“አገሬ፣ አገራችን ኢትዮጵያ ነች። እንደ ኢትዮጵያዊ እንከራከራለን። ኢትዮጵያ
መኖር አለባት። ሁላችንም የኢትዮጵያ አባል መኾን አለብን ብዬ ነው የማስበው።”
“የኢትዮጵያ አንድነት እና ነፃነት፣ እኩልነት ከተጠበቀ፣ በተፈጥሮ ሃብት
የተደላደለች፣ በታሪኳ የገነነች፣ ኢትዮጵያ ሳትከፋፈል እና ሳትቆራረስ ለዘላለም እንድትኖር፣ የጎሳ ልዩነት ሳይደረግ በኢትዮጵያ
ውስጥ የተወለደ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ኢትዮጵያዊነት ግዴታው እና
መብቱም ነው ብዬ አምናለሁ፡፡”
- ጃገማ ኬሎ (የበጋው
መብረቅ ይናገራል)
“I am
so humbled and am forever grateful to our ancestors; no matter what mistakes
they committed, they resisted all the colonizing powers in a way that made them
create a history and logo that branded Ethiopia as the very idea of the
decolonizing imagination.”
የዞን ዘጠኝ
ጦማሪዎች [ኢ-መደበኛ] ቡድን አባል መሆኔ በዚህ ዓመት ከተከሰቱልኝ ምርጥ እውነታዎች ውስጥ በጣም ጠቃሚው ነው፡፡ ቡድናችን
‹‹የንባብ ፕሮግራም›› የተሰኘ በአንድ ርዕሰ ጉዳይ፣ አንድ ጽሑፍ ላይ ተመስርቶ በተወሰነ የጊዜ ዝላይ (Time
Interval) መወያየት ጀምሯል፡፡
ይህ ጽሑፍ
የዚህ ‹‹የንባብ ፕሮግራም›› ትሩፋት ነው፡፡ በእንዳልክ መራጭነት ‹‹Oromo
Narratives›› የዶ/ር ዶናልድ ሌቪን ጥናት ላይ ለመወያየት ተጠራርተን ተገናኘን፡፡ ርዕሰ ጉዳዩ የኦሮሞ ብሔረሰብ የፖለቲካ
ጥያቄዎችና አማራጭ መልሶች ላይ በጥቅሉ የሚያጠነጥን ነበር፡፡ በጉዳዩ ላይ የጠለቀ እውቀት ለሌለው ለእንደኔ ዓይነቱ ልብን በብርሃን
የሚያጥለቀልቅ (enlights) የንባብና የውይይት ፕሮግራም ነበር፡፡ ይህንን ሳያካፍሉ መቅረት ስስት ነውና፣ ባይሆን እየቆነጠርኩ
ላካፍላችሁ፡፡