Saturday, May 28, 2016

“በአንድ ስርዓት ሥር ይህን ያህል ጊዜ መቆየት እጅግ ያንገበግባል”

ወይንሸት ሞላ የ25 ዓመት ወጣት ስትሆን፤ በኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ ዘመን ተወልዳ አድጋለች፡፡ በሌላ አነጋገር ወይንሸት አንዳንዶቹ ‘The EPRDF Generation’ የሚሉት ትውልድ አባል ነች፡፡ ወይንሸት ብቻ ሳትሆን ስልሳ አምስት በመቶው የኢትዮጵያ ሕዝብ ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ ሥልጣን ከያዘበት ጊዜ ወዲህ የተወለደ ሲሆን፤ ይሄም ከአገሪቱ አጠቃላይ ሕዝብ ሁለት ሦስተኛውን ይሸፍናል፡፡ ወይንሸት በዚህ ዕድሜዋ በሥልጣን ላይ ያለውን ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግን በዜጎች ላይ ግፍ ሲፈጽም አይቼ ዝም ብዮ አልቀመጥም በማለት የፖለቲካ ትግሉን ተቀላቅላ ለዛም ብዙ ዋጋ እንደከፈለች/እየከፈለች እንዳለች በመግለጽ “‹ዴሞክራሲ በዚህ አምባገነን  ስርዓት ሰፍኖ፣ አገሬ እንደ አገር ሉዓላዊነቷ ተከብሮ፣ ሕዝቧ የተሻለ ኑሮ ካላቸው አገሮች ተርታ ተመድባ አያለሁ› የሚል ተስፋ የለኝም”  ትላለች፡፡ እነሆ አንብቧት፡፡

ዛሬ ግንቦት 20፣ 2008 የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕ.ወ.ሓ.ት.)/ወያኔ ሠራዊት በረሃ
የወለደውን ብሶት ይዞ ቤተ መንግሥት የገባበትና ሕ.ወ.ሓ.ት. መራሹ የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ.) መንግሥት ወደሥልጣን መንበሩ የወጣበት 25ኛ ዓመት የብር እዮቤልዩ ‹በዓል› ያከብራል፡፡ ይህ ‹የድል በዓል› በኢትዮጵያ ከሚከበሩት ሕዝባዊ በዓላት ዝርዝር ውስጥ የሚገኝ ቢሆንም፤ እንደኔ ‹በዓሉ› በምንም መመዘኛ ሕዝብ የማይስማማበት ሲሆን፤ ገዥዉ ቡድን ግን  በአንድ በኩል “ግንቦት 20 ዴሞክራሲ የተወለደበት ቀን” በሌላ በኩል ደግሞ “ደርግ የወደቀበት ቀን” እያለ የፕሮፓጋንዳ ማጣፈጫ አድርጎታል፡፡ እውነታው ግን ባሳለፍናቸው 25 ዓመታት በዘርና በጥቅም የሰከሩ የገዥው መንግሥት ምንደኞች እንደ ‹በዓል› ለማክበር ሲንደፋደፉ ከማየታችን ውጭ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደ ‹በዓል› ሳይሆን የባርነት ቀን የተከናነበበት አድርጎ የሚያየው ቀን እንደሆነ ይሰማኛል፡፡

ዕለቱን ገዥው ቡድን ሥልጣኑን ለማራዘም የሚጠቀምበት ‹የፕሮፓጋንዳ ጡሩንባ› ሲሆን ሕዝብ ደግሞ ገዥው ቡድን በሚከተላቸው የተበላሹ ፖሊሲዎች የተሠሩበትን በደሎችና ግፎች የሚያስታውስበትና እንደ አገር የተጋረጡበትን ችግሮች የሚያስብበት ነው፡፡ ለብዙ ሺሕ ዓመታት ታፍራና ተከብራ የኖረች ሀገራችን ሉዓላዊነቷ የተደፈረበትና  እንደ ሕዝብ  የደረሱብንን የዘር ጭፍጨፋዎች፤ አስከፊ በሆነው ድህነት፤ ስደት፤ ረኀብ፤ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና ለሰሚም በሚከብዱ የብዙኃን እንባዎች እንዲፈስ መነሻ የሆነ ዕለት በመሆኑ በምንም መመዘኛ የሕዝባዊ በዓል መሥፈርት የማያሟላ ቢሆንም በገዢው መንግሥት የፕሮፓጋንዳ ሚድያዎችና የሕዝብን ንብረት ያለከልካይ በሚያጠፉ ካድሬዎች ተከብሮ ይውላል፡፡

እኔ ተወልጀ ያደኩት በዘመነ ሕወሓት/ኢሕአዴግ ሲሆን፤ በሕይወቴም ከአንድ የፖለቲካ ሥርዓት ውጭም አላውቅም፡፡ ትምህርቴን የተማርኩት በዚህ ስርዓት የትምህርት ፖሊሲ ሲሆን፤ ለ‹አቅመ ፖለቲካ› ደርሼ ማሰብ በቻልኩበት ጊዜ ሁሉ ሕወሓት/ኢሕአዴግ ወጣትነቴን ነጥቆ ዜጎች እጅግ በጣም በሚያስደነግጥ የትምህርት ፖሊሲ በፍላጎታቸው እና በክኅሎታቸው ሳይሆን በዕጣ እንዲማሩ በተደረገበት የትምርት ፖሊሲ ትውልዱን ጉድጓድ ቆፍረው ሲቀብሩ እና በዚህ ውጤት በየዓረብ አገራት እህቶቼ የቁም ሞት መሞትና በየበረሀው ወድቆ መቅረት እና በሱስ መደንዘዝ እንዲሁም በአስከፊ ድህነት ውስጥ መኖር  የዚሀ ትውልድ ዕጣ ሆኗል፡፡ በአንፃሩ ከዚህ አስከፊ ስርዓት ለመውጣት የሚፍጨረጨሩ ወጣቶችን ደግሞ የአፈና ሕግ እያወጣ አፍኖ እና በጉልበት አንበርክኮ ይገዛል፣ በሌላ በኩል ደግሞ “ለዜጎች መሠረታዊ የፖለቲካ መብቶች ተከብረዋል” እያለ፤ በተቃራኒው የፖለቲካ ተቀናቃኞችን አሳዶ ያጠፋል፡፡ በሕገ መንግሥት ለይስሙላ በተደነገገው ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ሐሳባቸውን የገለጹ ጋዜጠኞችን በአሰቃቂ እስር ቤቶች አስሮ ያማቅቃል፤ በአሰቃቂ የምርመራ ዘዴ ያሰቃያል፤ ያሳድዳል፤ ይገድላል፤ ዜጎች ራሳቸውን በአሰቃቂ ሁኔታ እስኪያጠፉ ድርስ ተስፋቸውን ያጨልማል፡፡ ይህንንም ነባራዊ ሁኔታ በወጣትነት ዕድሜዬ ይህንን ትውልድ የቀበረ አስከፊ ስርዓት እንድታገል አስገድዶኛል፡፡

በሕይወት ዘመኔ በሕዝቡ ላይ የማየው አስከፊ እና ወደር የማይገኝለት የድህነት ደረጃ እንዲለወጥና ፍትሐዊ የሀብት ክፍፍል እንዲፈጠር ይህ ስርዓት መለወጥ ስላለበት በፖለቲካ ውስጥ እንድሳተፍ ትልቅ ምክንያት ሆኖኛል፡፡ የማየው የሕዝቡ ችግርና ብሶት በጣም ዘግናኝ ከመሆኑም በላይ፤ “ያለሁባት አገር መንግሥት ያለበት አገር ናት ወይ?” ብዬ እስከመጠየቅ አድርሶኛል፡፡

አሁን በኢትዮጵያ ላይ እየደረሰ ለሚገኘው እና በወቅቱ ለምገነዘባቸው ችግሮች መፍትሔ ለማግኘት በተለያዩ አጋጣሚዎች ለመጠየቅ የሞከርኩ እና በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የድርሻየን ለማበርከት እየተንቀሳቀሰኩ ሲሆን፤ ያየሁት አስከፊ እና ፈታኝ ጉዞ ግን በእሾህ ላይ የመራመድ ያክል እንደሆነ እና ገዥው ቡድን ‹ግንቦት 20ን አከብራለሁ› ከሚልበት ምክንያት በተቃራኒው እንደሆነ ነባራዊው ሁኔታ እንድገነዘብ አድርጎኛል፡፡ ይህ ክስተት ለአንድ ሁሉንም ማየት ለሚፈልግ ወጣት ቀርቶ ለማንም ቢሆን በአንድ ስርዓት ስር ይህን ያህል ጊዜ መቆየት እጅግ ያንገበግባል፡፡ ስሜት ያለው ሲሆን በእኔ እና በእኔ ትውልድ  ዘንድም ከፍተኛ ምሬት እና ቁጭት አያለሁ፡፡ ኢትዮጵያ ከጊዜ ወደ ጊዜ ዘርፈ ብዙ ወደ ሆነ ችግር የገባች ሲሆን ለዚህ ሁሉ ችግር መነሻ በሆነው ይህ ስርዓት ምንም ዓይነት ጭላንጭል ተስፋ የለኝም፡፡ “ዴሞክራሲ በዚህ አምባገነን  ስርዓት ሰፍኖ አገሬ እንደ አገር ሉዓላዊነቷ ተከብሮ፤ ሕዝቧ የተሻለ ኑሮ ካላቸው አገሮች ተርታ ተመድባ አያለሁ” የሚል ተስፋ የለኝም፡፡

አሁን በሥልጣን ላይ የሚገኘው ቡድን አያቶቼ ያስረከቡኝን አገር አሳጥቶኛል፡፡ ኢትዮጵያ በ21ኛው ክፍለ ዘመን በዘር ተከፋፍላ የምትገዛ የአምባገነኖች መፈንጫ ስትሆን ከ20 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ የተራበባት የዓለም ጭራ አገር ሆናለች፡፡ የአንድ አገር ኢኮኖሚ የባሕር በር የጀርባ አጥንት መሆኑን ከብዙ ሺሕ ዓመታት በፊት አባቶቻችን የተረዱትን ሐቅ ለመረዳት አቅም ወይም ፍላጎት የሌለው ገዥ ቡድን ታሪካዊ የወደብ ባለቤትነት መብታችንን እንደተራ ሸቀጥ ቆጥረው አራክሰውታል፡፡ “ከግመል መጠጫነት የተለየ ጥቅም አይሰጥም” ተብሎ የተቀለደበት ወደብ በዓመት ከስምንት መቶ ሚልዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ያስከፍለናል፡፡

የኔ ትውልድ ዛሬ ያለው ጭቆናና መከራ ብቻ አይደለም የሚያስጨንቀው፡፡ የኔ ትውልድ ፈተናው ከዚህም የከፋ ነው፡፡ ገዢው መንግሥት በሥልጣን ቆይታው በማይከፍለውና ብድር በተገኘ ገንዘብ የተሠራን አነስተኛ መሠረተ ልማት የገዥው ቡድን የኢኮኖሚ ፖሊሲ ስኬት ማሳያ አድርጎ ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ከማዋሉ በላይ፤ ከዓመት ዓመት ወለድ እየጨመረ የሚጠራቀም ዕዳን ለመጭው ትውልድ ሸክም አድርጎታል፡፡ ኢትዮጵያ ዛሬ ከዐሥራ አራት ቢልዮን የአማሪካ ዶላር በላይ ብድር ተሸካሚ ሆና በተዘዋዋሪ ‹ባርነት› ውስጥ ትገኛለች፡፡

ይህ አስከፊ ስርዓት ለዜጎች ሰብኣዊ መብት ክብር የማይሰጥና ዜጎች አገር እንደሌላቸው በየአገሩ ታርደው እና ወድቀው ሲቀሩ ኢትዮጵያዊነታቸውን በመካድ ሉዓላዊነታችንን  ያስደፈረ  ስርዓት ነው፡፡ ይህ አገዛዝ የፈጠረው የሙስናና  በግልጽ የሚታዩ ዘረፋዎችም የዚህችን አገር የቁልቁለት ጉዞ አመላካቾች ናቸው፡፡ አሁን የምናያት በአታላይ የውሸት ‹ፌደራሊዝም›፤ እንዲሁም ከሕግ አግባብ ውጭ በሆነ አካሔድ በሦስት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች የምትመራ አገር ስትሆን፤ ሥልጣን እና ሀብት ደግሞ በሕ.ወ.ሓ.ት. ስውር እጅ ውስጥ ይገኛል፡፡

ለዚህም ነው ለእኔ ግንቦት 20 ይህ የግፍ ስርዓት ወደ ሥልጣን ማማ የወጣበት ቀን በመሆኑ የሚታፈርበት እንጂ የሚከበር ቀን የማይሆነው፡፡

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!

4 comments:

 1. እናንተ የብድር የሚያስፈልገን ??

  ሰላም,

  የእኔ ስም Mr ፍሬድ ነው. እኔ የግል እና የኮርፖሬት ግለሰቦች ብድር መስጠት አንድ የግል አበዳሪ ነኝ. እናንተ ወደ ታች ዞር ብለዋል
  ብዙ ባንኮች? የእርስዎ ለማቋቋም ፋይናንስ ያስፈልገናል አድርግ
  የንግድ? ከእናንተ መስፋፋት የሚሆን የፋይናንስ ያስፈልገናል አድርግ
  የንግድ? ወይስ የግል ብድር የሚያስፈልገን ለምንድን ነው? የእኔ ብድር
  ክልሎች. የግል ከ የንግድ ብድር ነው. የእኔ ፍላጎት
  መጠን በጣም ያገናዘበ ነው. 3%, እና 50,000.00 € € 500,000,000,000.00 € ቢበዛ ቢያንስ, የእኛን የብድር ሂደት በጣም ፈጣን ነው
  እንዲሁም. እኔ ሁሉንም የገንዘብ ለማድረግ በጣም ፈቃደኛ ነኝ
  ባለፈው አንድ ነገር ያጠቃቸዋል. እናንተ በእርግጥ ዝግጁ ከሆነ
  የገንዘብ ችግር መፍትሔ እንዲያገኙ, ከዚያም ምንም ፍለጋ
  ተጨማሪ እና ብድር በዛሬው በኢሜይል በኩል ለ ተግባራዊ ይሆናሉ:
  (Fredlarryloanfirm@gmail.com). እኔ በማድረግ በጉጉት እንጠባበቃለን
  ከእናንተ ጋር የንግድ.

  አቶ ፍሬድ ላሪ
  ዋና ሥራ አስኪያጅ.

  ReplyDelete
 2. እናንተ የብድር የሚያስፈልገን ??

 3. እናንተ የብድር የሚያስፈልገን ??

 4. እናንተ የብድር የሚያስፈልገን ??