Sunday, July 8, 2012

ጋዜጣና መጽሔቶቻችን ከሰኞ እስከ ሰኞ - አምስት

(ከሰኔ 25፣ 2004 እስከ ሐምሌ 1፣ 2004)

‹‹በኢትዮጵያ ሊትሩ 135ሺህ ብር የሚሸጥ ዘይት ሊመረት ነው›› የሚል ዜና ይዞ የወጣው መሰናዘሪያ ጋዜጣ ነው፡፡ ‹‹…ቴራ የተባለ የጀርመን ካምፓኒ [ባሕርዳር] ከነሐሴ ወር ጀምሮ ሊትሩ 7,500 ዶላር የሚሸጥ ዘይት እያመረተ ለውጭ ገበያ እንደሚያቀርብ አስታወቀ፡፡….››

** ** **
‹‹ዲግሪ ያላቸው ዜጎች የጎዳና ተዳዳሪዎች ሆነዋል››  የሚል አስደንጋጭ መርዶ ያስነበበው ሪፖርተር ጋዜጣ በረቡዕ እትሙ ነው፡፡ ‹‹ቁጥራቸው በውል የማይታወቁ የማስተርስና የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው ዜጎች አዲስ አበባ ውስጥ የጎዳና ላይ ተዳዳሪዎች ሆነው መገኘታቸው ተጠቆመ፡፡

‹‹የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ… የጎዳና ላይ ተዳዳሪዎች ወደ መልካም ሕይወት ለመመለስ፣ … በማድረግ ላይ ባለው እንቅስቃሴ መምህር፣ ነርሶችና በተለያዩ ሙያዎች የተመረቁ ዜጎች የጎዳና ላይ ተዳዳሪ ሆው መገኘታቸውን አረጋግጧል….››

** ** **

‹‹ይቅርታ›› የኢሕአዴግ ቃጭል? ወይስ… ያለው ተመስገን ደሳለኝ ፍትህ ጋዜጣ ላይ ነው፡፡ ‹‹…እነሆም ማሰር፣ ከአሰሩ በኋላ በይቅርታ መልቀቅ፣ ከለቀቁ በኋላ ደግሞ ይቅርታን አንስቶ መልሶ ማሰር…‹በይቅርታ ተቀባዩ አንገት ላይ ተንጠልጥሎ ቀሪ ዘመንን በሞላ ‹ኪሊ፣ ኪል…› የሚል ‹ቃጭል› ነው›…››


** ** **

አዲስጉዳይ መጽሔት ‹‹ኮንደሚኒም የማን ነው?›› በሚል ርዕስ፣ ነጋድራስ ጋዜጣም በበኩሉ ‹‹ኮንዶሚኒየሙ የማን ነው? የሚል ተመሳሳይ ርዕስ ያለው ሐተታ ይዘው ቀርበዋል፡፡ ነጋድራስ ኮንዶሚኒየም ዝቅተኛና መካለኛ ገቢ ያላቸው ነዋሪዎች ዕጣው ቢወጣላቸውም እንኳን የመጀመሪያውን ክፍያ ለመሸፈን ስለሚያከራዩት አይኖሩበትም ብሏል፤ አዲስጉዳይም ይህንኑ ሲያጠናክር ‹‹ቤቶቹን ባለቤቶቻቸው አያውቋቸውም›› ብሏል፡፡ አዲስጉዳይ ሐተታውን ሲደመድም ‹‹…ለመሆኑ ኮንደሚኒየም ቤቶች የተገነቡት ለማነው? ለነጋዴው? አነስተኛ ገቢ ላለው ህብረተሰብ? ለመንግስት ባለስልጣናት ወይስ ለሕዝብ?›› የሚሉ ጥያቄዎችን አንስቷል፡፡

** ** **

ከእሁዱ የሪፖርተር ትኩረት የሚስቡ ዜናዎች መካከል፣ ‹‹የንግድ ባንክ ጐተራ ቅርንጫፍ የዘረፋ ሙከራ ተደረገበት››‹‹የገቢዎችና ጉምሩክ ኦዲተሮች 100 ሺሕ ብር ጉቦ ሲቀበሉ ተያዙ›› እና ‹‹የመጀመሪያው የአየር ትራንስፖርት ረቂቅ ፖሊሲ ተዘጋጀ›› የሚሉ ይገኙበታል፡፡ ዝርዝሩን የተሰመረበትን የድረ ገጹን ትይይዝ ጠቅ በማድረግ/በመከተል ማግኘት ይቻላል፡፡

ሌላም፣ ሌላም
  • አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ ሂዩማ ራይትስ ዎችና የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መ/ቤት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና አነዱዓለም አራጌ እንዲፈቱ ጥሪ አቀረቡ - የኛ ፕሬስ
  • ‹‹ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጤና አስተማማኝ ባለመሆኑ የፓርላማው መርሃ ግብር ተራዘመ››
    ‹‹ይሄ የኢሳትና የእሳት ወሬ ነው›› - አቶ ሽመልስ ከማል (ፍኖተ ነፃነት)
  • መድረክን ወደ ግንባር ከፍ ለማድረግ ሥራ አስፈፃሚው እየመከረ ነው፤ በቀጣዩ ዓመት በሚካሄደው ምርጫ ለመሳተፍ ገና አልተወሰነም - ሰንደቅ
  • ሐዋሳ ከተማ ወደ ፌዴራል አስተዳደር አትገባም፤ በከተማዋ ግጭት ለማቀጣጠል ሕገ-ወጥ ወረቀት ተበትኗ - ሰንደቅ
  • ከፖለቲካ ወገንተኝነት ያልፀዳው የስፖርት ውድድር - ሪፖርተር (ረቡዕ)
    ‹‹…ጉዳዩን ጠለቅ ብለው የሚያውቁ ታዛቢዎች እንደሚሉት፣ በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ የስፖርት ማኅበር አመራሮች መካከል የለው ልዩነት ጎልቶ የወጣው በወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ምክንያት ቢሆንም፣ ከዚያ በፊት ሥልጣን በሌላቸው መሥራቾችና በአመራሮች መካከል ከባድ የሆነ የውስጥ ትግል ነበር፡፡ ዋናው ችግራቸውም ከገንዘብ ጋር የተያያዘ ነበር፡፡…››
  • ተስፋዬ ገብረአብ ከሚበጀው የሚፈጀው - አለማየሁ ገላጋይ (ፍትህ)
    ‹‹… ተስፋዬ ጅል አይደለም፡፡ ውጤቱን እየገመተ ብቻ ሳይሆን እያወቀ የሚያደርግ ለመሰሪነት የቀረበ ሰው ነው፡፡ …››
  • በእነአንዱዓለም አራጌ መዝገብ ነፃ የተባሉ በይግባኝ ተፈረደባቸው፤ ከ10 ዓመት እስከ ዕድሜ ልክ እስራት እንዲቀጡ ተበይኖባቸዋል - አዲስ አድማስ
  • አርቲስት ሙሉዓለም ታደሰ የኢትዮጵያ ሴት የምግብ ዋስትና ጀግኖች አምባሳደር ሆና ተመረጠች - ኢትዮቻናል
  • ‹‹…ፀጥ በማለትና በደህንነት መካከል ያለውን ቅራኔ ለማስታረቅና ለማመቻመች የሚደረገው ጥረት አዲስ ዓይነት የስነግጥም ዘይቤ ፈጥሯል፤ ይህ ስመ ጥሩውና ‹ሰምና ወርቅ› የሚባለው ዘይቤ ነው…›› ለፖኦትሪ ፐርነሰስ (በዕውቀቱ ስዩም) - ኢትዮቻናል
  • በጫት ላይ ኤክሳይዝ ታክስ የሚጥል ረቂቅ አዋጅ ወጣ፤ ለአገር ውስጥ ገበያ በሚቀርበው ጫት ላይ በኪ.ግ 5 ብር ቀረጥ ያስከፍላል - አዲስ አድማስ እና ሪፖርተር (እሁድ) ኮሎምቢያ ጫት ገበያውን እያነቃቃ ነው - Fortune

ርዕሰ አንቀጽ

No comments:

Post a Comment