ቤተል
ፋንታሁን የ25 ዓመት ወጣት ስትሆን፣ በኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ዘመን ተወልዳ ያደገች ነች፡፡ በሌላ አነጋገር አንዳንዶቹ ‘The
EPRDF Generation’ የሚሉት ትውልድ አባል ናት፡፡ ቤተል ብቻ ሳትሆን ስልሳ አምስት በመቶው የኢትዮጵያ ሕዝብ ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ.
ሥልጣን ከያዘበት ጊዜ ወዲህ የተወለዱ ሲሆን፣ ይሄም ከአገሪቱ አጠቃላይ ሕዝብ ሁለት ሦስተኛውን ይሸፍናል፡፡ ቤተል በዚህ ዕድሜዋ
“እውነተኛው የግንቦት 20 ፍሬ ግንቦት 7 ብቻ ነው፤ ሌላው ሁሉ ግንቦት 20 ቢኖርም ባይኖርም መኖሩ አይቀርም” ትለናለች፡፡ አንብቧት፡፡
የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ)ን በ6 ወራት ዕድሜ አንሰዋለሁ፤
ድንገት ቸኩሎ
ገብቶ ነው እንጂ ይደርስብኝ ነበር። እኔ ተረግዤ የጎተራው ሼል ይሁን ተቀጣጣይ ነገር (ግንቦት
27፣ 1983) ፈንድቶ ሕዝቤ ሸሽቶ እኛ ሰፈር መጣ አሉ፡፡ ታዲያ አንዳንዶች ሲያሾፉብን “የዛኔ ጥለውሽ ነው ያገኘንሽ ብለው ያወራሉ”፡፡ የኛን ሰፈር እወደዋለሁ፡፡ ግንቦት 20 ከሚባለው 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውጪ ኢሕአዴግ ለኛ ሰፈር ያደረገው ነገር የለም፡፡ ትምህርት
ቤቱም፣ ሰፈሩም በ97 ምርጫ ማግስት በተያዘብን ቂም ምክንያት ከ50 ዓመታት በላይ ያሳለፈ ሰፈር ባለፈው ዓመት ነው ‹ኮብልሰቶን› የገባበት፡፡ እንዲያውም ከአንዳንድ ሰዎች ጋር ተማክሬ UNESCO ላይ ለስመዘግበው ስል ለጥቂት ነው የቀደሙኝ። እሱ ይገርማችሁዋል፡፡ የቀድሞው የኢሕአዴግ ጠቅላይ ሚኒስትር ‹የመረሸ› ጊዜ እንኳን ብቸኛው ድንኳን ያልተጣለበት ሰፈር ነው፤ የኛ ሰፈር፡፡ ይሄን ሰማን ብለው ደግሞ የያኔውን ዛሬ እንዳይመጡ። “ኢትዮጵያ ውስጥ ነው ወይ?” ትሉኝ ይሆናል፡፡ አዎ እዚሁ
አዲስ አበባ፡፡
የግንቦት 20 ፍሬ፡ 1
ምርጫ ‘97, ‘02, ‘07
1997 - እንደዛኔ 18 ዓመቴ እንዲሆን የተመኘሁበት ጊዜ የለም:: የዛኔ የ8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ተፈታኝ ነበርኩ:: በላያችን ላይ የተኩስ እሩምታ ሲወርድ ‹አንፈተንም› ብለን ፈተናው ለ30 ደቂቃ ዘገየ። እንዲህ እንዲህ እያልን 1998 ላይ ሁለቴ ትምህርት ቤቱን አዘጋነው፡፡ በሁለተኛው በፌደራል ተገረፍን፡፡ ሰፈሬን የምወድበት አንዱ ምክንያት የሰፈሬ ልጆች ያኔ ‹ልጆቹን አናስነካም› ብለው ለፖሊሶቹ
መንገድ መዝጋታቸውን ሳስበው ነው፡፡ የዛኔ ቤት ሲፈተሽ ኮርኒስ አልቀራቸውም። ‹ወንድ አይትረፍ› የተባለ ይመስል የሰፈሬ
ወንዶች ሁሉ ተለቅመው እስር ቤት ገቡ። 2002 ሞራላችን ዝቅ አለ፤ አሽቆለቆለ ሁለት ጣት የልለ፣ አምስት ጣት የለ፡፡ 2007 መቶ ፐርሰንት በልሉን፡፡ ለነገሩ ምርጫ አልነበረም ማለት ነው እኮ፡፡ ፓርላማው ውስጥ ራሱ ምን እንደሚያደርጉ አላውቅም ልላችሁ ነበር፤ ግን ሳስታውሰው ለካስ ‹ቤርጎ› ሆኗል፡፡ ዕድሜ ለፌስቡክ ይሁን።
የግንቦት 20 ፍሬ፡ 2
“አንድ ፓርቲ ገዢ ሆኖ አገር ሲመራ ማድረግ ያለባቸው 10 ነጥቦች” ብዬ ለመዘርዘር አሰብኩና 10 ነጥቦችን ደረደርኩ ለካስ ብዙ ነገር ተደርጎልናል መንገድ፣ ኮንዶሚንየም (ሊያውም ምትሃተኛ)፣ ባቡር ከነመንገዱ:: ግን መንግሥት ይህን ካልሠራ ታዲያ ምን ሊያደርግ ነው? መቼም ከኔ ጋር ቁጭ ብሎ ‹ቃና› ቴሌቪዥንን አያይ። መንገድ ተሠራ እልልታ፡፡ ቤት ተሠራ እልልታ፡፡ ቆይ ልጠይቃችሁ አለቃ ወይ አስተማሪ አላችሁ እንበል፣ የሆነ ሥራ ተሰጣችሁ፣ ካልሠራችሁ ትባረራላችሁ፡፡ አለቀ በቃ፡፡ ኢሕአዴግም እንዳናባርረው ነው የሚሠራው እሱንም ሠራ ከተባለ (ሽርሽር እንሂድ ብለው ጓሮ እንደሚያዞሩት ሕፃን) የምር ለኛ አስቦ የሚመስለው ሰው ካለ እንተዋወቅ።
የግንቦት 20 ፍሬ፡ 3
ግንቦት 7። ወሳኝ ከምንላቸው የግንቦት 20 ፍሬዎች መሐል ግንቦት 7 አንዱ ነው፡፡ እውነት እውነት እላችኋለሁ ከላይ የጠቀስኳቸው ነገሮች
በሙሉ ግንቦት 20 ባይኖርም የሚኖሩ ናቸው፡፡ አያጠራጥርም አሁን ሳስበው ‹ግን› ለማለት ካልሆነ በቀር ‹ግ› የሚለውን ቃል ራሱ የምንጠቀምበት አይመስለኝም። በኢሕአዴግ ፓርላማ ግንቦት 7 አሸባሪ ተብሎ ከታወጀ በኋላ ብዙ ጓደኞቻችን ከሱ ጋር ግንኙነት አላችሁ ተብለው ተሰቃይተዋል፤ ወኅኒ ወርደወል፡፡ እኛም ከፖሊሶች ጋር አፍ ተካፍተናል። እንዲያውም ‹መቃወም› ለሚለው የአማርኛ መዝገበ ቃል ፍቺ ‹አሸበረ› ወይም ‹ግንቦት 7› ሊባል ነው የሚሉ ሁሉ አሉ። ‹አሉ› ነው እንግዲህ፤ ያየ የለም፣ ማስረጃ አምጡ እንዳትሉ።
የግንቦት 20 ፍሬ፡ 4
የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ… መቶ ጊዜ ሥሙን መጥራት ሰለቸኝ፡፡ አዋጁን ሳስብ አዋጅ ሳይሆን የግል ሐሳብ ይሆንብኛል። የፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉ የታወጀበት ዓላማ ለኔ ግልጽ አይደለም፡፡ የአዋጁ ሰለባ ከሆኑት ውስጥ አንዷ እህቴ ነች፤ ለስንት ዓመታት አብራኝ የኖረች እህቴን አይደለም አገር ልታምስ፣ እኔን ነክታኝ የማታውቅን ልጅ ‹አሸባሪ› ብሎ መፈረጅ (ለሁሉም የ‹አሸባሪ› ቤተሰቦች) ከባድ ነው። ምን አለ መሰላችሁ? ሌብነትን የማውቀው ሌባ ከሆንኩ ብቻ ነው፡፡ ሌባ እንዳይሰርቀኝ ብዬ ከተናካሽ ውሻ እስከ አደገኛ አጥር ድረስ ራሴን እከላከላለሁ። የፀረ ሽብርተኝነት ሕጉም ያው እንደተናካሽ ውሻ የምትፈልገው ሰው ሲመጣ ታስረዋለህ ወይ በተቃራኒው ታስነክስበታለህ።
ቀጣይ ስንት ግንቦት 20 እንደምናከብር ባላውቅም፤ እኔ ግን ስንትም ባናከብር ደስ ይለኛል፡፡ “ኢሕአዴግ ግን ‹ዴሞክራሲያዊ ነኝ› የሚል ከሆነ ለምን እኛ የመረጥነውን ቀን የድልና የነጻነት ቀን አድርጎ አያከብርልንም?” የሚል ነገር አሰብኩና ብዙም አልቀጠልኩበትም፡፡ እሺ ‹ዴሞክራሲያዊ ነኝ› ብሎ “የብዝኃነት…” ምናምን ብሎ ይጽፋል:: እኔስ ደስ ያለኝን በቀይ ቀለም ማሳለጫው ላይ ብጽፍ ምን አለበት? ምንም! ምናለበት ትውት ቢያደርገን? ውስጣችንን እርም እርም ባያሰኘው።
ማስታወሻ
You completed a number of fine points there.
ReplyDeleteI did a search on the subject and found mainly people will agree with your blog.
ReplyDeleteThank you for the good post.
ReplyDelete