Tuesday, June 19, 2012

የኢትዮጵያ ጦማሮች ምን ፃፉ?




(ከሰኔ 6 እስከ ሰኔ 13)

‹‹እነአልበርት አንስታይን ስለዘንድሮው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ምን ይላሉ?››በማለት በ‹የበፍቄ ዓለም› ላይ ይህን ፅሁፍ ጀባ ያለን በፍቃዱ ዘሀይሉ ነው፡፡ በዚህ ጽሁፉ ላይ የዓለም ሶስት ታላላቅ ሰዎችን እይታ ከአገራችን ነባራዊ የፖለቲካ አስተሳሰብ ጋር አነጻጽሮልናል፡፡

በአልበርት አንስታይን ታዋቂ አባባል “The world will not be destroyed by those who do evil, but by those who watch them without doing anything.” (ዓለማችን የምትጠፋው ክፉ በሚያደርጉ ሰዎች ሳይሆን ክፉ ሲያደርጉ እያዩ ዝም በሚሏቸው ሰዎች ነው፡፡) የጀመረው ይህ ፅሁፍ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ችግር አይተው እነዳላዮ አላፊዎችን እነዲህ ሸንቆጥ አድርጓቸዋል፡፡

‹‹በኢትዮጵያ የፖለቲካ እውነታ በየጓዳው ከመንሾካሾክ እና ከመብሸቅ ባሻገር ይሄ መንግስት (ይሄ ገዢ) ያለ እኛ ተገዢነት እና ፈቃደኝነት ሊጨቁነን እንደማይችል ገብቶን የተነጠቅነውን ነፃነት ለማስመለስ የምንሞክር እጅግ ጥቂቶች ነን፡፡ በተለይም ‹‹ኢኮኖሚያዊ ዕድገቱ ብዙሐኑን ስላላማከለ አንድ ቀን አገሪቱ ወደማትወጣው ችግር ውስጥ ትገባለች፣ ወዘተ. ወዘተ...›› እያሉ የጋን ውስጥ ትንታኔያቸውን የሚሰጡት ነገር ግን ለጋዜጣ እንኳን ማብራሪያ ለመስጠት ‹‹ስሜ ከተጠቀሰ አይሆንም›› የሚሉ ምሁራን ከአጥፊው ገዢው ፓርቲ ይልቅ - ለጥፋቱ ተጠያቂ መሆናቸው አይቀሬ ነው፡፡››ቀሪውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ፡፡

ተስፋዬ ገ/አብ የቅዳሜ ማስታወሻ በሚለው ጦማር በዕለተ ሰኞ ባኖረው ፅሁፍ አነጋጋሪው ‹ሰውለሰው› ድራማ መጠናቀቅን ተከትሎ የተዋናዮቹን ገጸባህሪ ወደ ነባራዊው አለም ቀይሮታል፡፡

አስናቀ አሸብርን እንደ‹ህወሃት ወኪል›

ማህሌትን እንደ ‹ኢትዮጵያ›

መስፍንን እንደ ‹ፕሮፌሰርመስፍን›

የመስፍንና የማህሌት ሁለት ልጆች እንደ ‹የኢትዮጵያ ህዝብ ወኪሎች›

ልኡል (የአስናቀን ወንድ ልጅ) እንደ ‹ከህወሃት የታወገዱት የህወሃት አመራር አባላት ወኪል›

ተስፋዬ በድራማው ከፍተኛ ትኩረት ያገኘውን አስናቀ የተባለው ገጸባህሪ ከህወሃት አሰራር ጋር እንዲህ አነጻጽሮታል፡፡

      ‹‹የወያኔ ድርጅታዊ አሰራሮች በድራማው በብዙ ቦታ ተጋልጠዋል። ለአብነት ማህሌት ህገወጥ ተግባር እንድትፈፅም ያደረጋት ራሱ አስናቀ ነበር። መልሶ ግን ማስረጃውን ለግል ጥቅሙ በማዋል ማህሌት እንድትንበረከክለት ለማድረግ ሲሞክር ይታያል። ወያኔ እነአባዱላን ወንጀል እንዲሰሩ ካደረገ በሁዋላ መልሶ እንደፈለገ የሚጠቀምባቸው በዚሁ መንገድ ነበር። እንደ ማህሌት በየዋህነት የፈፀሙት ወንጀል እንዳይጋለጥባቸው ሲሉ፣ ለህወሃት እየሰገዱ ለመኖር የተገደዱ በርካታ ባለስልጣናትን አውቃለሁ። ቀሪውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ፡፡

በየጊዜው ሽሙጦችን ጀባ የሚለን አቤቶክቻው) በስማቸው መጨረሻ ‹‹ዬ››ን እየጨመረ እያቆላመጠ የሚጠራራቸው አቶ መለስ ለቡድን ሀያ አገራት ስብሰባ ወደ ሜክሲኮ በሄዱ ጊዜ ከብዙ ጊዜ በኋላ እንዳያቸውና እንደናፈቃቸው እንደ ድሮ ጎረቤት ቢሆኑ ኖሮ በቴሌቪዥን መስኮት ሲጠፉበት በሳሎናቸው መስኮት ለማየት ሙከራ እንደሚያደርግና ዛሬ ግን ተራርቀው ናፍቆታቸው ሲያስጨንቀው እንደሰነበተ ባያቸው ጊዜም መክሳታቸው እንዳሳሰበው ‹‹ጠቅላይ ሚኒስትርዬ ከሱብኝ!››ባለው ጽሁፍ ምክር ቢጤም ጣል አርጎላቸዋል፡፡

‹‹ምን ሆኑ!? እንዴ ጠንከር ይበሉ እንጂ ጠቅላይ ሚኒስትርዬ! ቀጣዩ ጩኸት እኮ እየባሰነው የሚመጣው! ታድያ ጠንከር ጠንከር ማለት አይሻልም ይላሉ? ቁጣ እና ጩኸት ይህንን ያህል የሚረብሽዎት ከሆነ ግን ዘዴውን ልንገርዎት…!? እሺ አይሉኝም እንጂ ዛሬውኑ ስልጣንዎን ልቅቅ አድርገው አዲስ አገራዊ መግባባት፣ አዲስ አገራዊ ምርጫ ማከናወን! አቤት ያኔ ጤናዎ ላይ ራሱ ምን አይነት መሻሻል አንደሚመጣ ያዩት ነበር››በማለት ተቆርቋሪነቱን አሳይቷል፡፡

በመቀጠልም ከዚህ ቀደም በአዲስ አድማስ በወጣ ፅሁፍ አበበ ገላው ዋሽንግተን ዲሲያል ሄደው በርካታ የኢህአዴግ ደጋፊዎች ስላሉ እነርሱን ፈርቶ ነው!” ብላችሁን ነበረ። ሰውየው እኮ አንገታቸውን የደፉት በዋሽንግተን ዲሲ ነው። በማለት ‹‹ምን አይነት አዲስ አድማሰ መጣ ደግሞ ባካችሁ!?›› ሲል ጥያቄ ጥሎ አልፋል፡፡ ቀሪውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ፡፡

ከአቤ ወግ ሳንወጣ የኢሃዴግን ባለስልጣን የሆኑት አቶ በረከት ከአረብሳት ባለስልጣናት ጋር ባደረጉት ውይይት የኤርትራ ቴሌቪዥን ከፈለገ ይግባ በኢሳት ጉዳይ ግን አንደራደርም! ”ባሉት ንግግራቸው አቶ በረከትን ኢሳትን ትተው ለኤርትራ መፍቀዳቸው ወገንተኝነታቸውን እንዲሁም ‹‹ለአባይ መገደብያ ብለን በምናዋጣው ገንዘብ ራሳችንን እና እነኢሳትን መገደቡን ቀጥሎበታል።በዚህ አይነት ሁኔታ ነውለቀጣይ አርባ አመት ለመኖር ያቀድነው…? አረ ይደብራል!?.............

ተዉብሶቲቱ ዛሬም ታረግዛለች።

ተዉብሶቲቱ ዛሬም ትወልዳለች።

ተዉዛሬም ጀግና ይፈጠራል

ተዉዛሬም ንጉስ ይከሰሳል

ተዉኋላ ማጣፊያው ይቸግራል

ተዉምክር መስማት ይሻላል።

ተዉተዉተዉዉዉዉ…!

እያለ በዜማ አለቃቅሷል፡፡ ቀሪውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ፡፡መልካም ሽሙጥ!

            ጉዳያችን የተኘው ጦማር ‹‹የአምባ ገነንነት ዲግሪው ስንት ነው?›› በተሰኘው ጽሁፍ ውስጥ ‹‹አንባገነንነት ምንድን ነው?›› ለሚለው ጥያቄ ዊኪፒድያን ጠቅሶ ይህን ፍቺ ይሰጣል፡፡ ‹‹ አንድ ሰው ወይንም የተወሰኑ ቡድሮች ፈላጭ ቆራጭ አስተዳደር፤ በዘመናዊ ትርጉም ደግሞ ለህገመንግስት፣ለ ማህበረሰባዊ ህጎች ሁሉ የማይገዛ የመንግስት አስተዳደር›› ነው ይለዋል፡፡ በመቀጠልም የአምባገነኖችን አመራር ዘይቤ አንድ እርምጃ ወደፊት ሶስት እርሚጃ ወደኋላ ይለዋል፡፡ ‹‹ አምባገነን ስርዓት ስር የሚተዳደር ሃገር መንገድ ይሰራ ይሆናል ነገር ግን በመንገዱ ላይ የሚሔደው በፍርሃት የተሸበበ እና የተከዘ ህዝብ ነው፤


      በ አምባገነን ስርዓት ስር የሚተዳደር ሃገር ዩንቨርሲቲ ይከፍት ይሆናል:: ነገር ግን ስለምን መመራመር፤ ስለምን ማውራት፤ወዘተ እንዳለባቸው የሚነገራቸው ብቻ ሳይሆኑ የቱን ማንበብ ፤የቱን አለማንበብ፤ እንደሚገባቸው የተወሰነላቸው ምሁራን የሞሉበት ተቋም ይሆናል፤ ›› ቀሪውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ፡፡

ሰሞኑን የመነጋገሪያ ርዕስ ስለሆነው የቴልኮም አዋጅ እንዳልክ እነዲህ ጦምሯል፡፡ሙሉ ጽሁፉን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ፡፡

የዳንኤል ክብረት ጦማር <<…….ሰው ከእንስሳት ከሚለይበት ነገሮች አንዱ ይኼው ነው፡፡ ለምድራዊ ህልውናው ብቻ ሳይሆን ለሌላውም ህልውናው ይጨነቃል፤ ያስባል፡፡ ሲኖርም ለእነዚያም ጭምር ይኖራል፡፡ እንስሳት በምድር ላይ ስላላቸው ኑሮ እንኳን አያስቡበትም፡፡ በደመ ነፍስ ይኖሩበታል እንጂ፡፡ ከዚያም አልፈው ሌላ ዓይነት አነዋወር የላቸውም፡፡ ትናንት የሚሉት ታሪክ፣ ነገ የሚሉት ተስፋ የላቸውም፡፡ ህልውናቸውን ሰው እንጂ ራሳቸው አይወስኑትም፡፡ ስለዚህም ብቻቸውን ሊመሰገኑም ሆነ ሊወቀሱ አይችሉም፡፡……>>ሙሉ ጽሁፉን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ፡፡

No comments:

Post a Comment