)

·         የፌ/ዓ/ሕ/መ/ቁ 480/07

1.      ለምለሙ በሽሬው በላይ
2.     ት/ሚካኤል ት/ስላሴ ማለዳ
3.     አብዬ ተስፋ ልፎ
4.     እሸቴ ግርማይ በዜ
5.     ሃብታሙ ተረፈ ሙሉነህ
6.     አታሎ ደሳለኝ መኮንን
7.     ዶክተር ባየው አበራ
8.     መልካሙ ታደሰ ነገሰ
9.     ኃ/ማሪያም ገነት ተሾመ
አንቀፅ 7(1 እና 2)

·         የፌ/ዓ/ሕ/መ/ቁ 456/07

1.      ዘላለም ወርቅአገኘው (ጦማሪ)
2.     ሃብታሙ አያሌው
3.     ዳንኤል ሽበሺ
4.     አብርሃ ደስታ
5.     የሽዋስ አሰፋ
6.     ዮናታን ወልዴ
7.     አብርሃም ሰለሞን
8.     ሰለሞን ግርማ
9.     ባህሩ ደጉ
10.   ተስፋዬ ተፈሪ

አንቀፅ 4 እና 7 (1)

‹የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር›  (ኦብነግ) አባል እና ተሳታፊ በመሆን በሚል ክስ፡

·         በእነማርቲን ሽብ የክስ መዝገብ

1.      ማርቲን ካርል ሽብዬ (ሲዊድናዊ)
2.     ጁሃን ከርል ፐርሰን  (ሲዊድናዊ)
3.     አብዲወሊ መሐሙድ እስማኤል
4.     ከሊፍ አሊ ዳሂር

አንቀፅ 3 (1) (2) አንቀፅ 4 እና አንቀፅ 7 (1)


‹የጋምቤላ ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄ› (ጋሕነን) የተባለ የሽብርተኛ ድርጅት› አባል በመሆን የሽብርተኝነት ድርጊት መፈፀም በሚል ክስ፡

·         በእነኡመድ ኡከት ኡመድ የክስ መዝገብ

1.      ኡመድ ኡከት ኡመድ
2.     ኡጁሉ ገመቹ
3.     ፖል ኡመድ
4.     ኡመድ አዴል
5.     ኡጅሉ ባብ
6.     ኡባንግ ኪሩ
7.     ኡራንግ ኡቻን
8.     ኪሩ ኡመድ
9.     አካይ ኦፒዮ
10.   ዋና ሳጅን ኦኬሎ አዋኘንግ ኡሎንግ
11.     ኡመድ ኡኮቾ
12.    አዱኛ ኡማን
አንቀፅ 3 (1) (2) እና (4)

·         በፌ/ዓ/ህ/መ/ቁ 322/06

1.      ኡቺሚ አፐይ ኡቻላ
2.     ኡማን ኡድሉ ቻም
3.     ኡቻን ኡድላ ኦፒዮ
4.     ኡመድ ኡጁሉ ኡማን
5.     ኝበዲ ኡባንግ ኡጃቶ
6.     ኦፒዮ ቹር ኡባንግ
7.     ኡመድ ኡቶ ኡማን
8.     ኡፐዶካ ኡቱን ኝግየው
9.     ታደሰ ኡዱጊ ቲፋ
10.   ኡማን ኡካይ ኡኩችና
11.     ኦኬሎ ኡበር ኡቻን
አንቀፅ 3 (1፣ 2 እና 3)

·         የፌ/ዓ/ሕ/መ/ቁ/ 29/07

1.      ፒሊማን ኩዎት አግድ አዷቶ
2.     በኳች ማሞ ኡቶይ
3.     እኛንግ አጃልቡራ
4.     አዱሉ አኮላ
5.     አቶኦ ኡኮላ
6.     ኡጁራ አዋር
7.     ኡመድ ባች ኡዱኣ
8.     ፓቦች ኡመድ ኡባንግ
9.     ኡጁሉ ታታ ኡመድ
10.   ኡማን ኡጋላ ኡቻንግ
11.     ኡመድ አፒየው አኳይ
አንቀፅ 7 (1 እና 2)

‹የጋምቤላ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ› (ጋዴን) የተባለ ‹የሽብርተኛ ድርጅት› በማቋቋም በሚል ክስ፡

·         የፌ/አ/ህ/መ/ቁ 508/06

1.      ኦኬሎ አኳይ ኡቻላ
2.     ዴቪድ ኡጅሉ ኡባንግ
3.     ኡቻን ኦፒዮ ኡሞድ
4.     ኡማን ኝክየው ኡድሉ
5.     ኡጅሉ ቻሞ ኡኮይ
6.     ኦታካ ኡዋር ኡጋላና
7.     ኡባንግ ኡመድ አቦላ
አንቀፅ 4

የተለያዩ ‹የሽብርተኛ ድርጅቶችን› በማቋቋም በሀገር ውስጥ ‹የሽብርተኝነት ተግባር› ሊፈፅሙ ሲንቀሳቀሱ በሚል ክስ፡

·         በነውብሽት የክስ መዝገብ

1.      ውብሸት ታዬ  (ጋዜጠኛ)
2.     ርዕዮት ዓለሙ (ጋዜጠኛ)
3.     ዘሪሁን ገብረእግዚአብሔር
4.     ሒሩት ክፍሌ
5.     ኤልያስ ክፍሌ  (ጋዜጠኛ)

አንቀፅ 4 እና አንቀፅ 7 (1)·         /ዓ/ሕ/መ/ቁ 05/07

1.      ሶልያና ሽመልስ ገ/ማርያም (ጦማሪ)
2.     በፍቃዱ ኃይሉ ተጫኔ (ጦማሪ)
3.     ናትናኤል ፈለቀ አበራ (ጦማሪ)
4.     ማህሌት ፋንታሁን ተፈራ (ጦማሪ)
5.     አጥናፉ ብርሃኔ አያሌው (ጦማሪ)
6.     ዘላለም ክብረት በዛ (ጦማሪ)
7.     አቤል ዋበላ ሱጌቦ (ጦማሪ)
8.     አስማማው ኃ/ጊዮርጊስ ግዛው (ጋዜጠኛ)
9.     ኤዶም ካሳዬ ገላን (ጋዜጠኛ)
10.   ተስፋለም ወ/የስ ኤራጎ (ጋዜጠኛ)

አንቀፅ 3 (2) እና አንቀፅ 4


ማስታዎሻ፡

®    ዝርዝሩ ሙሉ አይደለም፡፡ ሌሎች ተጨማሪ ሰዎችም በፀረ-ሽብርተኝነት አዋጁ ተከሰው የተፈረደባቸው/በነፃ የተለቀቁ አሉ፡፡

®    በዝርዝሩ ውስጥ የተካተቱት ግለሰቦች በመደበኛ ችሎት የፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉ አንቀፆች ተጠቅሶባቸው የተከሰሱ ብቻ ናቸው፡፡ ነገር ግን በፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ዘርፍ የሚታሰሩ እስረኞች የጊዜ ቀጠሮ ፍርድ ቤት በሚቀርቡበት ወቅት የፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉ ተጠቅሶባቸው የሃያ ስምንት ቀናት ቀጠሮ ይሰጥባቸውና በመጨረሻ መደበኛ ክስ ሲከፈትባቸው አንቀፁ ከፀረ-ሽብርተኝነት አዋጁ ውጭ ሊሆን ይችላል - ለምሳሌ ስለላን ወይም የርስ በርስ ጦርነትን የሚመለከቱ የወንጀል ሕጉ አንቀፆች፡፡


®    በዝርዝሩ ውስጥ ከተካተቱት ሰዎች መካከል የተፈረደባቸው፣ ክሳቸውን ገና እየተከታተሉ ያሉ፣ በነፃ የተለቀቁ እና ክሳቸው የተቋረጠላቸው ግለሰቦች ይገኙበታል፡፡