Sunday, September 16, 2012

የሳምንቱ ጋዜጣና መጽሔቶች ከሰኞ እስከ ሰኞ




ሰንደቅ ጋዜጣ

ሰንደቅ ጋዜጣ በዚህ ሳምንት አትሙ 2004 . ጉልህ ክስተቶች የሚል የፌት ገጽ ይዞ ወጥቶዋል፡፡የአመቱ ዋና ዋና ክስተቶች ናቸው የተባሉት መካከልም የደርግ ባለስልጣናት መፈታት፣ኢትዮጵያ ለአሜሪካ ሰው አልባ ጄቶች ማኮብኮቢያ መፍቀዱዋ፣አወዛጋቢው 70/30 የበጎድራጎት ድርጅቶች ህግ የአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ መዘጋት እና የዳቦ ዋጋ ጭማሪ፣የአበራሽ ሃይላይ ጉዳይ እና የግብረሰዶማዊያኑ ስብሰባ በኢትዮጵያ ይገኙበታል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ዲያቆን ዳንኤል ክብረትን በእንግድነት ይዞ የመጣው ሰንደቅ ዳንኤልየሚያስጨንቀኝ ቀጣዩ ፓትሪያርክ ሳይሆን ቀጣይዋ ቤተክርስቲያን ናትማለቱን ጠቅሶዋል፡፡

አዲስጉዳይ መጽሔት

ባለፈው ሳምንት ለገበያ መብቃት ያልቻለችው አዲስ ጉዳይ መጽሔት በበኩልዋ የአመቱን አነጋጋሪ ጉዳይ ሞት በማድረግ በአመቱ በሞት የተለዩ ታላላቅ እና ታዋቂ ሰዎችን ይዛ ወጥታለች፡፡በዋና ዋና አምዶቹም
         የአዲስ ዓመት ገበያ
         ሞት የአመቱ አነጋጋሪ ጉዳይ
         መለስ ዜናዊ የአመቱ አብይ ጉዳይ
         2004 የኢትዮጵያ ፖለቲካ የተጠበቀው የቀረበት ያልተጠበቀው የመጣበት
         2004 ያልተቋጨው የህዝብ ብሶት (ከሊዝ አዋጅ እስከ ኑሮ ውድነት፣የሙስሊሙ ህብረተሰብ የመብት ጥያቄ) ሲሆኑ የተለመዱት ቋሚ አምደኞችም የተለያዩ ጽሁፎቻቸውን ይዘው ወጥዋል፡፡

አዲስ አድማስ

አዲስ አድማስ በቅዳሜ እትሙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ተቀዛዝዋል በሚል ዜና የፊት ገጽ ዜና ይዞ የወጣ ሲሆን ዶር ነጋሶ ጊዳዳን በፓርቲው ጋዜጣ ፍኖተ ነጻነት መታገድ እና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ አናግሮዋቸዋል፡፡አድማስ በተጨማሪም በፊት ገጽ ዜናው እና አህመዲን ጀማል /ቤቱን ይቅርታ ጠየቁ የሚል ዜና ይዞ ወጥቷል፡፡

የሙስሊም ማህበረሰብ ችግር መፍትሔ አፈላላጊ በተሰኘው ኮሚቴ ውስጥ ከሚገኙ 17 አባላት መካከል ስምንቱ በረመዳን ወቅት ከተከሰተው ግጭት ጋር ተያይዞ መታሰራቸውና መከሰሳቸው የሚታወቅ ሲሆን፤ ተከሳሾቹ ለእስልምና ጉዳዮች /ቤት የይቅርታ ደብዳቤ ማስገባታቸውን ምንጮች ጠቆሙ፡፡ የኮሚቴው አባላት ከምክር ቤቱ ጋር በነበራቸው ግጭት፤ የምክር ቤት ምርጫ ለረዥም ጊዜ ተቋርጦ መቆየቱን በመጥቀስ ምርጫ እንዲካሄድ መጠየቃቸው የሚታወስ ሲሆን፤ ምርጫው እንደሚካሄድ ከተወሰነ በኋላ ምርጫ የት ይካሄድ በሚለው ጥያቄ አለመግባባት መፈጠሩ ይታወቃል፡፡ ውዝግቡ መፍትሄ ሳያገኝ በረመዳን ወቅት ወደ ግጭት እንደተሸጋገረ የሚታወስ ሲሆን፤ ከኮሚቴው አባላት መካከል ስምንቱ ታስረው ክስ እንደቀረበባቸው ታውቋል፡፡ ተከሳሾቹ የሠራነው ስራ ስህተት በመሆኑ እንደገና በመወያየት ወደተሻለና አዲስ አሠራር እንድንመጣ እንፈልጋለን በማለት ለም/ቤቱ ደብዳቤ እንዳስገቡ የገለፁት ምንጮች፤ የተከሰሱበት ክስ ቀርቶ በይቅርታ ሊፈቱ ይችላሉ በማለት ግምታቸውን ገልፀዋል፡፡ የመጽሔት አዘጋጅ የሆነውን አህመዲን ጀማልን ጨምሮ በእስር በሚገኙት ስምንት አባላት ፊርማ ደብዳቤው ለምክር ቤቱ እንደደረሰም ምንጮቹ ተናግረዋል፡፡ በሌላ በኩል በቀረበባቸው ክስ /ቤት ለጥቅምት 2 ቀን 2005 . ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ብሏል አድማስ በዘገባው

አዲስ አድማስ ከዶ/ ነጋሶ ጋር ካደረገው ቃለ መጠይቁ በጥቂቱ

ጋዜጣችሁ አሁንም እንደታገደ ነው?

አዎ እንደታገደ ነው፡፡ ባለፈው አርብ ልዩ እትም ለማሳተም ሰዎች ልከን ክፍያ ለመፈፀም ስንል የብርሃንና ሠላም ማርኬቲንግ ሃላፊው ክፍያውን አልቀበልም አለ፡፡ ምክንያቱን ሲጠየቅ፤ በቁጥር 1 ልዩ እትማችሁ ያሳተማችሁት ነገር ቅሬታ ስላስነሳብንና የዚህን አይነት ጋዜጣ እንዴት ታወጣላችሁ ስለተባልን አናትምም ሲል መለሰ፡፡ ልዩ እትሙ የጠ/ሚኒስትሩን ሞት ተከትሎ የተፃፉ በርካታ ሃሳቦችን የያዘ ነበር፡፡ ከሃሳቦቹ መካከልምለፍርድ ሳይቀርቡ መሞታቸውየሚልና እኔ የፃፍኩትህገመንግስቱና /ሚኒስትሩየመሳሰሉ በርካታ በሳል ጽሑፎች አካትቷል፡፡

ሆኖም ግን ጋዜጣችሁን በተመለከተ በስልክ ቅሬታ ስለቀረበባችሁ፣ ማኔጅመንቱ ተወያይቶበት ጋዜጣው እንዳይታተም ወስነናል መባሉ ተነገረን፡፡ እኛም በማግስቱ ሃላፊ ለማነጋገር ሔድን፡፡ እኔ፣ አቶ ግርማ ሠይፉ እና አቶ አስራት ጣሴ ነበርን፡፡ ማርኬቲንግ ማናጀሩ ለኛም ያንኑ ደገመልን፡፡ ታዲያ ምን ይሻላል ብለን ስንጠይቀው ሃላፊዬን አነጋግሩ አለን፡፡ ዋናዋ ስላልነበረች ምክትሉ ቢሮ ገብተን ስናነጋግረው፣ ጋዜጣችን አይታተምም የተባለው ማርኬቲንግ ሃላፊው እንዳለው ሳይሆን በሌላ ምክንያት መሆኑን ሰማን፡፡እኛ አቅም የለንም ነው ያልነው፤ ለኦሮሚያ ክልል የትምህርት መጽሐፍትን ለማተም ጨረታ አሸንፈናል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ለብዙ ጊዜ ደንበኞች የሆኑ የተወሰኑ ጋዜጦች ስላሉ የእነሱን ብቻ እናትማለን እንጂ የናንተን ለማተም አቅም የለንም፡፡ ማኔጅመንቱ ተወያይቶ የደረሰበት ውሳኔ ይሄ ነው፤ እናንተ አዲስ ስለሆናችሁ የናንተን ላለማተም ወስነናልአለን፡፡ ይሄኔ በጣም ተናደድኩናበምን መስፈርት ነው የእኛን አናትምም ብላችሁ የሌሎችን የምታትሙት?” ብዬ ጠየቅሁት፡፡እነሱ የቆዩ ደንበኞች ስለሆኑ ነው፤ የፈለጋችሁትን ነገር አድርጉ፤ አናትምምብሎ ድርቅ አለብን፡፡ ሆኖም እኛ በደረሰን መረጃ መሠረት፤ እዚያ ማተምያ ቤት አንድ ሰው አለ፤ ጋዜጣው ሲመጣ ምን አይነት ይዘት እንዳለው ለደህንነቱ ሃላፊዎች ደውሎ የሚጠቁም፡፡ ከዛ ጉዳዩ የመንግስት ኮሙኒኬሽን /ቤት ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት አቶ ሽመልስ ከማል ጋር ይደርሳል፤ አቶ ሽመልስ ደግሞ ለም/ሥራ አስኪያጁ ደውሎ እንዳይታተም ያዛል፡፡ እንደዚያ ነው የሆነው፡፡ ይሄ ማለት ደግሞ ከዚህ በፊት እንደነበረው ዓይነት የአፈናና የዲሞክራሲ መብቶች እረገጣ ነው፡፡ በመንግስት ላይ ተቃዋሚ አስተያየትና ሃሳብ የሚሰነዝሩ ግለሰቦችንና የህትመት ውጤቶችን ልሳን መዝጋት ነው፡:

የጋዜጣችንን ሥርጭት 2500 ኮፒ ጀምረን ነበር 20ሺህ ኮፒ ያደረስነው፡፡ ግን ታገደ፡፡ ብርሃንና ሰላም አላትምም ሲለን እሱን ትተን ወደ ግል ማተምያ ድርጅቶች ሄደን ነበር፡፡ አንዳንዱ አቅም የለንም ይላል፤ ሌላው ደግሞ ለማተም ይቸግረናል ይለናል፡፡ ቦሌ ማተሚያ ሆራይዘን፣ ቅድስት ማርያም ማተምያ ቤቶች ሄደናል፤ ግን ለማሳተም አልቻልንም፡፡

ከጋዜጣውን መዘጋት ጋር ተያይዞ ፓርቲው ሰላማዊ ሠልፍ እንደሚጠራ ገልጿል፡፡ የሠልፍ ፈቃድ ባታገኙም በሌላ መንገድ በመጥራት እናካሂዳለን ብላችኋል፡፡ እንዴት ነው ያሰባችሁት?

በመጀመሪያ የምናደርገው ብርሃንና ሠላም ማተሚያ ድርጅት አላትምም ያለበትን ምክንያት በጽሑፍ እንዲገልጽልን ሲሆን ከዚያ በፊት ግን እንደገና አስቦበት እንዲያትምልን ደብዳቤ ልከናል፡፡ የመንግስትና የህዝብ ተቋም ስለሆነ መንግስትም ሃላፊነት አለበት፡፡ /ጠቅላይ ሚኒስትሩም በጉዳዩ ላይ እርምጃ እንዲወስዱ ደብዳቤ ጽፈናል፡፡ በተጨማሪ እኔ በራሴ የቦርዱ ሊቀመንበር / ብስራት ጋሻው ጠና ጋር ደውዬ ልነግራቸው ሞክሬ ነበር፤ ሆኖም አሁን እሳቸው የብአዴን ሃላፊ ስለሆኑ ባህርዳር ናቸው፡፡ ጉዳዩን አላውቀውም፤ አጣርቼ መልስ እሠጣለሁ ብለውኛል፡፡ ያንን እየጠበቅሁ ነው፡፡ ስለዚህ ዝም ብለን አንቀመጥም፡፡ ከዛ በኋላ ነው ሠላማዊ ሠልፉን የምንጠራው፡፡ የሚያስፈልገውን ሁሉ እርምጃ እንወስዳለን፡፡ የታገደውን ጋዜጣ ለማስጀመር እስከመጨረሻው እንታገላለን፡፡

አዲሱ /ሚኒስትር ቢሆኑ ብለው የሚያስቡት ወይም የሚመርጡት ሰው አለ?
ተመርጫለሁ የሚለው ኢህአዴግ ነው፤ ከዛ አንፃር የአገሪቱን ችግሮች ጠንቅቆ የሚያውቅና የሚፈታ ሰው ቢሾም ነው የሚሻለው፡፡ ለዚህ ደግሞ ብቃት አላቸው ብዬ የማስባቸውና ድሮ ከማውቃቸው መካከል … (ስልጣን ከለቀቅሁ 11 አመታት ሊሆነኝ ነው) አቶ ግርማ ብሩ ቢሆኑ ብዬ 1993 . ሃሳብ አቅርቤ ነበር፡፡ አሁን እድሜም ጨምሯል፤ ሆኖም እሱ ቢሆን ችሎታ አለው ብዬ አምናለሁ፡፡ ከህወሓት ብርሃኔ /ክርስቶስ ቢሆን እላለሁ እድሜው ባይገፋ ኖሮ ስዩም መስፍንም ጐበዝ ነው፡፡ ከብአዴን ደግሞ አቶ አዲሱ ለገሠ፡፡ በእርግጥ እነዚህ ሰዎች አርጅተዋል፤ መተካት አለባቸው፡፡ አዲሶቹን ወጣቶች ሊያደርጓቸው ይችሉ እንደሆነ አላውቅም፡፡ እኔ የምሻው ግን የስርአት ለውጥ መጥቶ ህዝቡ በዲሞክራሲያዊ መንገድ ይመራኛል የሚለውን ቢመርጥ ነው፡፡
የእግርዎ የጤንነት ሁኔታ እንዴት ነው?

አሁን በጣም ጤነኛ ነኝ፡፡ የእግሬን ጉዳይ በተመለከተየስኳር በሽታ አለብኝ፡፡ በሰውነቴ ውስጥ የተከማቸ ኮሌስትሮል አለ፡፡ ለብዙ አመታት ደግሞ ሲጋራ አጨስ ነበር፤ እነዚህ ነገሮች የእግር የደም ስርን የመዝጋት ሁኔታ ፈጥረው ነበር - በሁለት እግሮቼ ላይ፡ እረጅም መንገድ መሄድ አልችልም ነበር፡፡ ስለዚህ ሳልታከም ብቆይ ኖሮ አደገኛ ችግር ማስከተሉ አይቀርም ነበር፡፡ አሁን የተዘጋውን የደም ሥር ከፍተውልኛል፡፡ በሙሉ ጤንነት ላይ ነኝ፡ አንዳንድ ሚዲያዎች አጋነውት ነው እንጂ እግሬ መቆረጥ ደረጃ ላይ አልደረሰም፡፡

ዕንቁ መጽሔት

የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስትር የአቶ መለስ ዜናዊን ፎቶ በፊት ገጹ ይዞ የወጣው እንቁ መጽሔት እንደሌሎቹ ሁሉ የተለያዩ የአመቱን ክስተቶች እና የእንቁን እትሞችን ማጠቃለያ ይዛ ወጥታለች፡፡ዋና ዋና ጽሁፎቹም
         ሰላም ወይስ ሁከት - ምርጫችን
         መለስ የጀመረው ህልም ህያው ይሁን - በያሬድ ጥበቡ
         መለስ ዜናዊ እና ያላለቀው የኢትዮጵያ ዘመናዊነት ፕሮጄክት - በፕሮፌሰር መሳይ ከበደ
         የመለስ ሞት እንቆቅልሾች እና ምቹ ጊዜያት- በፕሮፌሰር ቴወድሮስ ኪሮስ

አዲሱ ዓመትን አስመልክቶ በእንቁ ለተነሱ ጥያቄዎች የተሰጡ መልሶች

  1. ትዳር ሳይኖር ልጅ አይኖርም ስለዚህ ትዳር መቅደም አለበት እላለሁ - / ሃይሉ ሻወል ከእውቀት ከስልጣን ከሃብት ከትዳር እና ከልጅ የቱን ያስቀድማሉ ተብሎ ከእንቁ ለቀረበላቸው ጥያቄ የሰጡት መልስ
  2. የትራፊክ አደጋ መጨመሩ መጥፎ ነው፡፡ሌላው የክቡር /ሚር መለስ ዜናዊ መሞት በጣም አስከፊ እና አስደንጋጭ ነው፡፡በርካታ መንገዶች ተሰርተዋል ይህ ደግሞ በጣም ጥሩ ነገር ነው፡፡ - ዋና ሳጅን አሰፋ መዝገቡ ስለአለፈው ዓመት መጥፎ እና ጥሩ ጉዳዮች ከእንቁ ለተጠየቁት ጥያቄ የሰጡት መልስ
  3. ለአገሬ በአዲሱ ዓመት የምመኘው ያለ አንድ ጥይት ተኩስ ማንኛውም የመንግስት ለውጥ በሰላማዊ መልኩ እንካሄድ እና ዴምክራሲያዊ በሆነ መንገድ እንዲከናወን ነው፡፡ ማንኛውም ሽግግር በዴሞክራሲያዊ መልክ የሚከናወን ከሆነ መጪው ትውልድ ቢያንስ ከዚህ የሚወርሰው እዳ አይኖርም፡፡ - ደራሲ አያልነህ ሙላት በአዲሱ ዓመት በአገርዎ ምን ቢደረግ መልካም ይሆናል ይላሉ ለሚለው የእንቁ ጥያቄ የሰጡት መልስ

ሌሎችም

         የመጀመሪያዋ የሴት ጄኔራል ተሾሙ - ሪፓርተር ጋዜጣ
         በአዲሱ ዓመት ሁላችንም ከባድ የቤት ስራ አለብን - / ኤፍሬም ይስሃቅ የሃገር ሽማግሌዎች ህብረት ሊቀመንበር ለአዲስ ጉዳይ መጽሔት
         ከመንግስት ሆደ ሰፊነት ይጠበቃል-አቶ ተመስገን ዘውዴ አንድነት ፓርቲ የውጪ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ አባል - ለአዲስ ጉዳይ መጽሔት
         ሼህ አላሙዲን ተመራቂዎች ተማሪዎች ባገኙት የስራ መስክ አገራቸውን እንዲያገለግሉ መከሩ -  ሰንደቅ ጋዜጣ

ርዕሰ አንቀጾች

         በአዲስ ዓመት አዲስ መንግስት - ዕንቁ መጽሔት
         ፍቅሬ ፍቅሬ አይብዛ - አዲስ ጉዳይ መጽሔት
         አዲሱ ዓመት ጉድለቶቻችንን የምንሞላበት ዓመት ይሁንልን - ሰንደቅ ጋዜጣ
         የሚታመን ውሸት ለመዋሸት ከፈለግህ፤ የማይታመን እውነት አትናገር” - የጃፓኖች አባባልእያንዳንዷ ሩዝ ላይ የሚ በላት ሰው ስም ተፅፏል!” - የህንዶች አባባል - አዲስ አድማስ ጋዜጣ
         ጉዞአችን የመቀጠል ብቻ ሳይሆን የመጨመርም ይሁን - ሪፓርተር ጋዜጣ

No comments:

Post a Comment