ሰሞኑን በኢንተርኔት ተጠቃሚ ዘንድ እያወዛገበ ያለው የቴሌኮም አዋጅ አቶ ሽመልስ ከማል በቴሌቭዥን መስኮት ብቅ ብለው ስካይፒን መጠቀም ይቻላል ካሉ በሗላ ጋብ ብሎ ቢቆይም አቶ በረከት ሰጡት በተባለው መግለጫ ደግሞ ስካይፒን እንዘጋለን ወይም “ስካይፕም ሆነ ሌሎች የቴሌን ገቢ የሚቀንሱ እና ለደህንነት ስጋት የሚሆኑ የኢንተርኔት አገልግሎቶችን እንዘጋለን” የሚል ግራ የሚያጋባ ንግግር በትነዋል፡፡
Thursday, June 28, 2012
የኢትዮጵያ ጦማሮች ምን ጻፉ?
ሰሞኑን በኢንተርኔት ተጠቃሚ ዘንድ እያወዛገበ ያለው የቴሌኮም አዋጅ አቶ ሽመልስ ከማል በቴሌቭዥን መስኮት ብቅ ብለው ስካይፒን መጠቀም ይቻላል ካሉ በሗላ ጋብ ብሎ ቢቆይም አቶ በረከት ሰጡት በተባለው መግለጫ ደግሞ ስካይፒን እንዘጋለን ወይም “ስካይፕም ሆነ ሌሎች የቴሌን ገቢ የሚቀንሱ እና ለደህንነት ስጋት የሚሆኑ የኢንተርኔት አገልግሎቶችን እንዘጋለን” የሚል ግራ የሚያጋባ ንግግር በትነዋል፡፡
Sunday, June 24, 2012
ጋዜጣ እና መጽሄቶቻችን ከሰኞ እስከ ሰኞ - ሦስት
የተመሰረተበትን አንደኛ ዓመት በልዩ ዝግጅት ለማክበር ደፋ ቀና እያለ ያለው ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ አንድነት ለፍትሕና ለዴሞክራሲ በዓይነቱ የተለየ ‹‹የንድፈ ሐሳብና የፖሊሲ ትንተና መጽሄት›› ሊያሳትም እንደሆነ የሚነግር ዜና ይዞ ወጥቷል፡፡ ‹‹.. በዓይነቱ የተለየ የንድፈ ሐሳብና የአማራጭ ትንተና የሚቀርብበት መጽሄት ለማሳተም ዝግጅት መጨረሱን አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ ለዝግጅት ክፍላችን አስታወቀ፡፡ ‹ዳንዲ› የሚል ስያሜ የተሰጣት መጽሄቷ ሙሉ ለሙሉ የንድፈ ሐሳቦችና አማራጭ የፖሊሲ መነሻ የሚሆኑ ሐሳቦች የሚተነተኑባት መሆኗ ተነግሯል፡፡
* * *
‹‹የመንግስት ገንዘብ ለሚያባክኑ መ/ቤቶች ከፍተኛ በጀት ተመደበ›› ያለው ደግሞ የኛ ፕሬስ ጋዜጣ ነው፡፡ ‹‹ከፍተኛ የመንግስት ገንዘብ ባለማወራረድ ዋና ኦዲተር ለመሰከረባቸው መስሪያ ቤቶች ከበፊቱ የበለጠ ከፍተኛ በጀት እንደተመደበላቸው ተጠቆመ፡፡›› ካለ በኋላ ባለፈው ዓመት 1.2 ቢሊዮን ብር ያባከኑትን መ/ቤቶች ሲዘረዝር ‹‹… መከላከያ ሚኒስቴር፣ የግብርና ቴክኒክና ሙያ ስልጠና፣ የመቀሌ ዩንቨርሲቲ፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ፣ የመቀሌ ጤና ሳይንስ፣ የአይደር ሪፈራል ሆስፒታል፣ የትምህርት ሚኒስቴር፣ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ፣ የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የመንግስትን ገንዘብ ያለበቂ ማስረጃ ወጪ በማድረግና ሳያወራርዱ በመቅረት በዋና ኦዲተር ጥቁር መዝገብ ውስጥ እንደገቡ አረጋግጧል፡፡›› በተመሳሳይ ዜና ፍኖተ ነፃነትም የመጪው ዓመትን በጀት ‹‹ለአፈና የሚውል በጀት›› ሲል ወርፎታል፡፡
* * *
‹‹የየመኑ ፕሬዘዳንት ሳላህ አዲስ አበባ መሽገዋል?›› የሚል መካከለኛ ሐተታ ይዞ የወጣው መሰናዘሪያ ‹‹…የብዙዎች ግምት ሳላህ ከእይታ የተሰወሩት ለደህንነታቸው በተፈጠረው ስጋት ሳይሆን ቀደም ሲል ስልጣን ላይ እያሉ ለሕዝባቸው እኔ በፊት በየቀኑ ጫት እቅም ነበር፡፡ አሁን የምቅመው በሳምንት አንድ ጊዜ ነው ስለዚህ እናንተም የእኔን አርአያ ተከተሉ በማለት ያስተላለፉትን መልዕክት መነሻ በማድረግ በኢትዮጵያ መሽገው ሱሳቸውን እያወራረዱ ነው ወይም ከሕዝብ በዘረፉት ገንዘብ አዲስ አበባ እየተመላለሱ ሱሳቸውና ፍላጎታቸውን እያጣጠሙ እንደሆነ የሚገልፅ ነው፡፡…››
* * *
ሪፖርተር ጋዜጣ ‹‹ዳኞች የፍርድ ቤት ተገልጋዮን በቁጣ ማሸማቀቃቸው ጥያቄ አስነሳ›› የሚል ዜና በረቡዕ ዕትሙ የፊት ገጽ ላይ ይዞ ወጥቷል፡፡ በዝርዝሩም ‹‹…በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የተለያዩ የክስ ሒደቶችን የሚያስችሉ ዳኞች በተገልጋዮ ላይ በሚያደርሱት ቁጣ፣ ተገልጋዮቹ በችሎቱ የተገኙበትን ጉዳይ ሳያስረዱ ተሸማቅቀው እንደሚመለሱ ተገለጸ፡፡..›› እያለ ይቀጥላል፡፡ ይህ የተገለጸው ከሕዝብ በቀረቡ ጥያቄዎች እንደሆነ በዜናው ላይ ተገልጧል፡፡
* * *
ሰንደቅ ጋዜጣ ‹‹ተማሪዎችን በውጤት ያንበሸበሸው የአ.አ.ዩ. ባልደረባ ቅጣቱን እየጠበቀ ነው›› ሲል ዘግቧል፡፡ ‹‹በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ እና የስነ-ትምህርት ፋኩሊቲዎች ውስጥ የተማሪዎች ሪከርድና ማኅደር ክፍል ሰራተኛ ሆኖ የ18 ተማሪዎችን ውጤት ከዲፓርትመንቱ መምህራኖች በመቀበል አሻሽሎ ወደሬጅስትራር አስተላልፏል ሲል የፌዴራሉ የሥነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚስን ዐቃቤ ሕግ ክስ የመሰረተበት አቶ ሰለሞን ኩምሳ….. የሰውም ሆነ የሠነድ መከላከያ ማስረጃ የለኝም በማለቱ የፍርድ ውሳኔ ለመስጠት.. ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቶታል፡፡››
* * *
ተመስገን ደሳለኝ በፍትህ ጋዜጣ ላይ ‹‹ፍትህን እና አልሻባብን ምን አገናኛቸው?›› ባለው መጣጥፉ ላይ ካልታወቀ እራሱን የአልሻባብ ወኪል ብሎ ከፍትህ ጋዜጣ ጋር ውል እንደነበረው ለማስመሰል በፍትህ ኢሜይል መልዕክት ስለላከ ሰው ጽፏል፡፡ ‹‹… እንደምታውቀው ለ30 ተከታታይ እትሞች 24,000 የአሜሪካን ዶላር ከፍለንሃል፡፡ አሁን ግን አልሻባብ ዕቅዶቹን ለመፈፀም የስልት ለውጥ አድርጓል፡፡ ስለዚህም 11,200 የአሜሪካን ዶላር የሚሆነውን የ14 እትሞች ክፍያ ለአልሻባብ እንዲመለስ እንፈልጋለን፡፡…›› የሚል እና ሌላም፣ ሌላም ይዘት ያለውን ደብዳቤ ተመስገን የተቀነባበረ ሴራ እንደሆነ ማረጋገጫ ያላቸውን ነገሮች ከዘረዘረ በኋላ ‹‹… ስርዓቱ እዚህ ድረስ ወርዶ ለመወንጀል እየሞከረ ያለው ሀገራችንን ጥለን እንድንሄድ አልያም ራሳችንን በዝምታ እንድንሸብብ ከሆነ፤ የሚሰማ ካለ አቋማችንን በተደጋጋመ ማሳወቃችንን ብቻ አስታውሶ ከማለፍ ውጪ አማራጭ የለውም፡፡..›› ብሏል፡፡
* * *
‹‹ዶ/ር እሌኒ ከኃላፊነታቸው ለቀቁ›› የሚል ዜና በፊት ገጹ ያስነበበው አዲስ አድማስ ‹‹… የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ የነበሩት ዶ/ር እሌኒ ገ/መድህን፣ የሥራ ማስፋፊያ ዕቅዳቸው ተቀባይነት ማጣቱን ሮይተርስ የዘገበ ሲሆን ሥራ አስፈፃሚዋ ከነበራቸው ኃላፊነት ለቀዋል፡፡ ዶ/ር እሌኒ በምርት ገበያ መስራችነታቸው ዓለምአቀፍ እውቅናና ሽልማቶች እንዳገኙ የሚታወቅ ሲሆን ድርጅቱን ለመመስረትና ለመምራት አብረዋቸው እንዲሠሩ በዓለምአቀፍ መመዘኛ ቀጥረዋቸው የነበሩ ዘጠኝ ባለሙያዎችም ከሳቸው ጋር ለቀዋል፡፡ የደርጅቱን ሥራ ለማስፋፋት ከመንግስት ጋር ውይይት ሲያካሂዱ መቆየታቸውን የተናገሩት ዶ/ር እሌኒ፣ አንዳንድ ዋና ዋና እቅዶች እንደከሸፉ ለሮይተርስ ገልፀዋል፡፡…. በዶ/ር እሌኒ ምትክ የአቢሲኒያ ም/ፕሬዚደንት የሆኑት አቶ አንተነህ አሰፋ የተሾሙ ሲሆን፣ ኩባንያው ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ሲሰሩና ልምድ ሲቀስሙ የነበሩ የአገር ውስጥ ተቀጣሪ የማኔጅመንት ባለሙያዎች፣ አመራሩን ተክተው ይሰራሉ ተብሏል፡፡…››
* * *
ላይፍ መጽሄት ‹‹‹ጥቁር ሰው› ለሚኒልክ፣ ‹ስቴድ›ስ ለማን ተዘፈነ?›› በሚል ርዕስ በጻፈው ጽሁፍ ላይ የብርቱኳን ሚዼቅሳን ምስል አስቀምጦ ለርሷ እንደተዘፈነ ተከራክሯል፡፡ እንደማስረጃ ያስቀመጠው ‹‹…ቃል እንዲህ ሆነ እንዴ…›› የሚለውን ሐረግ ሲሆን ይህንንም ያለው ብርቱኳን ለሁለተኛ ጊዜ ከመታሰሯ በፊት ‹‹ቃሌ›› ብላ የጻፈችውን ደብዳቤ በማጣቀስ ነው፡፡ በተጨማሪም ‹‹…ቃል እንዲ ሆነ እንዴ…›› ካለ በኋላ በደበሰባሳው ‹‹…በሃገሬ…›› የሚል ዜማ ያሰማል በማለት ክርክሩን አጠናክሯል፡፡
* * *
የቴዎድሮስ ተ/አረጋይን ቃለ ምልልስ በአዲስጉዳይ የሚያነቡ ከBBC - Hardtalk ጋር ያመሳስሉታል፡፡ በዚህ ሳምንት አቦይ ስብሃትን አነጋግሯቸዋል፡፡ ‹‹አቦይ ስብሃት ከኢሕአዴግ ፊትና ኋላ›› የሚል ርዕስ ከተሰጠው ምልልሳቸው ውስጥ እየቀነጫጨብን እንመለከታለን፡-
Friday, June 22, 2012
ህግ ምርኩዝ ነው ዱላ ?
ህዝብ አብሮ ሲኖር ግጭት ሊያስወግደው የማይችለው ነገር ነው፡፡ የሰዎች የእርስ በእርስ ግንኙነት እስካለ ድረስ ግጭት አለ፡፡ በግጭቱ ጉልበተኛው አሸንፎ ተሸናፊውን እንደፈለገ ይቀጣል ማለት ነው፡፡ ይህ እንግዲህ እንግሊዛዊው የስነ መንግስት ሊቅ Thomas Hobbes ‘State of Nature’ የሚለው ወይም ጉልበተኛ የሚገዛበት ደካማ የሚጠቃበት እና Hobbes “ life is solitary, poor, nasty, brutish, and short” ብሎ የገለፀው ሀሳባዊ አለም ነው፡፡
ይህ እንዳይሆን ህዝብ ስምምነት ላይ ደረሰ ይሄንም ስምምነት በልቦናው ፈረመ 'መንግስት' የሚባልም አካል መሰረተ፡፡ ይህ አካልም ከህዝቡ ጉልበት ተቀንሶ ጉልበተኛን ይቀጣ ዘንድ ተሰጠው እንዲሁም ይህ መብት እንዳለው ሁሉ የህዝቡን ሰላም የማስጠበቅም ግዴታ ተሰጠው፡፡ ማን ? መንግስት የተባለው አካል፡፡
ታዲያ መንግስት በጦር በጎራዴ ብቻ ሰላምን አያሰጠብቅም ይልቅስ ሰላማዊ መሳሪያውን ይመዛል ይሄም መሳሪያ የመንግስት ህግ ነው፡፡ ህዝቡም ያከብረው ዘንድ ይወዳል ወይም ይገደዳል፡፡ ስለዚህ የመንግስት ህግ ማለት መንግስት ህዝብ ከራሱ የተፈጥሮ ስልጣን ቀንሶ መንግስት ለተሰኝው አካል ስለሰጠው መንግስቱ ይሄን የህዝብ አደራ ለመጠበቅ የሚቀርብ በትር ነው፡፡
በመሰረቱ የኢትዮጵያም ታሪክ በዚህ የመንግስት ህልዮት ይገዛል፡፡ ነገሩ የሚበላሸው መንግስት የተባለው አካል የህዝብን አደራ በልቶ ሌላ ዳቦ መጋገር ሲጀምር ነው፡፡ የህዝቡን ዳቦ በልቶ የራሱን ሽልጦ ሲያነጉት ነው መከራው፡፡
መንግስታት በተቀያየሩ ቁጥር የህዝብን ሰላም እና ጥቅም ለመስጠበቅ ህግ ያወጣሉ፣ ይከለክላሉ፣ ያስጠብቃሉ፡፡ ይሄም እውነት በጠነከረ ሁኔታ አሁን ባለንባት ኢትዮጵያ ገዝፎ ይታያል፡፡
ለምሳሌ
Wednesday, June 20, 2012
የቴሌኮም ማጭበርበር ሕጉ አወዛጋቢነት
በአገራችን ረቂቅ ሕጎች የሚመለከተው ሕዝብ’ጋ በግልፅ ሳይደርሱ በጭምጭምታ ይቆዩና ድንገት በነጋሪት ጋዜጣ ታትመው ሕግ የመሆናቸው የተለመደ ድራማ በዚህ ረቂቅ አዋጅ ይለወጣል ብሎ መገመት ሞኝነት ነው፡፡ ይሄም ጽሁፍ በጭምጭምታው እውነታነት እና በረቂቅ ሕጉ ዙሪያ መጠነኛ ትንታኔ ይሰጣል፡፡
በቃሉ ኃይሉ (ስሙ ለዚህ ጽሁፍ ሲባል የተቀየረ) በስካይፕ የሚያወራው ከሚናፍቃቸውና ባሕር ማዶ ከሚኖሩ፣ እሱን ለማግኘት ኮምፒዩተር ላይ ቁጭ ብለው ከሚጠብቁት ጓደኞቹ’ጋ እንደሆነ ይናገራል፡፡ ‹‹እኔ እስከማስታውሰው ድረስ›› አለ ለዞን ዘጠኝ አስተያየቱን ‹‹እኔ እስከማስታውሰው ድረስ፤ ምንም ዓይነት ሕግ ሲወጣ ብወደውም ብጠላውም እታዘዝለት ነበር፡፡ አሁን ግን በስካይፕ ማውራት ሕገ-ወጥ ከሆነ ከጓደኞቼ እና ከሕጉ መምረጥ ሊኖርብኝ ነው፡፡ ጓደኞቼን ከሕጉ የማስበልጥበት ምክንያት እስካሁን አይታየኝም፡፡›› በቃሉ ይህንን የተናገረው አዋጁ ስካይፕ መጠቀምን በወንጀልነት ፈርጆታል የሚለውን ወሬ ከሰማ በኋላ ነው፡፡
‹‹የቴሌኮም ማጭበርበር አዋጁ›› ከስያሜውና ከትርጉም ክፍሉ ውጪ 18 አንቀጾች ብቻ አሉት፡፡ በሕገ-ወጥ መንገድ ስልክ ማስደወልም ሆነ ሌሎች የቴሌኮም አገልግሎቶችን ያለ ኢትዮ ቴሌኮም እውቅና መስጠት የማይቻል መሆኑ ድሮም በሕግ የተደነገገ ቢሆንም አሁን የዚህ አዋጅ መውጣት አስፈላጊ የሆነው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በማሕበራዊ ደረገጾች ላይ እያደገ የመጣውን ፀረ-አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊነት ለመገደብ እንደሆነ ብዙዎች መጠራጠር ጀምረዋል፡፡ የአዋጁ መግቢያ ላይም እንዲህ የሚል ይነበባል፡፡ ‹‹…የቴሌኮም ማጭበርበር ከኤኮኖሚ ኪሳራውም ባሻገር ዋና የደህንነት ስጋት በመሆኑ…›› ህግ አውጪው በረቂቅ አዋጂ ከኢኮኖሚያዊ ምክንያቶች ባለፈ ለሃገር ደህንነት ማሰቡን በግልጽ ይናገራል፡፤(በዚህ ጽሁፍ ውስጥ አዋጁ የተጣቀሰው ከእንግሊዝኛው ቅጂ ሲሆን ትርጉሙ የዞን ዘጠኝ ነው፡፡)
ኢሕአዴግ ለአብዮታዊ ዲሞክራሲ የሚያደርገው ቅጥ ያጣ ጥበቃ አብዮታዊ ዴሞክራሲ ትችቶቹን በሐሳብ ማሸነፍ እንዳቃተው ያሳብቃል፡፡ በጥቅሉ የመረጃ መረብን እና በዋናነት ማሕበራዊ ድረገጾችን ማዕከል አድርገው የሚንቀሳቀሱት የመረጃ ምንጮች እንደ ዶ/ር ዳኛቸው አባባል ‹‹የመረጃ ኦና.›› (Information Vacuum) ለመፍጠርና አውራ ፓርቲው ‹የሕዝብ› መገናኛ ብዙሐንን በመጠቀም የሚያጮኻቸው ወደአንድ አስተሳሰብ ያዘነበሉ መረጃዎች ለሚፈጥሯቸው የገደል ማሚቱ ድምጾች እንቅፋት ሆነዋል፡፡
የቴሌኮም ማጭበርበር ሕጉ አወዛጋቢነት
በአገራችን ረቂቅ ሕጎች የሚመለከተው ሕዝብ’ጋ በግልፅ ሳይደርሱ በጭምጭምታ ይቆዩና ድንገት በነጋሪት ጋዜጣ ታትመው ሕግ የመሆናቸው ነገር የተለመደ ድራማ በዚህ ረቂቅ አዋጅ ይለወጣል ብሎ መገመት ሞኝነት ነው፡፡ ይሄም ጽሁፍ በጭምጭምታው እውነታነት እና በረቂቅ ሕጉ ዙሪያ መጠነኛ ትንታኔ ይሰጣል፡፡
በቃሉ ኃይሉ (ስሙ ለዚህ ጽሁፍ ሲባል የተቀየረ) በስካይፕ የሚያወራው ከሚናፍቃቸውና ባሕር ማዶ ከሚኖሩ፣ እሱን ለማግኘት ኮምፒዩተር ላይ ቁጭ ብለው ከሚጠብቁት ጓደኞቹ’ጋ እንደሆነ ይናገራል፡፡ ‹‹እኔ እስከማስታውሰው ድረስ›› አለ ለዞን ዘጠኝ አስተያየቱን ‹‹እኔ እስከማስታውሰው ድረስ፤ ምንም ዓይነት ሕግ ሲወጣ ብወደውም ብጠላውም እታዘዝለት ነበር፡፡ አሁን ግን በስካይፕ ማውራት ሕገ-ወጥ ከሆነ ከጓደኞቼ እና ከሕጉ መምረጥ ሊኖርብኝ ነው፡፡ ጓደኞቼን ከሕጉ የማስበልጥበት ምክንያት እስካሁን አይታየኝም፡፡›› በቃሉ ይህንን የተናገረው አዋጁ ስካይፕ መጠቀምን በወንጀልነት ፈርጆታል የሚለውን ወሬ ከሰማ በኋላ ነው፡፡
‹‹የቴሌኮም ማጭበርበር አዋጁ›› ከስያሜውና ከትርጉም ክፍሉ ውጪ 18 አንቀጾች ብቻ አሉት፡፡ በሕገ-ወጥ መንገድ ስልክ ማስደወልም ሆነ ሌሎች የቴሌኮም አገልግሎቶችን ያለ ኢትዮ ቴሌኮም እውቅና መስጠት የማይቻል መሆኑ ድሮም በሕግ የተደነገገ ቢሆንም አሁን የዚህ አዋጅ መውጣት አስፈላጊ የሆነው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በማሕበራዊ ደረገጾች ላይ እያደገ የመጣውን ፀረ-አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊነት ለመገደብ እንደሆነ ብዙዎች መጠራጠር ጀምረዋል፡፡ የአዋጁ መግቢያ ላይም እንዲህ የሚል ይነበባል፡፡ ‹‹…የቴሌኮም ማጭበርበር ከኤኮኖሚ ኪሳራውም ባሻገር ዋና የደህንነት ስጋት በመሆኑ…›› ህግ አውጪው በረቂቅ አዋጂ ከኢኮኖሚያዊ ምክንያቶች ባለፈ ለሃገር ደህንነት ማሰቡን በግልጽ ይናገራል፡፤(በዚህ ጽሁፍ ውስጥ አዋጁ የተጣቀሰው ከእንግሊዝኛው ቅጂ ሲሆን ትርጉሙ የዞን ዘጠኝ ነው፡፡
ኢሕአዴግ ለአብዮታዊ ዲሞክራሲ የሚያደርገው ቅጥ ያጣ ጥበቃ አብዮታዊ ዴሞክራሲ ትችቶቹን በሐሳብ ማሸነፍ እንዳቃተው ያሳብቃል፡፡ በጥቅሉ የመረጃ መረብን እና በዋናነት ማሕበራዊ ድረገጾችን ማዕከል አድርገው የሚንቀሳቀሱት የመረጃ ምንጮች እንደ ዶ/ር ዳኛቸው አባባል ‹‹የመረጃ ኦና.›› (Information Vacuum) ለመፍጠርና አውራ ፓርቲው ‹የሕዝብ› መገናኛ ብዙሐንን በመጠቀም የሚያጮኻቸው ወደአንድ አስተሳሰብ ያዘነበሉ መረጃዎች ለሚፈጥሯቸው የገደል ማሚቱ ድምጾች እንቅፋት ሆነዋል፡፡
ከቻይና ምን መማር?
‘ሪፖርተርስ ዊዝ አውት ቦርደርስ’ የተባለ የጋዜጠኞች ድንበር የለሽ ቡድን ቻይናን ‹ከኢንተርኔት ጠላቶች› አንዷ እንደሆነች ያስቀምጣታል፡፡ የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ ልኡካን ቡድን ደግሞ በአዲስ አበባ ለሚገኘው አቻው - ኢሕአዴግ በብዙሐን መገናኛ እና ኢንተርኔት አስተዳደር ዙሪያ ያካበተውን ልምድ አካፍሎ ተመለሰው በቅርብ ጊዜ እንደሆነ በገዢው ፓርቲ ድረገጽ ላይ የሰፈረው ዜና ያስረዳል፡፡
ቻይና ‹‹የምዕራቡ ዓለም የመረጃ ነፃነት ባሕል የአገሬን ባሕል ያጠፋል›› በሚል ስም ለበርካታ ብዙሐን መገናኛ በሯን ዘግታለች፡፡ ለቻይና ብቻ ተብሎ የተዘጋጀው ጉግል አንዳንድ የኮሙኒስት ፓርቲን የሚያስቀይሙ ቃላቶችን እንዳይፈልግ ተደርጎ በልኳ ተሰፍቶላታል፡፡ ፌስቡክና ትዊተርም ታግደዋል፡፡
የቻይና የፍቅር ልጅ የሆነችው ሃገራችን ከቻይና በቀሰመችው ልምድና ቴክኖሎጂ የቪኦኤና የዶቼቬሌን ሬዲዮ ጣቢያ ማፈኗን መንግስቷ አምኗል፡፡ በርካታ ድረገጾችም ታግደዋል፡፡ አንድ የዞን ዘጠኝ አባል በግሉ ባደረገው ቅኝት 65 ነፃ ድረአምባዎች፣ 14 የፓርቲ እና ለፓርቲ የሚወግኑ ድረአምባዎች፣ 37 ጦማሮች፣ 7 የበይነመረብ ሬዲዮና ቴሌቪዥኖች እና 37 የፌስቡክ ቡድን ገጾች በኢትዮጵያ እንዳይነበቡ መደረጋቸውን አረጋግጧል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ነው አዲሱ አዋጅ በመረጃ ደህንነት መረብ አርቃቂነት ለፓርላማ የቀረበው፡፡ ‹አዲሱ አዋጅ ምን ዓይነት በቀላሉ ትርጉማቸውን ሊጠመዘዝ የሚችሉ አንቀጾች አሉት? የማሕበራዊ ድረገጽ እንቅስቃሴዎችን እንዴት ያውካቸዋል? ሐሳብን በነፃ ከመግለጽ መብት አንጻርስ አዋጁ እንዴት ይታያል? ስካይፕና ጉግል ቶክን የመሳሰሉት በVoice over Internet Protocol የሚጠቀሙ አገልግሎቶችን ሕገወጥ ያደርጋቸው ይሆን?› የሚሉ ጥያቄዎችን የሚያጭሩ እና ለማብራሪያ ክፍት የሆኑ አንቀጾችን ከዚህ በታች እንጠቃቅሳለን፡፡
አወዛጋቢዎቹ አንቀጾች
በአዋጁ ክፍል አንድ በተለዩ ቃላት ትርጉሞች ላይ የሚከተሉትን ያስቀምጣል፡፡ አንቀጽ 2 ላይ ‹‹የቴሌኮሙኒኬሽን ቁሳቁስ ማለት ለቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት የዋለ ወይም ሊውል የታቀደ ዕቃ፤ መገጣጠሚያ (accessories) እና ሶፍትዌሮችን ጨምሮ ማለት ነው፡፡›› ይላል፡፡ አንቀጽ 1 ላይ ‹የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት› የሚለውን ሲተረጉም በኤሌክትሮኒክ መንገድ የሚቀርቡ ጽሁፎች እና ምስሎች ከአገልግሎቱ እንደሚካተቱ ጠቁሟል፡፡ ሶፍትዌሮችን በዚህ ትርጉም ውስጥ በማካተት የተከታይ አንቀጾችን ትርጉም በዚያ መልኪ እንድናይ ያስገድደናል፡፡
ክፍል ሁለት፣ አንቀጽ 3 ‹‹ሚኒስትሩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመምከር የትኞቹ የቴሌኮሙኒኬሽን ቁሳቁሶች፣ አምራቾች፣ ገጣጣሚዎች፣ አስመጪዎች ፈቃድ እንደማይሹ ይገልጻል፤ ደንብ ያበጃል›› ይላል፡፡ ይህም በሚኒስትሩ (ሚኒስትሩ የሚባለው የኢንፎርሜሽን እና ኮምዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ነው፡፡) ያልተዘረዘሩ የመገናኛ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም፣ ተጠቃሚውን በወንጀልነት እስከ 4 ዓመት ፅኑ እስራት እና እስከ 40,000 ብር በሚደርስ ቅጣት፣ አስመጪ እና አከፋፋይ ድርጅቶችን ደግሞ ‹‹..ከ10 እስከ 15 ዓመት የሚደርስ ጽኑ እስራት እና ከ100,000ብር እስከ 150,000 ብር የሚደርስ ቅጣት..›› ሊያስከትልበት እንደሚችል ረቂቁ ይደነግጋል፡፡
የዚህ አንቀጽ ለትርጉም ክፍት መሆን የምንጠቀምባቸው የበይነመረብ ማሰሻዎች (Internet browsers)፣ ሶፍትዌሮች (skype, google talk…)፣ የስልክ ቀፎዎች (blackberry, iPhone, Android ስልኮች፣ ወዘተ…)፣ እና ሌሎችም ዓይነት በሚኒስትሩ ይወሰናሉ፣ ካልተወሰኑ ደግሞ ለመጠቀም ፈቃድ ያስፈልጋል የሚል አንድምታ ይኖረዋል ማለት ነው፡፡(የጆሮ ማዳመጫ የተጠቀመ ሰው ያልተፈቀደ መሳሪያ ገጣጥሞ ተጠቀመ ቢባል ሊስቀጣው ነው ማለት ነው እስከሚል የተለጠጠ ትርጉም ድረስ ሊወስደን ሁሉ ይችላል)
አንቀጽ 6(1) ደግሞ ‹‹ማንም የቴሌኮም መረብን ወይም መሳሪያን በመጠቀም በፀረሽብርተኝነት አዋጅ 652/2001 መሰረት የሽብር መልዕክት ቢያሰራጭ ወይም በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ መሰረት የሚያስጠይቅ አጸያፊ መልዕክት ቢያሰራጭ… ከ3 እስከ 8 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት እና ከ30,000 እስከ 80,000 ብር ድረስ ይቀጣል›› ይላል፡፡በዚህ አንቀጽ የተጠቀሰውን ወንጀል መፈጸም በዚህ ህግ ቢካታትም ባይካተትም ማስጠየቁ የማይቀር ሆኖ ሳለ በድጋሚ የተለየ ሽፋን መስጠቱ የህጉን አስፈላጊነት እንድንጠይቅ ያስገድደናል፡፡
አንቀጽ 13 ‹‹የቴሌኮም ማጭበርበርን ለመከላከል፣ ለመመርመርና ለመቆጣጠር ብሔራዊ የቴክኒክ ሥራ ቡድን ከሚመለከታቸው አካላት ተውጣጥቶ ይቋቋማል፡፡››
አንቀጽ 14 ‹‹ፖሊስ የቴሌኮም ማጭበርበር ተከስቷል ወይም ሊከሰት ይችላል ብሎ ባመነ ጊዜ ከፍርድ ቤት የብርበራ ፈቃድ መጠየቅ ይችላል፡፡›› ይህም የአንድ ሰው የስልክ ንግግር፣ አጭር የጽሁፍ መልዕክቶች፣ የኢሜይል መልዕክት ልውውጦች እንደአስፈላጊነታቸው የሚበረበሩበትን የሕግ አግባብ ይሰጣል ማለት ነው፡፡ መንግስት የኢንተርኔት አጠቃቀምን በተመለከተ ለአገሪቱ ደህንነት የሚያሰጉ ነገሮች ካሉ መቆጣጠር አለበት የሚለው ነጥብ ላይ መስማማት ቢቻልም የግለሰቦችን ነፃነት በተራ ፍራቻ ማሳጣት ግን ከሰብአዊ መብት ጥሰት ውስጥ ሊመደብ ይችላል፡፡
ህጉ በአጠቃላይ ካሉበት መሰረታዊ ገደቦች(limitations) መካከል ዋና ዋናዎቹ የግለሰቦችን ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት በሃገር ደህንነት ስም መንጠቁ፣ለትርጉም ክፍት የሆኑ ሰፋፊ ሃሳቦችን ማጠቃለሉ እንዲሁም የህጉን አስፈላጊነት በሚገባ ሊያሳምን አለመቻሉ ናቸው፡፡
ከሌሎች የተለመዱ ሕጎች በተለየ የማስረጃ ሁኔታን የዳሰሰው ይህ አዋጅ ለወትሮ ከምንጠቀምባቸው የማስረጃ አይነቶች በተጨማሪ ተቀባይነት ያላቸው ያላቸውን ተጨማሪ የማስረጃ አይነቶች ይጨምራል፡፡ይህ ከመሰረታዊ ሰብአዊ መብት ጥበቃ ጋር እና ከመሰረታዊ የወንጀል ህግ ጋር መታረቁ ያልተገጋገጠ የማስረጃ ስርአት በህጉ ትግበራ ወቅት ታርሞ ይተገበራል ማለት ዘበት ነው፡፡
ወደ ኢንተርኔት ወደ ስልክ መደወልን፣ያልተፈቀዱ ሶፍትዌሮችን መጠቀምን፣ እንዲሁም የጽሁፎችን ይዘትን በብዙ ከሚወቀሰው የጸረ ሽብርተኝነት ህግ ጋር ማቀላቀሉ ህጉን ከተጸፈበት በላይ አላም እንዳለው ሌላ ምስክር ነው፡፡
ወደ ስልክ መደወል እና ማስደወልን የሚከለክለው የህጉ አንቀፅ አስር ከተከለከሉ ሶፍት ዌሮች ጋር ተደምሮ የኢንተርኔት የድምጽ ንግግርን ወደ ወንጀልነት ይቀይረዋል፡፡
VoIP (Skype, Google Talk…) በሚኒስትሩ ይፈቀዱ ይሆን?
የቀድሞዋ አዲስ ነገር መራኄ ኤዲተር መስፍን ነጋሽ በፌስቡክ ገጹ ላይ ‹Promote then criminalize!› በሚል ርዕስ ባሰፈረው አጭር የስዕል ማብራሪያ ላይ (ምስሉን እዚህ ጦማር ላይ መመልከት ይቻላል) ከሁለት ቀን በፊት በሚኒስትሩ ድረገጽ ላይ VoIPን (Voice over Internet Protocolን) የሚያስተዋውቅ ይዘት ያለው መልዕክት ተለጥፎ እንዳገኘ (ያ ገጽ አሁን በሌላ ይዘት ተተክቷል) በምስል አዘጋጅቶ እና የመጀመሪያው መስመር ላይ "ስለ VoIP ሰምታችሁ የማታውቁ ከሆነ የረዥም ርቀት የስልክ ጥሪዎችን የምታደርጉበትን መንገድ ለመቀየር ተዘጋጁ" የሚል ነገር እንዳነበበ ጠቅሶ ጽፎ ነበር፡፡ መስፍን ነጋሽ ይህንን ሁኔታ ከረቂቅ አዋጁ አንፃር በመታዘብ አገልግሎቱን እያስተዋወቁ፣ ተጠቃሚዎቹን ወንጀለኛ ከማድረግ የተቀነባበረ ሴራ ለይቶ እንደማያየው ተናግሯል፡፡
የሚኒስተሩ ድረገጽ በፍጥነት በሌላ ጽሁፍ መተካቱ አዋጁ እውነትም VoIP ኢላማ አድርጎ ተነስቷል ብሎ ለመጠርጠር እንደ አንድ ግብአት ሊቆጠር ይችላል፡፡ በሌላ በኩል እ.ኤ.አ. በ2002 የቴሌሴንተር አገልግሎት ፈቃድን በተመለከተ በወጣው መመሪያ አንቀጽ 13(2) ላይ VoIP (ከኮምፒዩተር ወደ ኮምፒዩተር የሚደረግ የድምጽ ግንኙነት ጨምሮ /ስካይፕን ያካትታል/) የተከለከለ ቢሆንም እስካሁን ድረስ የተለያዩ ኢንተርኔት ካፌዎች ስካይፕን በይፋ ሲጠቀሙ እንጂ በወንጀል ሲከሰሱ የታየበት አንድም መረጃ የለም፡፡ ሌላው ቀርቶ ኢቴቪ የሕዳሴው ግድብን አንደኛ ዓመት አስመልክቶ ለጠቅላይ ሚኒስቴሩ በስካይፕ ጥያቄ ማቅረብ ይቻላል እያለ ሲያስተዋውቅ መክረሙ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡
በመሆኑም መመሪያው እያለ፣ የፀረ-ሽብርተኝነቱም ሆነ የወንጀለኛ መቅጫ ሕጉ እያሉ አዲሱ ‹የቴሌኮም ማጭበርበር አዋጅ› እዚያ የተካተቱትን ሕግጋት ደግሞ መውጣቱ ያስፈለገበት ምክንያት ግልጽ አለመሆን የእነዚህን የቴክኖሎጂ ውጤቶች መስፋፋት ተከትሎ እያደገ የመጣውን ሐሳብን በነፃ የመግለጽ መብት ለማፈን የተወሰደ እርምጃ ነው የሚለውን መላምት ያጠናክረዋል፡፡ ለዚህም እንደዋቢ መጥቀስ የሚቻለው በረቂቁ ላይ ‹‹መንግስት በሕዝቡ አመኔታ እንዲያጣ የሚያደርግ…››፣ ‹‹… አፀያፊ ጽሁፎች›› የሚሉ አሻሚ እና ሰፊ ትርጉም የሚኖራቸውን ሐረጎች መጠቀሙ የአዋጁ ኢላማ በተለይ ማሕበራዊ ድረገጾች ላይ በሚደረጉ የግል ሐሳብን በነፃ የመግለጽ መብት ላይ ስጋት የሚጥሉ ሆነዋል፡፡
ሚኒስትሩ VoIPን ከሚከለከሉ አገልግሎቶች መካከል እንደሚያስቀምጣቸው ለመጠርጠር የሚያበቃ ሌላም ምክንያት አለ - የገዢው ፓርቲ የቅርብ ሚዲያ እና ህግ አውጪው ሬድዮ ፋና፡፡ የዜና መጽሄት በተሰኘው ፕሮግራሙ ሬዲዮ ፋና የረቂቅ አዋጁ መንፈስ ሁሉንም ዓይነት VoIPን የሚጠቀሙ አገልግሎቶችን ለማገድ የወጣ እንደሆነ ፍንጭ ይሰጣል:: በተለይ (በፕሮግራሙ ላይ) አንድ የምክር ቤት አባል የአዋጁን አስፈላጊነት ለማስረዳት ሲናገሩ ኢትዮ ቴሌኮም እንደስካይፕ ያሉ በኢንተርኔት ስልክ የማስደወያ ሶፍትዌሮችን በሕግም ሆነ በቴክኖሎጂ ቁጥጥር ስር ማድረግ እንዳለበት አስረድተዋል:: አዲሱ የቴሌኮም አዋጅ ረቂቅ ደግሞ ለቴሌ ይህን ሕጋዊ ዳራ ይፈጥርለታል::
አዋጁ ከኢትዮ ቴሌኮምም በላይ በድብቅ የኢንተርኔት ማጥለል (Internet filtration) ሥራ በመስራት የሚታማውን የመረጃ መረብ ደህንነት ኤጀንሲን (INSAን) ነፃ ያወጣዋል - የረቂቁ አንቀጽ 13 ‹የቴክኒክ የሥራ ቡድን›መቋቋም የሚለው ከለላ በማስቀመጥ፡፡
ባሳለፍነው ሳምንት እየተዘዋወርን ያነጋገርናቸው ጥቂት የኢንተርኔት ካፌ አገልግሎት ሰጪዎች ከወዲሁ (አዋጁ ከመጽደቁ እና በነጋሪት ጋዜጣ ከመውጣቱ በፊት) የስካይፕ እና ማንኛውንም የድምጽ (Voice over IP) አገልግሎት መስጠት ማቆማቸውን ለመረዳት ችለናል፡፡
ዳንኤል ብርሃነ ከላይ ባጣቀስነው ጦማሩ ላይ ‹‹ስካይፕ በሕግ እንደማይታገድ የጥብቅና ባርኔጣዬን አስይዤ እወራረዳለሁ›› ሲል ከተከራከረው በተቃራኒ መደምደም እንደሚቻለው፣ አዋጁ አሁን አሁን እያቆጠቆጠ የመጣው በበይነመረብ ላይ ሐሳብን በነፃ የመግጽ ፍላጎት ላይ ክፉ ጥላ መጣሉ ነው፡፡ እንዲያውም አንዳንዶች የአዋጁ ብቸኛ ዓላማም ይኸው ነው ሲሉ ጥርጣሬያቸውን ከወዲሁ እየገለፁ ነው፡፡ ውጤቱን ለማየት ግን አዋጁ ፀድቆ(በፓርላማ ክርክር እና የጋለ ውይይት ጋር) የተግባር እርምጃው እስኪጀመር ጥቂት ወራት ብቻ መታገስ በቂ ይሆናል፡፡
Tuesday, June 19, 2012
የኢትዮጵያ ጦማሮች ምን ፃፉ?
(ከሰኔ 6 እስከ ሰኔ 13)
‹‹እነአልበርት አንስታይን ስለዘንድሮው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ምን ይላሉ?››በማለት በ‹የበፍቄ ዓለም› ላይ ይህን ፅሁፍ ጀባ ያለን በፍቃዱ ዘሀይሉ ነው፡፡ በዚህ ጽሁፉ ላይ የዓለም ሶስት ታላላቅ ሰዎችን እይታ ከአገራችን ነባራዊ የፖለቲካ አስተሳሰብ ጋር አነጻጽሮልናል፡፡
በአልበርት አንስታይን ታዋቂ አባባል “The world will not be destroyed by those who do evil, but by those who watch them without doing anything.” (ዓለማችን የምትጠፋው ክፉ በሚያደርጉ ሰዎች ሳይሆን ክፉ ሲያደርጉ እያዩ ዝም በሚሏቸው ሰዎች ነው፡፡) የጀመረው ይህ ፅሁፍ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ችግር አይተው እነዳላዮ አላፊዎችን እነዲህ ሸንቆጥ አድርጓቸዋል፡፡
Monday, June 18, 2012
Opportunism (ዝንደዳ?)
ከሰው ልጆች የስልጣኔ ታሪክ ጋር እኩል የሚጠቀስ ረጅም ታሪክ አለው፡፡ ከክርስቶስ ልደት አምስት መቶ አመታት በፊት አቴና የብዙ ሰዎች መመላለሻ በመሆኗ የከተማው ኑሮ የበረታ ወድድርን ፈጠረ፡፡ በዚህም ምክንያት ከተለመደው የተመጠነ ጤናማ አካልና መንፈስን የሚያጎለብት ትምህርት በላይ የሆነ ነገር ያስፈልግ ነበር፡፡ በዘመኑ የነበሩ (sophist) ሶፊስት የተሰኙ ሊቃውንት ሰባት የትምህርት ስልቶች (grammar, dialectics, Rhetoric, mathematics, geometry, astronomy and music) በደንብ አቀናብረው የከተማውን መላ ወጣቶች በተለይ የሀብታሞቹን ልጆች ደሞዝ እየተቀበሉ በመዘዋወር (አንድ ቦታ ሳይረጉ) ያሰተምሩ ነበር፡፡ ዋናው ዓላማቸውም እንዴት የወቅቱን ሁኔታ ተጠቅሞ መክበር እንደሚቻል ማሳየት ወይም አላግባብ ለመበልጸግ የሚረዳ ዕውቀት ማቀበል ነበር፡፡ ፖለቲከኛውን ለስልጣን፣ ነጋዴውን ወደሀብት በሌላም የኑሮ ዘርፍ ለተሰለፈው ለሥራው አስፈላጊውን ነገር ብቻ ይሰጡ ነበር፡፡
ይህ ነገርን ሁሉ ለግል ጥቀም ማበጃጀት ለዓለማችን ስልጣኔ እንደምሶሶ የሚቆጠሩት ቀደምት ፈላስፎች (ሶቅራጠስ፣ ፕላቶና አሪስጣጣሊስ) በአጽንኦት የተቃወሙት ዐሳብ ነው፡፡ ትምህርት መታሰብ ያለበት ከጥቅም ባሻገር ነው፤ ከፍ ያሉ በሰውነት (ሰው በመሆን) በሚገኙ የስነምግባር ሕግጋትን በማስቀደም ነው፡፡ በተለይ ትልቁ የአውሮጳ መምህር ሶቅራጠስ ሰው እያንዳንዱን አጋጣሚ ለመመዝበር (to exploit) ወደወጭ ከማየቱ በፊት ‘ራስን ማወቅ’ን ፣ ወደውስጥ ማየትን ማስቀደም እንዳለበት አስተምሯል፡፡ ከእርሱ በወጉ የተማረው ፕላቶ ደግሞ ጉዳዩን አስፋፍቶ አስተምሯል፡፡ ይህ የትምህርት መሰረታዊ የአቅጣጫ ለውጥ በዘመናችን በምዕራባውያን መሪነት ዓለማችን ለደረሰችበት ቁሳዊም ሆነ ሌሎች ከፍታዎች እንደ መሰረትነት አገልግሏል፡፡የሶፊስቶችን ህጸጽ በቅጡ የተረዳው ጀርመናዊ ባለቅኔ “ዕውቀት ለአንዱ ለሁልጊዜ የሚያከብራት ወደላይ ወደአርያም የምትመራው ሰማያዊት ነብይት ናት፡፡ ለሌላው ግን በወተትና በቅቤ የምታገለግለው አንድ ወፍራም ላም ናት” ሲል የተናገረው ምነኛ! ድንቅ ነው፡፡
Sunday, June 17, 2012
ጋዜጣ እና መጽሄቶቻችን ከሰኞ እስከ ሰኞ - ሁለት
የኛ ፕሬስ ጋዜጣ ‹‹የኮንደምኒየም እጣ ውሃ በላው!›› የሚል ዜና ይዞ ወጥቷል፡፡ ‹‹… 128 ሰዎች ሁለትና ከሁለት በላይ የኮንደሚኒየም ቤቶችን ወስደዋል፣ ትክክለኛውን ተመዝጋቢ በመሰረዝና በሌላ በመተካት የሙስናና የዝምድና ሌብነት ተጧጡፏል፡፡…›› የሚሉ ችግሮችን የነቀሰው ዜና ምንጩ የመንግስት መስሪያ ቤት ነው፡፡ ‹‹… የፌዴራል የስነምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በአዲስ አበባ ከተማ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለተጠቃሚዎች በማስተላለፍ ሂደት ላይ ሰፋ ያለ ጥናት ያደረገ ሲሆን፣ ኮሚሽኑ አደረኩት ካለው ጥናት መኖሪያ ቤቶቹን ለተጠቃሚዎች በማስተላለፍ ሂደት ላይ ለሙስና የተጋለጡ ስምንት የሚደርሱ አሰራሮችን አጋልጧል፡፡…››
‹‹ከአብዮታዊ ዴሞክራሲ ውጪ ያለው ሁሉ የጥፋት መንገድ ነው የሚል አመለካከት ነበረኝ›› ያሉት አቶ ገብሩ አስራት ለየኛ ፕሬስ ጋዜጣ ነው፡፡ አቶ ገብሩ ከጋዜጣው ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ ቀነጫጭበን እንመለከታለን፡-
‹‹… እኛና ሌሎች ተቃዋሚዎች የምንሄድበት አቅጣጫ ይለያያል፡፡…››
‹‹… ከኢሕአዴግ ከወጣን በኋላ… ዴሞክራሲ ማለት ራሱ ምንድን ነው? ዴሞክራሲ ያለነፃ ጋዜጦች? ዴሞክራሲ ያለ ሲቪል ማሕበረሰብ? ያለነፃ የፍትሕ ስርዓት ሊኖር ይችላል ወይ? የሚል ጥያቄዎችን አንስተናል፡፡ በአብዮታዊ ዴሞክራሲ ሁሉም ተቋማት በአንድ ፓርቲ ስር መግባት አለባቸው የሚል አስተያየት አለ፡፡…››
‹‹…ልማትና ዕድገት ሁለት የተለያዩ ጉዳዮች ናቸው፡፡ ዕድገት ከየትም መጥቶ ጥቂት ሚሊየነሮችን ሊያስገኝ ይችላል፡፡ እነዚህ ሰዎች ገንዘብ ዘርፈው ካጠራቀሙም ዕድገት ነው፡፡…››
‹‹… እስቲ ቦሌ ሂዱና ተመልከቱ፡፡ ያ ሁሉ ሕንፃ የማነው? ምን ያህሉ እንዳሉ መቁጠር ትችላላችሁ፡፡ በመንግስት ስር የሚተዳደር ሰው ከ5 ሺህ እና 6 ሺህ በላይ አያገኝም፡፡ በዚህ ገንዘብ ልጆችን እንኳን ማስተማር አይቻልም፡፡ ነገር ግን እነዚህ ሰዎች ልጆቻቸውን ውጭ አገር ልከው እያስተማሩ ነው፡፡ በመንግስት ሠራተኛ ደሞዝ ይሄ ሁሉ ሀብት ሊገኝ ይችላል ወይ? ...››
‹‹… [የትግራይ ርዕሰ መስተዳድር ሳሉ የግል ጋዜጦችን በተመለከተ ‹ትግራይ የማንም ቆሻሻ ማራገፊያ አትሆንም› ስለማለታቸው] ሌሎች የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ሆኑ የግል ጋዜጦች ፋይዳ የላቸውም የሚል አቋም በፓርቲ ደረጃ ይዘን ነበር፡፡ አብዮታዊ ዴሞክራሲ ነው ትክክለኛው አቅጣጫ ከዚያ ውጪ ግን የጥፋት መንገድ ነው የሚል እምነት ነበረን፡፡…››
የኛ ፕሬስ ቴዲ አፍሮ ሁለት ድግሶችን በአንድ ሳምንት መደገሱን ጠቅሶ ባቀረበው ዘገባ ላይ ‹‹... ባለፈው ቅዳሜ በጣይቱ ሆቴል በተከናወነው የምስጋና የምሳ ግብዣ ላይ ንግግር እንዲያደርጉ የተጋበዙት የማስታወቂያ ባለሙያው አቶ ውብሸት ወርቅአለማሁ በወቅቱ አንድ ትልቅ ስብሰባ አቋርጠው ወደ ግብዣው እንደመጡ ከተናገሩ በኋላ ‹ይህንን ያደረግኩት ከእግዚአብሔር እና ከቴዲ አፍሮ ጥሪ ላይ መቅረት ያስቀስፋል› በሚል የተቀኘ የተጋነነ አድናቆታቸውን እንደሰነዘሩ ለመገንዘብ ተችሏል›› ብሏል፡፡
ምራቂ /ምርቃት/
የኛ ፕሬስ ጋዜጠኞች ከኢትዮ ቻናል ተገንጥለው ነው የራሳቸውን ጋዜጣ የከፈቱት፡፡ ከኢትዮ ቻናል ሲወጡ ‹ሰዓት እላፊ› የተሰኘች ተነባቢ አምዳቸውን ከነካርቱነኛዋ ይዘዋት ወጥተዋል፡፡ ይቺ አምድ የ‹‹ሴተኛ አዳሪዎችን›› ቃለ ምልልስ ይዛ የምትወጣ ሲሆን ከግርጌዋ ‹‹ራስዎንና ቤተሰቦን ከኤችአይቪ ኤድስ ይጠብቁ፤ የዚህ ገፅ ስፖንሰር፡- ሰላም ባርና ሬስቶራንት (ሰበታ)›› የሚለውን ሲያነቡ ፈገግታ ታጭራለች፡፡
* *
‹‹ኢትዮ ቴሌኮም ዌብሳይቶችን የሚገድብ ኔትወርክ እየዘረጋ ነው›› ያለው ደግሞ መሰናዘሪያ ጋዜጣ ነው፡፡ በዝርዝሩም ‹‹በኢትዮጵያ በብቸኝነት የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት የሚሰጠውና በኢትዮጵያ መንግስት የሚተዳደረው ኢትዮ ቴሌኮም ግለሰቦችና ድርጅቶች በኢንተርኔት የሚለዋወጧቸውን መረጃዎች እየለጠፈ የሚመረምርና እንደአስፈላጊነቱ ዌብሳይቶችን የሚገድብ ቶር የተባለ ኔትወርክ እየዘረጋ መሆኑን ሪፖርተርስ ዊዝ አውት ቦርደር የተባለ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ቡድን አስታወቀ፡፡…›› (በነገራችን ላይ መሰናዘሪያ ቶር በማለት የገለጸውን ዊኪፔድያ እንዲህ ሲል ይበይነዋል… Tor (short for The onion router) is a system intended to enable online anonymity. Tor client software routes Internet traffic through a worldwide volunteer network of servers to conceal a user's location or usage from anyone conducting network surveillance or traffic analysis. በሌላ በኩል የቶር ፕሮጀክት ድረአምባ በኢትዮጵያ እንዳይነበብ ታግዷል፡፡)
መሰናዘሪያ በሌላ ዜና ደግሞ ‹‹ኢትዮጵያ ድንበር ተሸጋሪ ጉዲፈቻ በስፋት ከሚካሄድባቸው አስር የአፍሪካ ሃግሮች በሁለተኛ ደረጃ መቀመጧን በመዲናችን በአዲስ አበባ በተካሄደው በአምስተኛው ዓለም አቀፍ የአፍሪካ ሕፃናት የፖሊሲ ኮንፈረንስ ላይ የቀረቡ መረጃዎች አመለከቱ፡፡…›› ብሎ ዘግቧል፡፡
* * *
ያለዕለቱ ዘግይቶ ረቡዕ የወጣው ፍኖተ ነፃነት ‹‹በቃሊቲ ማረሚያ ቤት የተደረገው የማደራጀት ሙከራ እስረኞችን አስቆጣ›› የሚል ዜና በፊት ገጹ ይዞ ወጥቷል፡፡ ሲተነትነው ‹‹ቃሊቲ በሚገኘው ማረሚያ ቤት የሚገኙ እስረኞች 1ለ25 እንዲደራጁ ታዘው አብዛኛዎቹ መደራጀት እንደማይፈልጉ አቋም በመያዛቸው አለመግባባት መፍጠሩን የዜና ምንጮቻችን አስታወቁ፡፡… እስረኞቹ የእያንዳንዱን እስረኛ የ24 ሰዓት ውሎ የሚገመግም አደረጃጀት እንዲታቀፉ ቢጠየቁ እምቢተኛ ሆነዋል፡፡…››
Friday, June 15, 2012
Generation “?”
[caption id="attachment_89" align="alignright" width="604"] courtesy "http://www.addisfortune.com"[/caption]
The Lost Generation ፡ ይሄ ትውልድ ከ19 ክፍለ ዘመን መጨረሻ እስከ አንደኛው የአለም ጦርነት መጨረሻ የነበረው ሲሆን በጦርነቱ ማብቂያ ህልውናው ያከተመ ነው፡፡
The Silent Generation፡ ይህ ዝምተኛ ትውልድ ደግሞ የአንደኛው የአለም ጦርነት ከተጠናቀቀበት እስከ ታላቁ የኢኮኖሚ ድቀት (The Great Depression) ድረስ የነበረው ሲሆን በአመዛኙ ድብታ የዋጠው ነበር፡፡
The Greatest Generation: ታላቁ ትውልድ የተሰኝው ደግሞ ታላቁን የኢኮኖሚ ድቀት ተቋቁሞ በሁለተኛው የአለም ጦርነት ተፈትኖ ያለፈው እና እንደ ብረት የጠነከረ የተባለው ነው፡፡
Generation X፡ ይህ ትውልድ ከሁለተኛው የአለም ጦርነት ማብቂያ ጀምሮ የ1960ዋቹን አለማቀፍ የነፃነት፣ የአንድነት እንዲሁም የፀረ-ጦርነት ሰልፎች ሲያካሂድ የነበረ እና በባህል ለውጥ ረገድ ትልቅ አስተዋፅኦ ያደረገው ትውልድ ነው፡
Generation Y or The Millennial Generation: የ Generation X ተከታይ ትውልድ ሲሆን በቴሌቪዥን እና በዲጅታል ሚዲያዎች ፍቅር የወደቀ እንዲሁም በሁሉም ነገር ለዘብተኛ ሊባል የሚችለው ትውልደ ነው፡፡
Generation Z፡ የDotcom Bubble ውጤት የWorld Wide Web ፍሬ እና ቀሰስተኛው ትውልድ ሲሆን ዘመኑም አሁን ነው ይላሉ፡፡
እነዚህን እና የመሳሰሉትን የትውልድ ተረኮች አሉ፡፡
ወደ ሀገር እኛ ሁኔታ ስንመጣ መሰረታዊ የሆነ የትውልድ ልዩነት፣ ጊዜ እንዲሁም ስያሜ አለ ማለት ባይቻልም በተለምዶ 'ያ ትውልድ' እየተባለ የሚጠራው እና የኢትየጵያን አብዮት የመራው እንዲሁም ከ ሶሻሊዝም ጋር በፍቅር ያበደው ትውልድ እንደ አንድ ትውልድ ይዘን ወደፊት እና ወደኋላ መሄድ እንችላለን፡፡
Sunday, June 10, 2012
ጋዜጦቻችን ከሰኞ እስከ ሰኞ - አንድ
በአጭር ጊዜ ውስጥ ተነባቢነት ያተረፈውና በአንድነት ፓርቲ አሳታሚነት ማክሰኞ ገበያ ላይ የሚውለው ፍኖተ ነፃነት በመላው ሃገሪቱ ሰፊ የመረጃ መረብ ስላለው ሁሌም ዜናዎቹ ትኩስና ያልተሰሙ ናቸው፡፡ በዚህ ሳምንትም ከዜናዎቹ ውስጥ እነዚህ ነበሩበት፡-
‹‹…በጎንደር ፖሊስ የሟቾችን አስከሬን በመኪና መሬት ለመሬት አስጎተተ….
‹‹… የዜና ምንጮቻችን እንደሚሉት ‹አቶ ሽንኩ ከፍያለውና አቶ ዳኛቸው የተባሉ ሁለት ግለሰቦች ከፀጥታ አስከባሪዎች ጋር የተኩስ ልውውጥ አድርገው ከተገደሉ በኋላ አስከሬናቸው መሬት ለመሬት ሲጎተት ውሏል› ብለዋል፡፡….››
ጋዜጦቻችን ከሰኞ እስከ ሰኞ - አንድ
በአጭር ጊዜ ውስጥ ተነባቢነት ያተረፈውና በአንድነት ፓርቲ አሳታሚነት ማክሰኞ ገበያ ላይ የሚውለው ፍኖተ ነፃነት በመላው ሃገሪቱ ሰፊ የመረጃ መረብ ስላለው ሁሌም ዜናዎቹ ትኩስና ያልተሰሙ ናቸው፡፡ በዚህ ሳምንትም ከዜናዎቹ ውስጥ እነዚህ ነበሩበት፡-
‹‹…በጎንደር ፖሊስ የሟቾችን አስከሬን በመኪና መሬት ለመሬት አስጎተተ….
‹‹… የዜና ምንጮቻችን እንደሚሉት ‹አቶ ሽንኩ ከፍያለውና አቶ ዳኛቸው የተባሉ ሁለት ግለሰቦች ከፀጥታ አስከባሪዎች ጋር የተኩስ ልውውጥ አድርገው ከተገደሉ በኋላ አስከሬናቸው መሬት ለመሬት ሲጎተት ውሏል› ብለዋል፡፡….››
‹‹…በቤንች ማጂ ዞን በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገደሉ….
‹‹… የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ባደረጉት ማጣራት የፌዴራል ፖሊስና የመከላከያ ሰራዊት ከመጠን ያለፈ ኃይል ተጠቅመው [ለአራት ወራት የፀጥታ ችግር የሰፈነበትን] አካባቢውን ለማረጋጋት ሞክረዋል፡፡… በዚህ የኃይል እርምጃ በመቶዎች የሚቆጠሩ የአካባቢው ነዋሪዎች እንደተገደሉ [ምንጮች] አስረድተዋል….››
‹‹…የኢትዮጵያ ፕሬስ አሳታሚዎች ማህበር የመተዳደሪያ ደንቡን አፀደቀ….
‹‹… በምስረታ ላይ ያለው የኢትዮጵያ ፕሬስ አሳታሚዎች ማህበር (ኢፕአማ) ሰኞ ግንቦት 27 ቀን 2004 ባካሄደው ስብሰባ የመተዳደሪያ ደንቡን አፀደቀ….››
‹‹…ግንቦት 20ን ለማክበር 120 ሚሊዮን ብር መውጣቱ ተጠቆመ….
‹‹… [የፍኖተ ነፃነት ምንጮች] እንደሚሉት ‹ሰዎችን ጋብዞ ላመጣ አንድ ሺ ብር፣ ለፎረም አባል 600 ብር፣ ለቀበሌ ቀስቃሽ 300 ብር፣ ለሰልፈኛ መቶ ብር እየተከፈለ የተሰበሰበ ነው፡፡ ለዚሁ ማስፈፀሚያ የሚውል ለኦሮሚያ ብቻ 30 ሚሊዮን ብር መመደቡን› ያስረዳሉ፡፡ ….››
የፈቴሌ እማሬ እና ፍካሬ (ፍኖተ ነፃነት፤ በነብዩ ኃይሉ) ያስነበበን ትንታኔ ደግሞ ስለስልክ መጠለፍ ያወጋናል፡- ‹‹… በአንዳንድ የስልክ ልውውጦች ላይ የራስህን ድምጽ መልሰህ የምትሰማበት፣ ከሌሎች ስልኮች በተለየ በአድ ድምጽ የምትሰማበት፣ የሦስተኛ ወገን ንግግር በጣልቃ የሚሰማበትና የሚቆራረጥበት ሁኔታ ስልክ መጠለፉን የሚያሳዩ ምልክቶች ናቸው፡፡… ባለሙያዎች እንደሚሉት ቴሌ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ እያጋጠሙት ያሉት ችግሮች መካከል በዋነኝነት የሚጠቀሰው የኔትወርክ መጨናነቅ ድርጅቱ ለጠፋ ተግባር የሚጠቀምባቸው በአድ መሳሪያዎች ጠንቅ እንደሆነ ይናገራሉ…››
* * *
የጋዜጠኛ ስንዱ አበበ አስገራሚ ቃለ ምልልስ ከየኛ ፕሬስ ጋዜጣ ጋር፤ ቀንጨብ፣ ቀንጨብ እያረግን እንመልከተው፡-
‹‹ጥንቆላ ለልማት መዋል ቢችል ኢትዮጵያ ፈጣን ለውጥ ታመጣለች›› ይላል ርዕሱ!
‹‹… ብዙ ኢትዮጵያውያን ችሎታ እንዳላቸው ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ ግን ችሎታቸውን ለክፋት ነው የሚያውሉት፡፡ ለምን? እኔ አሁን እንዲጠየቅልኝ የምፈልገው ይሄንን ነው፡፡…
‹‹… እኔ እንግዲህ ጋዜጠኛ ነበርኩ፡፡ ነፃ ጋዜጣ ሲመሰረት ጀምሮ ከነበሩት ሰዎች አንደኛዋ ነበርኩ፡፡ አንዱ ጋዜጣ ጥሩ ነገር ሲያወራ ሰምተሃል? አሉባልታ፣ ክፋት፣ የሰው ስም ማጥፋት፡፡ እንድታድግ፣ እንድትቀየር፣ የተሳሳትከውን ነገር እንኳ ሲጽፉ የሚፅፉበት መንገድ በክፋት ተወሳስቧል፡፡ ክፋት በዝቷል፡፡ ለምን ይህን ያህልስ እንከፋፈላለን? ክፋት ምን ያደርጋል? ግን ችሎታህን ለክፋት መጠቀም በጣም መርዛማ መርዛማ አኗኗር ነው፡፡ ቫይብሬሽኑን ራሱ መርዛማ አድርገውታል፡፡ የመጀመሪያው ተጠያቂ ደግሞ ሚዲያው ነው፡፡…
‹‹… በማጂክ የምንኖር መሰለኝ እኮ! ሰርተህ ምንም የለም፡፡ እኔ አሁን ዘጠኝ መጽሃፍ አትሜያለሁ፡፡ ላይፌን ደሞ እየው፡፡ ምንድን ነው ይሄ? ምንም ማለት ነው፡፡ ምን ሆኖ? የት ሄደ? የሰራኹት ገንዘብ የት ሄደ? ያ ሁሉ ስራ ምንድን ነው የሆነው? ብትለኝ ላስረዳህ አልችልም፡፡ ውልብልብ ነው… ሁሉም ሰው ገብቶታል ይሄ፡፡…
‹‹… በመንግስት በኩል ለምሳሌ እንየው ብንል ማተሙን አትከለከልም፡፡ ግን ማከፋፈል ላይ ይይዙሃል፡፡ ሜጋ አይገባም ካሉህ አለቀ፡፡ በስንት ቡክ ሾ ልትሸጥ ነው ሜጋ ካልገባህ፡፡ ስለዚህ ያከስሩሃል፡፡…
‹‹…[ኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው ጋዜጠኝነት] መጥፎ የሆነ ህዝብ የሚመራ መድረክ ስለሆነ ህዝቡንም ምን ያህል ክፉ እንዳደረግነው አስብ፡፡ እና በጣም ያሳፍራል፡፡ እና ጋዜጠኛ መባል፣ ቃሉንም መባሉንም አልፈልገውም፡፡ ስለነበርኩም አሁን ላይ ይደብረኛል፡፡…
‹‹… ብዙ ጊዜ ደግሞ ጋዜጦቹ ማተም የሚፈልጉት አሉባልታ ነው እንጂ እውነት የተደከመበት ስራ አይደለም፡፡…
‹‹… ስታየው ያለንበት ሁኔታ ተመሰቃቅሏል፡፡ ሃይማኖቶቹም ተመሰቃቅለዋል፡፡ ፖለቲካውም ተመሰቃቅሏል፡፡ ምንድን ነው ስትል ‹‹ሞስትሊ›› ጥንቆላ የሚባለው ጠልሞስ፣ ዛር፣ ደብተራ… እንግዲህ እነኚህ በአግባቡ ያልፈተሽናቸው ኢትዮጵያውያን እሴቶች ናቸው፡፡ አሁን አሉ? የሉም? መጠናት አለበት፡፡ ግን እኔ አሁንም ባለው ሁኔታ ላይ ጥንቆላ ለልማት መዋል ቢችል ኢትዮጵያ ፈጣን ለውጥ ታመጣለች፡፡…
‹‹… እናድናለን ይላሉ፡፡ ያጎራሉ፤ ከሁሉ ነገር ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ስለዚህ ለኔ ኢትዮጵያዊ አዕምሮ - የያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ አዕምሮ ከጥንቆላ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ስለዚህ እነዚህ ሴክተሮች ተጠንተው ለልማት የሚውሉበት መንገድ ካለ መንግስት ይህን ቢመረምር ይሻላል የሚል አቋም አለኝ፡፡…››
‹‹… እኔ የሰራኋቸው መጽሃፎች ወደፊት ገና ትንታኔ ይፈልጋሉ፡፡ በአዋቂ ሰዎች፣ ዩኒቨርስቲዎ ፔፐር ይሰሩባቸዋል፡፡ ይደርሳል፡፡ እንደሚደርስ እርግጠኛ ነኝ፡፡ ከአምስት ስድስት ዓመተ በኋላ የኔ መጽሃፎች በጣም እንደሚፈለጉ አምናለሁ፡፡ ስለዚህ ይህን ቀን ለማየት ፀጥ ብሎ ራስን አክብሮ መኖር፡፡››
* * *
መሰናዘሪያ በበኩሉ የዶ/ር ኃይሉ አርአያን ምስል ከሽፋን ገጹ ላይ ይዞ ወጥቷል፡፡ ዶ/ሩ ለጋዜጣው ሲነግሩት እንዲህ ብለዋል፤ ‹‹… የአንድ አምባገነን ግለሰብ መለወጥ ምንም ለውጥ አያመጣም…
‹‹… የልማት ማዕከሉ ሰው ነው፡፡ አንድ ነገር አደገ ሲባል የሰውን ህይወት መለወጥ አለበት… የዕለትተዕለት ኑሮውን ካላሻሻለው ዋጋ የለውም፡፡ … ያለነፃነት የተሟላ ልማት ሊኖር አይችልም፡፡ ውሸት ነው ቀጣይ የሆነ ዘላቂ ልማት ሊኖር አይችልም፡፡…››
* * *
ሪፖርተር በረቡዕ እትሙ ‹‹… የኤርትራ ጦር በባድመ አንድ ትምህርት ቤትና አንድ አውቶቡስ አቃጠለ…›› የሚል ዜና ይዞ ወጥቷል፡፡
‹‹… ባለፈው እሁድ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት በባድመ ግንባር የሚገኘው የኤርትራ ጦር ኃይል በከባድ መሣርያ (ተወንጫፊ) ባደረሰው ጥቃት፣ ‹‹ባድመ ቀዳማይ ብርኪ ቤት ትምህርቲ›› (ባድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት) ሙሉ ለሙሉ በመቃጠሉ ከጥቅም ውጪ ሆኗል፡፡…››
‹‹መለስ በምስክርነት ፍርድ ቤት ሊቀርቡ ነው›› የሚል ዜና ያስነበበን ደግሞ ኢሕአዴግ ሲቀነስ መለስ ምን ይሆናል? የሚል ጥያቄ ሽፋን ገጹ ላይ ይዞ የወጣው ሰንደቅ ጋዜጣ ነው፡፡ ስለመለስ ፍርድ ቤት መቅረብ ሲዘረዝር፡-
‹‹ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ጨምሮ የቀድሞ የህወሓት አመራሮች ለምስክርነት መቐለ ከተማ ፍ/ቤት ሊጠሩ ነው፡፡ አመራሮቹ ለምስክርነት የተጠሩት የህወሓት መስራች ከነበሩት አንዱ አቶ አስገደ ገ/ስላሴ ላይ አቃቤ ሕግ የቀረበባቸውን የስም ማጥፋት ክስ ተከላከሉ በመባላቸው ነው፡፡…››
አቶ አስገደ ‹ጋሃዲሦስት› በተባለው መጽሃፋቸወ ምዕራፍ 29 ላይ የቀድሞ የህወሓት የፀጥታና ደህንነት አባልን ስም አጥፍተዋል በሚል በአቃቤ ሕግ ለቀረበባቸው ክስ ነው… መከላከያ ምስክር የጠሩት፡፡
‹‹… አቶ አስገደ በመከላከያ ምስክርነት ከጠሯቸው የመከላከያ ማስረጃዎች መካከል አቶ መለስ ዜናዊ፣ አምባሳደር ሙሉጌታ አለምሰገድ (ነዋሪነታቸው በጣሊያን) አቶ ስብሃት ነጋ፣ አቶ መኮንን (የአባታቸው ስም ለጊዜው ያልታወቀ)፣ አቶ ወልደስላሴ አብርሃ (በትግራይ የሚገኙ)፣ አቶ ሰለሞን ተስፋዬ፣ አቶ ፍሬው ተስፋሚካኤል (በደቡብ ሱዳን ጁባ የሚገኙ)፣ አቶ ገብሩ አስራት፣ አቶ አባይ ፀሃዬ፣ አቶ ስዬ አብርሃ (በአሜሪካ ሃርቫርድ ዩንቭስቲ የሚገኙ)፣ አቶ ስዩም መስፍን (ቻይና በአምባሳደርነት የሚያገለግሉ)፣ አቶ አርከበ እቁባይ፣ አቶ ኪሮስ አቡዬ፣ አቶ አክሊሉ ኪዳነማርያም (በአድማስ ኮሌጅ አዲስ አበባ የሚገኙ) እና ሦስት የመከላከያ ጄኔራሎች ይገኙበታል…››
ሰንደቅ እንደቀጠለ ነው…
‹‹የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ባለስልጣናት የኢሕአዴግ አቻዎቻቸውን አሰለጠኑ…
‹‹… አምስት አባላት ያሉት የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ዓለም አቀፍ አባላት [በአቶ ሴኮቱሬ ለሚመራው] ለኢሕአዴግ አቻቸው….በብዙኃን መገናኛ አቅም ግንባታ፣ በመገናኛ ብዙኃን ተቋማት አስተዳደርና በኢንተርኔት አስተዳደር [ቻይና] ያላትን ልምድ በስልጠናው ተመርጠው ለተገኙ የኢሕአዴግ ከፍተኛ የአመራር አባላት አካፍለዋል፡፡…
‹‹… ቻይና ፌስቡክን ጨምሮ የኢንተርኔት አገልግሎትን በማፈን (ጃም በማድረግ) በዓለምአቀፍ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅቶች ተቃውሞ የሚቀርብባት ሲሆን በሃገሪቱ የሚዲያ አፈና እና የጋዜጠኞች መብት የማይከበርበት መሆኑ በተደጋጋሚ መዘገቡ ይታወሳል፡፡››
* * *
‹የዋጋ ግሽበቱ እና የ‹‹መለኖሚክስ›› [የመለስ-ኢኮኖሚክስ] ክስረት› በሚል ርዕስ የኢኮኖሚ ምሕዳሩን ቅኝት በፍትሕ ጋዜጣ ላይ ያቀረበው ኃይለመስቀል በሸዋምየለህ ‹‹… በየሦስት አልያም አራት ቀናት ውስጥ አንዱን ምንም ምግብ እቤት ውስጥ የማይኖርበት ጊዜ የተለመደ ነው፡፡ እንዲህ ዓይነት ችግር ሲገጥመኝ ለልጆቼ ምንም የሚበላ ነገር እንደሌለ እነግራቸዋለሁ፡፡ አጋጣሚ ሆኖ የተገኘ ጊዜ ደግሞ አንዷን እንጀራ አራት ቦታ ቆርሼ፣ ትንሽ ሽሮ ፈሰስ አደርግና እንዲቃመሱ አደርጋቸዋለሁ፡፡ አሁን እግዚአብሔር ይመስገን ህፃናቱ ያለውን ችግር እየተረዱ መጥተዋል፡፡ እንደከዚህ ቀደሙ ምግብ አምጪ እያሉ አያስቸግሩኝም፡፡…›› ያሉ የኢኮኖሚው መገለጫ ንግግሮችን ከጥናቶች አሰባስቦ አቅርቧል፡፡
የፍትሕ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝም በበኩሉ ‹የጠፋው ትውልድ እና የታህሪር ናፍቆት› በሚል ርዕስ በጻፈው ጦማሩ ‹‹… የባልቻ አባት ሳፎ እንጂ አባ ነፍሶ አይደለም የሚለው ጉንጭ አልፋ ክርክር ሳይሆን ይህች ሀገር እስከመቼ ድረስ እንዲህ በግለሰቦች የተናጠል ትግል ህልውናዋ ሊጠበቅ ይችላል?...›› በማለት ምሁራኑ እንኳን ፈርተው የሸሹትን ‹‹ብቸኛ ታጋይነቱ››ን አወድሷል፡፡ ተመስገን ስለ ‹ያ ትውልድ›፣ ስለ ‹አምላጭ ትውልድ› ሐተታ ካቀረበ በኋላ ‹ታህሪር ናፋቂ› ስላለው ትውልድ ሳምንት ለመመለስ ቃል ገብቶ ተሰናብቷል፡፡
ባለፈው ሳምንት የ‹‹ቃሊቲው ምስጢሮች›› ላይ የሰላ ትችቱን የሰነዘረው ብርሃኑ ደቦጭ በዚህ ሳምንት ደግሞ ‹‹ባለቀለተ ጉዳይ ፍርድ ቤት ከመከራከር ለሕዝብ ዳኝነት አንድ መጽሐፍ መጻፍ፤ የሲሳይ አጌና መጽሐፍ አንድምታ›› በሚል ርዕስ ለዘብ ትችቱን አቅርቧል - በፍትሕ ጋዜጣ!
ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ የኤፍ.ኤም ፕሮግራሞችን በታዘቡበት የሰላ ትችታቸው ‹‹…የዛሬዎቹ ‹ታዲያስ አዲስ›፣ ‹የፍቅር ክሊኒክ›፣ … የመሳሰሉ የኤፍ.ኤም ፕሮግራሞች በየእለቱ የሚረጩት መርዝ የትውልዱን ስነምግባር ሸርሽሮ ከስሩ ነቅሎ እስከሚጥለው፣ ሀገራችን በእውቀትና በስነምግባር የታነጸ ዜጋ ማጣትዋ በግልጽ እስከሚታይ ስንት ዓመት ይፈጃል?...›› ሲሉ ‹ዘመኑ እኮ የኤፍ.ኤም ነው› በሚል ርዕስ ፍትሕ ጋዜጣ ላይ ባወጡት ጽሁፍ በምሬት ጠይቀዋል፡፡
* * *
አዲስ አድማስ ነፃ አስተያየት በተሰኘው አምዱ ‹‹የመንግስት ወከባ ከፍርሃት የማያላቅቅ የሕልም ሩጫ›› የሚል ሰፊ ሐተታ አስነብቧል፡፡ ‹‹… ዲግሪ ወይም ዲፕሎማ የያዙ ስራአጦች እየበዙ ነው፣ ቁጥራቸው በ5 ዓመት ውስጥ በ3 እጥፍ ይጨምራል፣ የትራንስፎርሜሽኑ እቅዱ 2 ዓመት ሊሞላው ነው፤ ነገር ግን በርካታ እቅዶች በተያዘላቸው ጊዜ አልተሰሩም፣ የስራ ፈላጊ ከተሜዎቹ ቁጥ በ330ሺ ይጨምራል፤ ሩብ ያህሉ ብቻ መደበኛ የስራ እድል ያገኛሉ፡፡ የገጠር ሕዝብ በየዓመቱ በ2ሚ. እየጨመረ ነው፤ የዝናብ እጥረት ሳይኖርም ከ12ሚ. በላይ ሰዎች ተረጂ ናቸው…›› እያለ የመንግስት እቅድንና አፈፃፀምን ይተቻል፡:
‹‹.. ይድረስ
ለወዳጄ፡-
እንደምን ሰንብተሃል እኛ ባለንበት እግዚአብሄር ቸርነት ደህና ነን፤ መቼም ወቅት ፈቅዶ ለብዙ ትውልዶች ያህል ተራርቀን ብንኖርም ያገሬ ታሪክ የጀግኖች ታሪክ መቼም አይዘነጋም ብዬም አልነበር… እናም ይሄውልህ በእናንተው ዘመን ደግሞ ብላቴናው ቴዎድሮስ ካሳሁን ‹‹ጥቁር ሰው›› ብሎ ታሪካችንን ብድግ አደረገዋ!
እንግዲህ ምን ትላለህ? ከሆነልህማ የፊታችን ማክሰኞ ከአመሻሹ 12 ሰዓት ላይ ከቤተመንግሥታችን ዝቅ ብሎ ከሚገኘው ሂልተን ውቴል ብቅ በልና ጠበል ፀዲቅ ቅመስ፤ ስናወጋ እናመሻለን
አደራ እንዳትቀር
ያልመጣህ እንደሆነ ግን ማርያምን እቀየምሃለሁ፡፡
ዳግማዊ አጤ ምኒልክ ግንቦት 28/2004 ዓ.ም. ›› - የቴዲ አፍሮ ‹ጥቁር ሰው› ሙዚቃ ቪዲዮን ለማስመረቅ የተዘጋጀው የጥሪ ወረቀት ላይ የተጻፈ ጽሁፍ (አዲስ አድማስ)
* * *
ነጋድራስ ጋዜጣ ‹‹በጽንፈኝነት የተቃኘች ሃገር›› በሚል በደሳለኝ ስዩም ባቀረበው ሰፊ ሐተታ ሃይማኖተኞችን፣ የገዢው ፓርቲንና ወገኖችን፣ ተቃዋሚዎችን፣ ጋዜጦችንና ፕ/ር መስፍንን ሳይቀር በማስረጃ እያስደገፈ ተችቷል፡፡ ከጽሁፉ ጥቂት ለመጨለፍ ያክል፡- ‹‹…በመገናኛ ብዙሃን ኢንዱስትሪ ውስጥ መካከለኛ ማግኘት ከባድ ነው፡፡ ጭልጥ ያሉ የአብዮታዊ ዴሞክራሲ እና የኢሕአዴግ አቀንቃኝ የሆኑ የመንግስት ብዙሐን መገናኛዎች እና ጭልጥ ብለው ምንነቱ ያልታወቀ የተቃውሞ እንቅስቃሴ የሚደግፉ /ኢሕአዴግን በመጥላት ላይ ብቻ የተመሰረቱ/ ብዙሐን መገናኛዎች በየራሳቸው ጽንፍ ላይ ቆመዋል፡፡…››
የጋዜጦቹ ርዕሰ አንቀጽ
- የምሁራን ዝምታ ይሰበር - ፍኖተ ነፃነት
- ‹‹ጎፈሬ አበጣሪው›› ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር - የኛ ፕሬስ
- ዘመናዊውን የህፃናት ንግድ ማስቆም የሁሉም ኃላፊነት ይሁን - መሰናዘሪያ
- የሠራተኛ ጉልበት እንሸጣለን ብለን የዜጎችን ማንነትና ክብር እንዳንሸጥ እንጠንቀቅ - ሪፖርተር (ረቡዕ)
- በጀት መዝጊያ ነው በሚል በግዥ ስም የመንግስትና የሕዝብ ገንዘብ መመዝበር ይቁም - ሰንደቅ
- መንግስት የሰብዓዊ መብት አያያዙን ያስተካክል! - ፍትሕ
- ሞኝ የተቆረጠ እሸት ይጠብቃል - አዲስ አድማስ
- ጥይት የማይጮህባት ኢትዮጵያን እንፈልጋለን! - ነጋድራስ
- ‹‹የአባትህ ቤት ሲበዘበዝ…i›› - ኢትዮ ቻናል
ሌላም፣ ሌላም
- በአዲስ አበባ በቤተ-ክርስቲያን ይዞታ በተቀሰቀሰ ግጭት የሁለት ሰው ህይወት አለፈ፡፡ - ፍትሕ
- በጋዜጠኛ ርዕዮት ላይ የይግባኝ አቤቱታ ክርክር ሊጀመር ቀጠሮ ተያዘ - ፍትሕ
- አቶ አስገደ ‹‹የመከላከያ ምስክሮቼን ለማሰማት ከፍተኛ የገንዘብ ችግር ገጠመኝ›› አሉ - ፍትሕ
- ‹‹ገመና ድራማ ተተራመሰ፤ ተፈሪ አለሙና መሰረት መብራቴ ጀማነሽ ሰለሞንን ተከትለው ራሳቸውን አገለሉ›› - የኛ ፕሬስ
- ጋዜጠኛ አበበ ገላው በደጋፊዎችና ተቃዋሚዎች አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል - አዲስ አድማስ
- ‹‹ስለ ካሴቱና ስለፕሮግራሙ የምሰጠው አስተያየት ባይኖረኝም ክሊፑ በጣም አሪፍ ነው፤ የሠሩት ልጆች መመስገን አለባቸው፡፡›› - የፊልም ባለሙያ ቴዎድሮስ ተሾመ (አዲስ አድማስ)
ቀልድ
‹‹ማርሻል ቲቶ የዩጎዝላቪያ መሪ በነበሩበት ጊዜ ነው አሉ፡፡ ቲቶ የደህንነት ሚኒስትራቸው ራንኮቪክን አስከትለው በከተማዋ ጉብኝት ያድረጋሉ (የሥራ ልትሉት ትችላላችሁ፡፡) መጀመሪያ ወደ አንድ ወላጅ አልባ ህፃናቱ ያሉበትን ሁኔታ ለማሻሻል በሚል 10ሺ ዲናር ይለግሳሉ - ቲቶ፡፡ በመቀጠል ጋብቻ ሳይመሰርቱ የወለዱ እናቶች መጠላያ ይሄዱና 15ሺ ዲናር ይሰጣሉ - የእናቶቹንና የህፃናቶቻቸውን የአኗኗር ሁኔታ ለማሻሻል በሚል፡፡ የቲቶ ቀጣይ ጉብኝት ወህኒ ቤት ነበር፡፡ እዚያ ደግሞ 80ሺ ዲናር ሰጡ - የእስረኞች አያያዝ እንዲሻሻል በማዘዝ፡፡…. ቲቶ ለወህኒ ቤቱ ባደረጉት የበዛ ልግስና የተገረሙት የደህንነት ሚኒስትራቸው፤ ‹ለምንድን ነው የእስረኞች አያያዝ እንዲሻሻል ያን ሁሉ ገንዘብ የሰጠኸው?› ሲሉ ይጠይቋቸዋል፡፡ ቲቶም ሲመልሱ፤ ‹ክፉ ቀን ቢመጣ እኔና አንተ ማረፊያችን የት ይመስልሃል? የህፃናት ማሳደጊያ ተቋም፣ የእናቶች መጠለያ ወይስ ወህኒ ቤት?››› በማለት የጻፈው በብዕር ስሙ ኤሊያስ የአዲስ አድማስ ‹ፖለቲካ በፈገግታ› አምደኛ ነው፡፡ በጽሁፉ ‹‹…አዲስ አዋጅም በሉት መመሪያ ሲወጣ ከዕለታት አንድ ቀን እኔም ላይ ተፈጻሚ ሊሆን ይችላል ብሎ ማሰብ ቢቀር እንኳን መጠርጠር ክፋት የለውም…›› ብሏል፡፡
በመጨረሻም ስፖርት
‹‹በበርካታ የአፍሪካ ዋንጫ ውድድሮች ባለመሳተፏ የተረሳችው ኢትዮጵያ በዘንድሮው የ2012 የአውሮፓ ዋንጫ ስሟ የሚጠራበት አጋጣሚ ተፈጥሯል፡፡ በመጪው አርብ ሰኔ 1 ቀን 2004 በሚጀመረውና ፖላንድ እና ዩክሬን በሚያስተናግዱት የአውሮፓ ዋንጫ ለቼክ ሪፐብሊክ ብሔራዊ ቡድን ከሚሰለፈው ቴዎዶር ገብረስላሴ ጋር ኢትዮጵያም መጠራቷ አይቀርም፡፡…›› - ሰንደቅ፡፡
Saturday, June 9, 2012
“የቃሊቲው መንግስት” እኔ እንዳነበብኩት
ርዕስ - የቃሊቲው መንግስት
ዝግጅት ፣ጥንቅር ፣ ጸሐፊ - ሲሳይ አጌና
የገጽ ብዛት - 443
አሳታሚ - Netsanet publishing and distributing agency
ዋጋውና እና የት እንደታተመ አይገልጽም
Friday, June 8, 2012
የሁለት ‘ሚኒስትሮች’ ወግ
እኛም ከዚህ ትርጉም ውስጥ ‹‹የተደረገውን ታሪክ ማውጋት መተረክ›› የሚለውን ተከትለን የሁለት መሪዎችን/ጠቅላዮችን ጨዋታ እንጨዋወታለን፡፡
Twitter በተባለው የማህበራዊ ድረ ገፅ አስከ ፈረንጆቹ 2012 ድረስ ከ 140 ሚሊየን በላይ ግለሰቦች ተመዝግበው ስለተለያዩ ጉዳዮች ሃሳባቸውን ያካፍላሉ በተከታዮቻቸውም (Followers) ምላሽ እና አስተያየት ያገኛሉ እነርሱም የፈለጉትን ሰው መከተል (Follow) ይችላሉ፡፡
ከነዚህ መራጆቸ (Twitterati) መካከልም ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ Twitterን የተቀላቀሉት ከ3 ዓመት በፊት ማለትም April 9/2009 እንደሆነ የTwitter ታሪካቸው ያስረዳል፡፡ በመጀመሪያ ያደረጉት Tweetም “Just had some of my favorite Shiro. Thank You Chef” የሚል ሲሆን፡፡ ይህችም Tweet በተለያዩ ግለሰቦችም ዘንድ የተለያየ አንድምታ የምትፈጥር ሆናለች፡፡
Thursday, June 7, 2012
ልማታዊ ጋዜጠኛነት ወይስ ይሁንታን ማምረት?
የነዚህ ሁለት ወጣቶች አቋም የነሱ ብቻ አቋም አድርጌ አልመለከተውም:: የመንግስትም አቋም እንደሆነ አምናለሁ:: አለመታደል ሆኖ እንጂ መንግስት ለዲሞክራሲ መጎልበት እንዲህ መሰረታዊ ፋይዳቸው ላቅ ያሉ ጉዳዮችን አደባባይ አውጥቶ ሕዝባዊና ምሁራዊ ክርክሮች እንዲካሄዱ ከመፍቀድም አልፎ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ነበረበት ግን አልሆነለትም፤ ወደ ምክንያቶቹ አልሄድም የጽሁፌ ትኩረት አይደለምና። የግል መገናኛ ብዙሃንም ቢሆኑ ጥቂቱ በሀገር ውስጥ ግማሹ ከሀገር ውጪ በመሆን እንዲህ ያለውን ጉዳይ በተንጠባጠበ እና አልፎ አልፎ በሚነሳ የአምድ ማሟያነት ከክርክር ባለፈ ጉዳዩን በጥልቀት በመመርመር የፖሊሲ አቅጣጫዎችን ለመጠቆም በሰፊው ለመስራት በሞከሩ ነበር: ምንም እንኳ የእስካሁኑ ሙከራቸው ቢያስመሰግናቸውም፡፡
በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ እየተተገበረ ያለው ልማታዊ ጋዜጠኝነት ነው/አይደለም የሚለው ክርክር በልማታዊ ጋዜጠኝነት ኀልዮቶች ላይ የተንጠለጠለ መሆን የለበትም:: በእርግጥ የ”ልማታዊ” ጋዜጠኝነት ኀልዮቶችን ፋይዳ እና መገለጫዎቹን የ”ልማታዊ” ጋዜጠኞችን ስነ ምግባር እና ሌሎችንም ከርዕሰ ጉዳዩ ጋር ቅርበት ያላቸውን ዝርዝር ጉዳዮች በሙሉ መነጋገርም መወያየትም ተገቢ ነው:: ነገር ግን ይህን የመሰለ ሀገራዊ አብይ ጉዳይ በኀልዮት ደረጃ ብቻ ተወያይቶ ወይም “ምናምን” ብሮድካስት ኮርፖሬሽን፤ በሚባለው ራድዮ ጣቢያ አንዳንድ ፕሮግራሞች ላይ ምንትስ ስለሚባል ሰፈር ወጣቶች ድህነትትን ለመዋጋት በማህበር ስለመደራጀታቸው ሰምቻለሁ:: ምንትስ በሚባለው FM ራድዮ ዜጎች ያለ ፍርሃት በስነተዋልዶ ጤና ሲወያዩ ሰምቻለሁ፣ አይቻለሁ፤ ስለዚህ በኢትዮጵያ ውስጥ እየተተገበረ ያለው ልማታዊ ጋዜጠኝነት ነው ብሎ አፍን ሞልቶ ማውራት ይችላል ለሚሉ ባልዳረባዎቼ እኔ ልላቸው የምችለው ነገር ቢኖር እነዚህ የክርክር ነጥቦች የየዋህነት አልያም የጅልነት ወይም ደግሞ አውቆ የተኛ ዓይነት የመከራከሪያ ነጥቦች ናቸው:: ምክኒያቱም ልማታዊ ጋዜጠኝነት በኀልዮት ደረጃ እንኳ በቅጡ ያልተደላደለ ወጥ የሆነ የጋዜጠኝነት ስነ ምግባር የሌለው ከምዕራባዊያን የጋዜጠኝነት ባህል እንኳ በምን እንደሚለይ ጥርት ባለ ሁናቴ ሳይታወቅ፥ በኢትዮጵያ ውስጥ እየተተገበረ ያለው ልማታዊ ጋዜጠኝነት ነው ብሎ በችኮላ ከመደንገግ በፊት የሀገራችንን የሚዲያ መልክዐ ምድር(Media Landscape)፣ ህጋዊ ዳራቸውን እና ጋዜጠኞቻችን ሙያቸውን እየተገበሩ ያሉበትን አውድ በሚገባ ዘርዘር አድርጎ ማየቱ ይቀድማል ብዬ ስለማምን ነው:: ከዚህም ባሻገር የመገናኛ ብዙሃን የሥራ ባህል እና የጋዜጠኝነት ልምድ ትንተና ባንድ አገር ውስጥ ካላቸው ተጨባጭ ኹኔታ ነው መጀመር ያለበት። እስቲ ተጨባጩን የአገራችንን የመገናኛ ብዙሐን የሥራ ባህል እና የጋዜጠኝነትን ስራ አንኳር ነጥቦች በወፍ በረር እንቃኛቸው፦
የኢቴቪ ልማታዊነት ሲጠየቅ
Tuesday, June 5, 2012
ነፃነት እና ዳቦ
በነፃነት ሃሳብን የመግለፅ (ወይም የሌላ አይነት ነፃነት) እጦት እራሱን ከሚያሳይባቸው መንገዶች አንዱና ዋነኛው ዜጎች በሀገራቸው ጉዳይ ላይ ንቁ ተሳታፊ መሆን የሚያስከፍላቸው ዋጋ ከፍተኛ እንደሆነ ተገንዝበው፥ ግላዊ የሆነ ጭቆና እስካላጋጠማቸው ድረስ የተፈቀደላቸውን ብቻ እየተናገሩ/እየፃፉ/እያደረጉ ተቆጥበው መኖርን መምረጣቸው ነው፡፡
አከራካሪውን የቅደም ተከተል ጉዳይ ወደ ጎን ትተን ነፃነትንና ብልፅግና ሁለቱም እንደሚያስፈልጉን ግልፅ ነው፡፡ የነፃነት ጫፍ የተረጋገጥባት ነገር ግን ሰዎች ከዕለት ጉርሻ እጦት በየዕለቱ የሚረግፉባት ሀገር እንዲኖረን የማንመኘውን ያክል ዜጎች ችጋር የሚባል ነገር ሲነገር ብቻ የሚሰሙባት ነገር ግን መንግስት የሚናገሩትን፣ መስራት የሚችሉትን ወይንም ለአጠቃላይ እንቅስቃሴያቸው ልኬት አበጅቶ ጥሩ ከሚቀለብ የቤት እንስሳ የማይለዩበት ሀገር እንዲኖረን ፈዕሞ አንፈልግም፡፡
መጀመሪያ ራሴን ልቻል ወይስ መጀመሪያ ራሴን ልሁን?
Monday, June 4, 2012
በአገሩ ጉዳይ የሚያገባው ትውልድ ፍለጋ
‹‹የአሁን እኛ?››
በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት ምሽቶችን የሚያደምቁ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጫወታዎን የሚታደሙ፣ ከዚያም አልፈው ጎራ ለይተው የሚሰዳደቡና የሚወቃቀሱ፣ የባሰ ዕለት ደግሞ በትልልቅ ጫወታዎች መልክ ጎራ ለይተው የሚቧቀሱ ወጣቶችን ማየት የከረመ አገራዊ ትዕይንት ሆኗል፡፡ ቅጥ ባጣ የፈረንጅ እግር ኳስ ፍቅር፣ ‹‹ከብርሃን ፍጥነት›› በላይ እየተስፋፉ ባሉ ‹‹የሱስ መሰረተ ልማቶች›› ውስጥ በመጥፋትና በቸልተኝነት የሚታማው ይህ ትውልድ ከላይ በተጠቀሱ ‹‹አደንዛዥ›› ጉዳዮች ተጠልፎ ካልወደቀም በጥልቅ ‹‹ራስን የማዳን›› ስሜት በመዋጥ አገሩን የረሳ፣ ፖለቲካ የማይገደው፣ ምርጫ የማያሳስበው ትውልድ ነው ተብሎ ይታማል፤ አለፍ ሲልም ደግሞ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በስደት ወደተገኘው አገር ለመጓዝ ልቡ የቆመ፣ በአገሩ ተስፋ የቆረጠ፣ በየትኛውም አጋጣሚ አገር ጥሎ ለመሄድ ጓዙን ጠቅልሎ የተሰናዳ ወጣት እንዴት አገርን ይረከባል? ሊረከብስ ቢዘጋጅ ከማን እና እንዴት ይረከባል? ይህችን አገር ከእኛ የሚወስዳት ማነው የሚሉ ‹‹አባቶችም›› መኖር ሌላው ነባራዊ ሐቅ ነው፡፡
ለዚህ ዓይነቱን ትውልድ መፈጠር (ዓይነቱ ይሄ አይደለም ብለው የሚከራከሩ ባይጠፉም) ኃላፊነት የማይወስዱበት ‹‹የጎረቤት ልጅ›› ይመስል እዚህ ለመድረሱ ኃላፊነትን አንወስድም ዓይነት አንድምታ ያላቸውን ሐሳቦች መስማት አዲስ ነገር አይደለም፡፡ እንደውም አልፈው፣ ተርፈው ‹‹በእኛ ዘመን ቀረ!››ን ልክ እንደ አንድ የታሪክ ኩራት መገለጫ ያደረጉና ትውልዳዊ ኃላፊነታቸውን የረሱ ፖለቲከኞች ስለምክንያቱ ከማውራት ይልቅ ውጤቱን መውቀስ ይቀናቸዋል፡፡
ለምን? ለምን? ለምን?