Saturday, May 28, 2016

የግንቦት 20 ፍሬዎች




ቤተል ፋንታሁን የ25 ዓመት ወጣት ስትሆን፣ በኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ዘመን ተወልዳ ያደገች ነች፡፡ በሌላ አነጋገር አንዳንዶቹ ‘The EPRDF Generation’ የሚሉት ትውልድ አባል ናት፡፡ ቤተል ብቻ ሳትሆን ስልሳ አምስት በመቶው የኢትዮጵያ ሕዝብ ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ሥልጣን ከያዘበት ጊዜ ወዲህ የተወለዱ ሲሆን፣ ይሄም ከአገሪቱ አጠቃላይ ሕዝብ ሁለት ሦስተኛውን ይሸፍናል፡፡ ቤተል በዚህ ዕድሜዋ “እውነተኛው የግንቦት 20 ፍሬ ግንቦት 7 ብቻ ነው፤ ሌላው ሁሉ ግንቦት 20 ቢኖርም ባይኖርም መኖሩ አይቀርም” ትለናለች፡፡ አንብቧት፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ)ን 6 ወራት ዕድሜ አንሰዋለሁ፤
ድንገት ቸኩሎ ገብቶ ነው እንጂ ይደርስብኝ ነበር። እኔ ተረግዤ  የጎተራው ሼል ይሁን ተቀጣጣይ ነገር (ግንቦት 27፣ 1983) ፈንድቶ ሕዝቤ ሸሽቶ እኛ ሰፈር መጣ አሉ፡፡ ታዲያ አንዳንዶች ሲያሾፉብንየዛኔ ጥለውሽ ነው ያገኘንሽ ብለው ያወራሉ”፡፡ የኛን ሰፈር እወደዋለሁ፡፡ ግንቦት 20 ከሚባለው 2 ደረጃ ትምህርት ቤት ውጪ ኢሕአዴግ ለኛ ሰፈር ያደረገው ነገር የለም፡፡  ምህርት ቤቱም፣ ሰፈሩም በ97 ምርጫ ማግስት በተያዘብን ቂም ምክንያት 50 ዓመታት በላይ ያሳለፈ ሰፈር ባለፈው ዓመት ነውኮብልሰቶን› የገባበት፡፡ እንዲያውም ከአንዳንድ ሰዎች ጋር ተማክሬ UNESCO ላይ ለስመዘግበው ስል ለጥቂት ነው የቀደሙኝ። እሱ ይገርማችሁዋል፡፡ የቀድሞው የኢሕአዴግ ጠቅላይ ሚኒስትርየመረሸ› ጊዜ እንኳን ብቸኛው ድንኳን ያልተጣለበት ሰፈር ነው፤ የኛ ሰፈር፡፡ ይሄን ሰማን ብለው ደግሞ የያኔውን ዛሬ እንዳይመጡ።ኢትዮጵያ ውስጥ ነው ወይ?” ትሉኝ ይሆናል፡፡ አዎ እዚሁ አዲስ አበባ፡፡

የግንቦት 20 ፍሬ፡ 1

ምርጫ ‘97, ‘02, ‘07

1997 - እንደዛኔ 18 ዓመቴ እንዲሆን የተመኘሁበት ጊዜ የለም:: የዛኔ 8 ክፍል ሚኒስትሪ ተፈታኝ ነበርኩ:: በላያችን ላይ የተኩስ እሩምታ ሲወርድአንፈተንም› ብለን ፈተናው 30 ደቂቃ ዘገየ። እንዲህ እንዲህ እያልን 1998 ላይ ሁለቴ ምህርት ቤቱን አዘጋነው፡፡ በሁለተኛው በፌደራል ተገረፍን፡፡ ሰፈሬን የምወድበት አንዱ ምክንያት የሰፈሬ ልጆች ያኔ ‹ልጆቹን አናስነካም› ብለው ለፖሊሶቹ መንገድ መዝጋታቸውን ሳስበው ነው፡፡ የዛኔ ቤት ሲፈተሽ ኮርኒስ አልቀራቸውም።ወንድ አይትረፍ› የተባለ ይመስል የሰፈሬ ወንዶች ሁሉ ተለቅመው እስር ቤት ገቡ። 2002 ሞራላችን ዝቅ አለ፤ አሽቆለቆለ ሁለት ጣት የልለ፣ አምስት ጣት የለ፡፡ 2007 መቶ ፐርሰንት በልሉን፡፡ ለነገሩ ምርጫ አልነበረም ማለት ነው እኮ፡፡ ፓርላማው ውስጥ  ራሱ ምን እንደሚያደርጉ አላውቅም ልላችሁ ነበር፤ ግን ሳስታውሰው ለካስቤርጎ› ሆኗል፡፡ ዕድሜ ለፌስቡክ ይሁን።

የግንቦት 20 ፍሬ፡ 2

“አንድ ፓርቲ ገዢ ሆኖ አገር ሲመራ ማድረግ ያለባቸው 10 ነጥቦችብዬ ለመዘርዘር አሰብኩና 10 ነጥቦችን ደረደርኩ ለካስ ብዙ ነገር ተደርጎልናል መንገድ፣ ኮንዶሚንየም (ሊያውም ምትሃተኛ)፣ ባቡር ከነመንገዱ:: ግን መንግሥት ይህን ካልሠራ ታዲያ ምን ሊያደርግ ነው? መቼም ከኔ ጋር ቁጭ ብሎቃና› ቴሌቪዥንን አያይ። መንገድ ተሠራ እልልታ፡፡ ቤት ተሠራ እልልታ፡፡ ቆይ ልጠይቃችሁ አለቃ ወይ አስተማሪ አላችሁ እንበል፣ የሆነ ሥራ ተሰጣችሁ፣ ካልሠራችሁ ትባረራላችሁ፡፡ አለቀ በቃ፡፡ ኢሕአዴግም እንዳናባርረው ነው የሚሠራው እሱንም ሠራ ከተባለ (ሽርሽር እንሂድ ብለው ጓሮ እንደሚያዞሩት ሕፃን) የምር ለኛ አስቦ የሚመስለው ሰው ካለ እንተዋወቅ።

‹የሥልጣን ባለጌ› ያሳደገው የእኔ ትውልድ


ዮሴፍ መርጉ የ25 ዓመት ወጣት ሲሆን፤ በኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ዘመን ተወልዶ ያደገ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር አንዳንዶቹ ‘The EPRDF Generation’ የሚሉት ትውልድ አባል ነው፡፡ ዮሴፍ ብቻ ሳይሆን ስልሳ አምስት በመቶው የኢትዮጵያ ሕዝብ ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ሥልጣን ከያዘበት ጊዜ ወዲህ የተወለደ ሲሆን፤ ይሄም ከአገሪቱ አጠቃላይ ሕዝብ ሁለት ሦስተኛውን ይሸፍናል፡፡ ዮሴፍ “ከዚህ በኋላ በኢሕአዴግ ተስፋ ማድረግ፤ በራሱ ተስፋ መቁረጥ እንደሆነ አድርጌ እወስደዋለሁ” በማለት መፍትሔ ይሆናል የሚለውን ሐሳብ ይሰነዝራል፡፡ አንብቡት፡፡

ከ1996 አንስቶ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ከስድስተኛ ክፍል ጀምሮ መሰጠት የጀመረው ‹የሥነ-ዜጋ›
ትምህርት በፖለቲካ ንቃቴ ላይ በቀላሉ የማይገመት አስተዋፅዖ አድርጓል፡፡ በአጋጣሚ ይሁን ሆን ተብሎ ባላውቅም መምህራኑ ሥነ-ዜጋንና የታሪክ ነክ ትምህርቶችን ደርበው እንዲይዙ በመደረጉ በመንግሥትና አስተዳደር ግንዛቤዬ ላይ ደማቅ አሻራን አሳርፏል፡፡ እንዲህ፣ እንዲህ እያለ እየዳበረ የመጣው የፖለቲካ ግንዛቤዬ ከፍ እያልኩኝ ስመጣ በተለያዩ መጽሐፍት ታግዞ፤ ብሎም የበይነ-መረብ እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ መናኘቱ ስሜቴን በአደባባይ የመግለጽ ድፍረቱንና አጋጣሚውን ፈጠረልኝ:: ብዙም ነገር እንዳውቅም ሆንኩኝ፡፡

1983 እኔ የተወለድኩበት ዓመት ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ.) ወደ ሥልጣን የመጣውም በዚሁ ዓመት ነው:: ዘንድሮ በ2008 የብር ኢዮቤልዩውን የሚያከብረው የኢሕአዴግ መንግሥት፣ የእሱን መንግሥት ብቻ በማውቀው በኔ እንዴት ይታያል የሚለውን እስኪ እንመልከት::

ማወቅ ዕዳ ነው። አንድ ሰው በማወቁ የተለያዩ የስሜት ፈረቃዎችን ለማስተናገድ ይገደዳል። በትውልድ ዘመኔ አንድ መንግሥት ብቻ ማየቴና በአንጻሩ ደግሞ የምዕራቡ ዓለም በነጻ ምርጫ የተለያዩ መንሥታትን ማየት መቻላቸው የፈጠረውን ነገር ማወቄ የተለያዩ ስሜቶችን ሰጥቶኛል። አንድ መንግሥት ያለገደብ በሥልጣን ላይ መቆየቱ ‹የሥልጣን መባለግን› ከመፍጠር ውጭ ለአገሪቱ የሚፈጥረው ነገር የለም። ይህንንም ለማረጋገጥ አፍሪካን ለረጅም ጊዜ ያስተዳደሩና እያስተዳደሩ ያሉ መንግሥታትን ማየት ብቻ ብቂ ነው። በሌላ መልኩ ደግሞ የምዕራቡ ዓለም አገራት ነጻና ፍትሐዊ ምርጫ በማካሔድ ባሻቸው ጊዜ የፈለጉትን መንግሥት መቀያያር ይችላሉ፡፡። በውጤቱም አንዱ መንግሥት የሰነፈበትን ተተኪው መንግሥት እየሠራ እንዲያልፍ፤ ይህም ብቻ አይደለም ተተክቶ ያለፈው መንግሥት የጎበዘበትን አዲሱ መንግሥት በተሻለ ሁኔታ በማስቀጠል አልፏል። እያለፈም ነው።

ይህንንና መሰል ሁነቶችን ሳስብ በትውልድ ዘመኔ አንድ መንግሥት ብቻ ማየቴ እኔም እንደ ዜጋ፤ አገሬም እንደ አገር የተለያዩ መንግሥታት፤ የተለያዩ ክኅሎቶችን የማጣጣም ዕድል ማጣት ከሚፈጥረው ቁጭት ጋር ጭምር ነው፡፡ የኔም ትውልድ ፖለቲካን በፍላጎት ሳይሆን በቁጭት የሚገባበት ረመጥ ሆኖበታል:: እዚህ ድምዳሜ ላይ ያደረሱኝን የታሪክ አጋጣሚዎች እንመልከት::

በ1990 የኤርትራ መንግሥት የኢትዮጵያን ድንበር አልፎ መግባቱን ተከትሎ ‹ለኤርትራ መንግሥት ምን ዓይነት የአፀፋ ምላሽ ይሰጥ?› በሚለው ላይ የሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕ.ወ.ሓ.ት) ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት በሁለት ጎራ በመሆን የተለያየ አቋም ይይዛሉ:: ይኽም የአቋም ልዩነት በስየ አብርሃና በመለስ ዜናዊ በኩል የጎላ ከመሆኑም ባሻገር የእርስበርስ መተማመን ላይ የማይናቅ ጥላሸትን ፈጠረ:: ጊዜ ሊያስታርቀው ያልቻለው የሁለቱ ግለሰቦች መቃቃር ፓርቲውን ለሁለት መሰንጠቅ የዳረገው ሲሆን፤ በሽኩቻው መጨረሻም ‹የነስየ ቡድን› የፓርላማ አባልነት በዚያውም ያለመከሰስ መብታቸውን በመንጠቅ ተጠናቀቀ:: ይኽም አልበቃ ብሎ “ስየ አይተኛልኝ” ብሎ ያሰበው መለስ እነስየ ከፓርላማ በተሰናበቱ በአራተኛ ቀን “ስየን እግር ተወርች ያስርልኛል” ያለውን የሙስና ‹ካርድ› በመምዘዝ ያለበቂ ማስረጃ ዘብጥያ እንዲወርድ አድርጎታል:: ከዛ በኋላም ባለው የፓርቲው አባላት መጠየቅ ሲጀምሩና የሐሳብ ልዩነት ሲያሳዩ ይኸው የሙስና ‹ካርድ› እየተመዘዘባቸው ለእሥር ሲዳረጉ ተመልክተናል:: ይኽም የታሪክ አጋጣሚ በፓርቲው ውስጥ አዳዲስ ሐሳቦችን ማስተናገድ እንዳይቻልና ዴሞክራሲም ከውስጥ ይመነጫል ተብሎ እንዳይታሰብ አድርጓል:: ፓርቲው የውስጥ ቅራኔዎች የሚፈታበት አግባብ ከውጪ ሆኖ ለተመለከተው፤ ፓርቲውን መቀላቀል ማለት በዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት ከመጠርነፍ ባለፈ አዲስ ሐሳብ ማመንጨት መቻል እንዳልሆነ ይረዳል::

“በአንድ ስርዓት ሥር ይህን ያህል ጊዜ መቆየት እጅግ ያንገበግባል”


ወይንሸት ሞላ የ25 ዓመት ወጣት ስትሆን፤ በኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ ዘመን ተወልዳ አድጋለች፡፡ በሌላ አነጋገር ወይንሸት አንዳንዶቹ ‘The EPRDF Generation’ የሚሉት ትውልድ አባል ነች፡፡ ወይንሸት ብቻ ሳትሆን ስልሳ አምስት በመቶው የኢትዮጵያ ሕዝብ ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ ሥልጣን ከያዘበት ጊዜ ወዲህ የተወለደ ሲሆን፤ ይሄም ከአገሪቱ አጠቃላይ ሕዝብ ሁለት ሦስተኛውን ይሸፍናል፡፡ ወይንሸት በዚህ ዕድሜዋ በሥልጣን ላይ ያለውን ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግን በዜጎች ላይ ግፍ ሲፈጽም አይቼ ዝም ብዮ አልቀመጥም በማለት የፖለቲካ ትግሉን ተቀላቅላ ለዛም ብዙ ዋጋ እንደከፈለች/እየከፈለች እንዳለች በመግለጽ “‹ዴሞክራሲ በዚህ አምባገነን  ስርዓት ሰፍኖ፣ አገሬ እንደ አገር ሉዓላዊነቷ ተከብሮ፣ ሕዝቧ የተሻለ ኑሮ ካላቸው አገሮች ተርታ ተመድባ አያለሁ› የሚል ተስፋ የለኝም”  ትላለች፡፡ እነሆ አንብቧት፡፡


ዛሬ ግንቦት 20፣ 2008 የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕ.ወ.ሓ.ት.)/ወያኔ ሠራዊት በረሃ
የወለደውን ብሶት ይዞ ቤተ መንግሥት የገባበትና ሕ.ወ.ሓ.ት. መራሹ የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ.) መንግሥት ወደሥልጣን መንበሩ የወጣበት 25ኛ ዓመት የብር እዮቤልዩ ‹በዓል› ያከብራል፡፡ ይህ ‹የድል በዓል› በኢትዮጵያ ከሚከበሩት ሕዝባዊ በዓላት ዝርዝር ውስጥ የሚገኝ ቢሆንም፤ እንደኔ ‹በዓሉ› በምንም መመዘኛ ሕዝብ የማይስማማበት ሲሆን፤ ገዥዉ ቡድን ግን  በአንድ በኩል “ግንቦት 20 ዴሞክራሲ የተወለደበት ቀን” በሌላ በኩል ደግሞ “ደርግ የወደቀበት ቀን” እያለ የፕሮፓጋንዳ ማጣፈጫ አድርጎታል፡፡ እውነታው ግን ባሳለፍናቸው 25 ዓመታት በዘርና በጥቅም የሰከሩ የገዥው መንግሥት ምንደኞች እንደ ‹በዓል› ለማክበር ሲንደፋደፉ ከማየታችን ውጭ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደ ‹በዓል› ሳይሆን የባርነት ቀን የተከናነበበት አድርጎ የሚያየው ቀን እንደሆነ ይሰማኛል፡፡

ዕለቱን ገዥው ቡድን ሥልጣኑን ለማራዘም የሚጠቀምበት ‹የፕሮፓጋንዳ ጡሩንባ› ሲሆን ሕዝብ ደግሞ ገዥው ቡድን በሚከተላቸው የተበላሹ ፖሊሲዎች የተሠሩበትን በደሎችና ግፎች የሚያስታውስበትና እንደ አገር የተጋረጡበትን ችግሮች የሚያስብበት ነው፡፡ ለብዙ ሺሕ ዓመታት ታፍራና ተከብራ የኖረች ሀገራችን ሉዓላዊነቷ የተደፈረበትና  እንደ ሕዝብ  የደረሱብንን የዘር ጭፍጨፋዎች፤ አስከፊ በሆነው ድህነት፤ ስደት፤ ረኀብ፤ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና ለሰሚም በሚከብዱ የብዙኃን እንባዎች እንዲፈስ መነሻ የሆነ ዕለት በመሆኑ በምንም መመዘኛ የሕዝባዊ በዓል መሥፈርት የማያሟላ ቢሆንም በገዢው መንግሥት የፕሮፓጋንዳ ሚድያዎችና የሕዝብን ንብረት ያለከልካይ በሚያጠፉ ካድሬዎች ተከብሮ ይውላል፡፡

እኔ ተወልጀ ያደኩት በዘመነ ሕወሓት/ኢሕአዴግ ሲሆን፤ በሕይወቴም ከአንድ የፖለቲካ ሥርዓት ውጭም አላውቅም፡፡ ትምህርቴን የተማርኩት በዚህ ስርዓት የትምህርት ፖሊሲ ሲሆን፤ ለ‹አቅመ ፖለቲካ› ደርሼ ማሰብ በቻልኩበት ጊዜ ሁሉ ሕወሓት/ኢሕአዴግ ወጣትነቴን ነጥቆ ዜጎች እጅግ በጣም በሚያስደነግጥ የትምህርት ፖሊሲ በፍላጎታቸው እና በክኅሎታቸው ሳይሆን በዕጣ እንዲማሩ በተደረገበት የትምርት ፖሊሲ ትውልዱን ጉድጓድ ቆፍረው ሲቀብሩ እና በዚህ ውጤት በየዓረብ አገራት እህቶቼ የቁም ሞት መሞትና በየበረሀው ወድቆ መቅረት እና በሱስ መደንዘዝ እንዲሁም በአስከፊ ድህነት ውስጥ መኖር  የዚሀ ትውልድ ዕጣ ሆኗል፡፡ በአንፃሩ ከዚህ አስከፊ ስርዓት ለመውጣት የሚፍጨረጨሩ ወጣቶችን ደግሞ የአፈና ሕግ እያወጣ አፍኖ እና በጉልበት አንበርክኮ ይገዛል፣ በሌላ በኩል ደግሞ “ለዜጎች መሠረታዊ የፖለቲካ መብቶች ተከብረዋል” እያለ፤ በተቃራኒው የፖለቲካ ተቀናቃኞችን አሳዶ ያጠፋል፡፡ በሕገ መንግሥት ለይስሙላ በተደነገገው ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ሐሳባቸውን የገለጹ ጋዜጠኞችን በአሰቃቂ እስር ቤቶች አስሮ ያማቅቃል፤ በአሰቃቂ የምርመራ ዘዴ ያሰቃያል፤ ያሳድዳል፤ ይገድላል፤ ዜጎች ራሳቸውን በአሰቃቂ ሁኔታ እስኪያጠፉ ድርስ ተስፋቸውን ያጨልማል፡፡ ይህንንም ነባራዊ ሁኔታ በወጣትነት ዕድሜዬ ይህንን ትውልድ የቀበረ አስከፊ ስርዓት እንድታገል አስገድዶኛል፡፡

እኔ እና ዕድለቢሱ ትውልዴ


ሲራክ ተመስገን የ24 ዓመት ወጣት ሲሆን፤ በኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ዘመን ተወልዶ ያደገ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር አንዳንዶቹ ‘The EPRDF Generation’ የሚሉት ትውልድ አባል ነው፡፡ ሲራክ ብቻ ሳይሆን ስልሳ አምስት በመቶው የኢትዮጵያ ሕዝብ ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ሥልጣን ከያዘበት ጊዜ ወዲህ የተወለደ ሲሆን፤ ይሄም ከአገሪቱ አጠቃላይ ሕዝብ ሁለት ሦስተኛውን ይሸፍናል፡፡ ሲራክ በዚህ ዕድሜው “እኔና ትውልዴን ጠፍጥፎ የሠራን ኢሕአዴግ ተስፋ አስቆርጦኛል” ይለናል፡፡ ቁጭቱን አንብቡለት፡፡


ማንም ሰው ወዶ እና ፈቅዶ ‹በዚህ ጊዜና እዚህ ቦታ ልወለድ› ብሎ አልተወለደም። እኔም ቀን
ሲጎልብኝ የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ.) ከበረሃ ተነስቶ ምኒልክ ቤተ መንግሥት ሲደርስ፣ በዚህች ምስኪን ድሃ አገር ተወለድኩ። እንደ መሰሎቼ ሁሉ የእኔን የፖለቲካ ማንነትም በአብዮታዊ ዴሞክራሲ ርዕዮተዓለማዊ ቅኝት በተቃኘች አገር ኢሕአዴግ ጠፍጥፎ ሠራው። የኢሕአዴግ ኢትዮጵያም፣ እኛም የግንቦት 20 ፍሬዎች ቀስ እያልን ማደግ ጀመረን። ዕድሜያችንም፣ ዕድልም 1997 አገራዊ ምርጫ ላይ አደረሰን። የተለያዩ የፖለቲካ ሐሳብ ያላቸው ቡድኖች መሐከል የሚካሄድ የአደባባይ የፖለቲካ ውይይት ለመጀመሪያ ጊዜ ለማዳመጥ ታደልን። እዚህ ላይ ነው እኔና የትውልዴ አባላት ነቃ ብለን ኢሕአዴግን በቆሪጥ ማየት የጀመርነው።

ኢሕአዴግ ልጆቹን እንዴት አሳደገን?

እኛ የኢሕአዴግ ልጆች ሁለት ተቃራኒ የማንነት ጥያቄዎች ከግራ እና ከቀኝ እየጎተቱን ነው ያደግነው። የአካባቢያዊ (የዘውግ) ማንነት እና አገራዊ (የዜግነት) ማንነት። አሳዳጊያችን ኢሕአዴግ መሠረቱን ያደረገው ፈግሞ በዚህ አካባቢያዊ ማንነት ላይ ነው። ገና በጨቅላ ዕድሜያችን አገራዊ ማንነነትን አፍሮሶ በአካባቢያዊ ማንነት የሚተኩ ንግግሮችን ከኢሕአዴግ አመራሮች አንደበት እየሰማን ነው ያደግነው። በእኔ እምነት እንሰማቸው የነበሩት እንደ “የአክሱም ሐውልት ለወላይታ ምኑ ነው?”፣ “ባንዲራ ጨርቅ ነው”፣ “የኢትዮጵያ ታሪክ የ100 ዓመት ታሪክ ነው”… የመሳሰሉት ንግግሮች አገራዊ ማንነትን በመተው አካባቢያዊ ማንነትን እንድንይዝ መሠረቱ ጥሏል ብየ አስባለሁ።

ካለፉ የታሪክ ኹነቶች ውስጥ አንድ ሊያደርጉን የሚችሉ ትርክቶችን ወደ ጎን በመግፋት፣ ሕዝቦችን ቅራኔ ውስጥ የሚከቱ ትርክቶች ብቻ ተመርጠው እየተመገብን ነው ያደግነው። ያለበሱን አገራዊ ማንነትን ሳይሆን አካባቢያዊ ማንነት ነው፡፡ ለዚህም ይመስለኛል አሁን ላይ የካቲት ሃያ ሦስትን የማያውቁ፣ ሕዳር ሃያ ዘጠኝን በሽር ጉድ የሚያከብሩ የትውልድ አጋሮቼ የበረከቱት፡፡

የትውልዳችን ፈተና

(ለመግባባት እንዲያመቸን ትውልዳችን ስል ኢሕአዴግ አዲስ አበባ በደረሰበት ዓመት እና በቀጣዩ ዓመት የተወለዱ ልጆችን ማለቴ እንደሆነ ይታወቅልኝ።)

የእኔ ትውልድ ብዙ ፈተናዎች አሉበት። እስኪ ዘርዘር አድርገን ለማየት እንሞክር።

ሀ. ‘ጸጥ-ለጥ’ ብሎ የተገዛው ትውልዴ

ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ኢሕአዴግ ባወጣው ሕገ መንግሥት ላይ ቢካተትም በሀገራችን ላይ በተጨባጭ የምናየው ግን ሐሳብን በነጻነት መግለጽ ከፍተኛ አደጋ ያለው እንደሆነ ነው፡፡ ብዙዎች ሐሳባቸውን በነጻነት በመግለጻቸው ተደብድበዋል፣ ተገድለዋል፣ ታስረዋል፣ ተሰደዋል። በአገራችንም ጠንካራ ‘ሚዲያ’ እንዳይፈጠር ቀን ከሌ’ት ገዢው ፓርቲ ትልቅ እንቅፋት ሆኗል።

ይህ የእኔ ትውልድ ከመንግሥት ጋር እንዲህ ዓይነት ቅራኔዎች ውስጥ አለመግባቱ የኢሕአዴግ ልጆች ‘ጸጥ-ለጥ’ ብለው እየተገዙ መሆኑን ያሳያል። ዘመናዊው ‘የማኅበራዊ ሚዲያ’ ላይ በጣም ጥቂቶች ሊባሉ የሚችሉ ግለሰቦች ፈራ-ተባ እያሉ መንግሥትን ሲተቹ ይታያሉ። ‘ጸጥ-ለጥ’ ብሎ የመገዛቱን ነገር የከፋ የሚያደርገው በእኔና ከእኔ ዕድሜ በታች ያሉ ሴቶች በአደባባይ መንግሥትን ሲተቹ አለማየት ነው።

ለ. ዕድለቢሱ ትውልዴ

ሌላው የእኔ ትውልድ ፈተና ዕድሎችን ማግኘት የሚችለው በብቃቱ ሳይሆን ለገዢው ፓርቲ ባለው ታማኝነት ወይም የገዢው ፖርቲ አካባቢ ተወላጅ ከሆነ ነው። ከ2005 ጀምሮ በመቶ ሺሕዎች የሚቆጠሩ የትውልድ አቻዎቼ ከተለያዩ ዩንቨርስቲዎች በየዓመቱ እየተመረቁ ነው። እኒህ ተመራቂ ተማሪዎች ትልቁ ፈተናቸው ሥራ ማግኘት ላይ ነው። ከመመረቂያ ሰርተፍኬታቸው ይልቅ ኢሕአዴግን ከመሠረቱት ከአራት ድርጅቶች የአንዱን በደም የሚመሳለውን መርጦ የአባልነት መታወቂያ ይዞ መገኘት የሥራ ዋስትና ነው። ኢሕአዴግን እየተቃወሙ የመንግሥት ሥራ የማግኘት ዕድል ያላቸው በጣም ጥቂቶች ናቸው። በተለያዩ የአመራርነት ቦታዎች መቀመጥ የማይታሰብ ነው። ከቀበሌ ካቢኔ አንስቶ እስከ ሚኒስትር ድረስ በኢሕአዴጋዊያን የተሞላ ነው። ባንድ ወቅት ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር አንድን ሰው በአመራርነት ቦታ ለማስቀመጥ ብቃት ሳይሆን ለፓርቲው ያለውን ታማኝነት እንደሚመርጡ በአደባባይ ተናግረዋል። ይህ ትውልድ ሥራ ሊያገኝ የሚችለው ወይ አመራር ሊሆን የሚችለው በብቃቱ ሳይሆን ለገዢው ፓርቲ ባለው ታማኝነት አለበለዚያ የዘር ሐረጉ ከገዢው ፓርቲ የሚመዘዝ ከሆነ ነው።

“እኔ… ተስፋ የለኝም?”



መልዕክተ ዓብይ የ25 ዓመት ወጣት ስትሆን፤ በኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ ዘመን ተወልዳ አድጋለች፡፡ በሌላ አነጋገር መልዕከተ አንዳንዶቹ ‘The EPRDF Generation’ የሚሉት ትውልድ አባል ነች፡፡ መልዕክተ ብቻ ሳትሆን ስልሳ አምስት በመቶው የኢትዮጵያ ሕዝብ ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ ሥልጣን ከያዘበት ጊዜ ወዲህ የተወለደ ሲሆን፤ ይሄም ከአገሪቱ አጠቃላይ ሕዝብ ሁለት ሦስተኛውን ይሸፍናል፡፡ መልዕክተ በዚህ ዕድሜዋ የፖለቲካ መነቃቃቷን ጨምራ በስርዓቱ ያላትን ‹ተስፋ› እንዲህ ታስነብበናለች፡፡ እስኪ አንብቧት፡፡

“ፖለቲከኛ አይደለሁም፤ ፖለቲካ አይመቸኝም፡፡ የኔ የመኖር ዓላማ፤ መጀመሪያ እኔ እራሴን እና ቤተሰቤን ካለሁበት ችግር ማላቀቅ ነው፡፡ ፖለቲካ የደላው እና ኑሮን ያሸነፉ ሰዎች ችግር እንጂ የኔ አይደለም፡፡ እኔ ምን ያገባኛል?”

ይህ እስከቅርብ ጊዜ የነበረኝ የፖለቲካ አመለካከት ነበር፡፡ በርግጥ አሁን ላይ በፊት ከነበረኝ
አስተሳሰብ የተለየ አመለካከት እየተፈጠረብኝ መመጣቱ በራሱ ረዥም ሒደት ነው፡፡ ፖለቲካ የሁሉም ሰው የሕይወት ሕልውና እንደሆነ እየገባኝ ነው መሰል የማየውም የምስማውም የምኖርውም ብቻ ባጭሩ እኔም ሆንኩ ማንም ሰው ‘ከፖለቲክሱ’ ነጻ ሆኖ መኖር እንደማይችል የገባኝ አሁን ነው:: በ25 ዓመቴ:: ያሳዝናል:: ያደለው በ25 ዓመቱ የሆነ ለውጥ በራሱ ላይም ሆነ በቤተሰቡ ከዛም አልፎ ለሀገሩ ያበረክታል፡፡ እኔ ግን  በ25 ዓመቴ ገና ምንም እንደማያቅ ሕፃን ልጅ የፖለቲካ ፅንሰ ሐሳብ እዲገባኝ ‘ሀ’ ብዬ ለመጀመር እየተነሳሁ ነው፡፡ ለዚህ ግን ተጠያቂው ማን ይሆን?

አባቴ ይሆን?

አይ፤ የኔ አባት የ14 ዓመት ልጅ እየለሁ ነበር በሞት የተለየኝ፡፡ በሕይወት በነበረበት ጊዜ ግን የቻለውን እና ያኔ በእኔ አቅም ልረዳው የምችለውን ይነግረኝ እና ያስተምረኝ ነበር፡፡ እሺ ታዲያ ማነው?

እናቴ ትሆን?

እናቴማ እኔን ለማሳደግ ደፋ ቀና ትበል ወይንስ ስለእኔ የፖለቲካ እና የሕይወት አመለካከት ትጨነቅ? በዚያ ላይ እንደሚታወቀው  የኛ እናቶች ከሕይወት ተሞክሯቸው ፖለቲካን በሩቁ ብናይላቸው ደስ ይላቸዋል፡፡ እናም፣ እናቴ ላይማ አልፈርድም፡፡

መምህሮቼ ይሆኑ?

መምህሮቼ? ለምን እንደዚህ ዓይነት አመለካክት እንዲኖረኝ አድርገው አሳደጉኝ? በተለይ የሥነ-ዜጋ መምህሮቼ ለምንድን ነው የተሻለ አመለካከት እና አሰተሳስብ እንዲኖረኝ አድርገው እና የእውነትም ከዚያ ትምህርት ማግኘት የነበረብኝን ዕውቀት ያላስቀሰሙኝ? ለምንድን ነው ያለሁበት ስርዓት ብቻ ትክክል እና ያለፉት ስርዓቶች ላይ ጥላቻ ብቻ እንዲኖረኝ አድርገው ያስተማሩኝ? አሁን አሁንማ ሲገባኝ እነሱ የማያምኑብትን ሐሳብ እኔ እንዳምንበት ሲያደርጉ እንደነበር ነው የሚሰማኝ:: ይገርመኛል፡፡

ከዕድሜው በላይ ታሪክ የተሸከመው የኔ ትውልድ


ዓለማየሁ ደንድር የ25 ዓመት ወጣት ሲሆን፤ በኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ዘመን ተወልዶ ያደገ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር አንዳንዶቹ ‘The EPRDF Generation’ የሚሉት ትውልድ አባል ነው፡፡ ዓለማየሁ ብቻ ሳይሆን ስልሳ አምስት በመቶው የኢትዮጵያ ሕዝብ ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ሥልጣን ከያዘበት ጊዜ ወዲህ የተወለደ ሲሆን፤ ይሄም ከአገሪቱ አጠቃላይ ሕዝብ ሁለት ሦስተኛውን ይሸፍናል፡፡ ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ሲገባ የ8 ወር ልጅ የነበረው ዓለማየሁ “ኢሕአዴግ ላይ ያለንን ተስፋ አንጠፍጥፈን ወደ ልኂቃኑ ማንጋጠጥ ጀምረናል” ይለናል፡፡ አንብቡት፡፡

የአሪስጣጣሊስ "Man is by nature a Political Animal" የሚለው ሐሳቡ፤ሳቡን ብቻ ሳይሆን
ጥሬ ትርጉሙን (literal meaning) ለመረዳት በኢሕአዴግ የኔታነት ለተማርነው ሊከብደን ይችላል። ጥቅልሳቡ 'ወደድክም ጠላህም ከፖለቲካ አታመልጥም' እንደማለት ይመስለኛል።አንተ ልጅ ፖለቲካ ማውራት ይቅርብህ ኢሕአዴግ ያስርሃል" ብለው የሚጨነቁልን ወዳጆች፤ በዛው አፋቸውተው አንተ የኢሕአዴግ ፖለቲካ... ልጁ ላይ አትድረስ" ማለት ቢችሉ መልካም ነበር። ከፖለቲካ ጋር ያለንን ኑሮ ለመረዳት ጊዜ ይወስዳል፤ ፖለቲካ ሲገነድስ እንጂ ሲሸርፈንና ሲጨርፈን አይታወቅም።

ፖለቲካ ሲጨርፈን

የጨረፈን የጫካ ጓዶች ከተማ ሲጣሉ ነው፤ በአገር ሥም ተዋጉ፣ አብሮ የኖረ ጎረቤት ተላቅሶ ተበታተነ። ልጅ ስለነበርን ፖለቲካ መሆኑን ለመረዳት ጊዜ ወስዶብናል። ከተማ ሲገቡ 8 ወር ልጅ ነበርኩ፤ ሳንጎረምስ ተባሉ፤ ከልጅነት የጨዋታ ሚስቴዊንታ ለጋስ ጋር እንኳን የጉርምስና መተፋፈር ሳይሆን ፖለቲካ ነው የለየን ብል ማን ያምናል? እንደዛ ለመረዳት ግን ጊዜ ወስዷል። "ዳሕላክ ላይ ልሥራ ቤቴን ... ነጠለኝ ክፉ ዘመን ከምወዳት ባለቤቴ" ተብሎ ሲዘፈን እንኳን ፖለቲካ መሆኑን አልተረዳሁም ነበር።

ከስንት አንዴ ብልጭ ከሚሉት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተቃውሞዎች በኋላ 97 ምርጫ የማንንም ቀልብ ይዟል፤ የትምህርት ደረጃ ሲባል 'ማንበብና መጻፍ' የሚለው ሁሉ ጋዜጣ ይገዛል፤ እየተቀበልን እናነባለን፡፡ ሙቀቱ እንጂ ጉዳዩ ብዙም አይገባንም፡፡ ያኔ 9 ክፍል ነበርኩ። ሙቀቱ ይስባል፤ እነ ልደቱአንከራከርም” ብለው ረግጠው ሲወጡ፤እንነጋገርበታለን”፤ቅንጅት ፓርላማ አልገባም” ሲልልክ ናቸው” እንላለን፤ ፖለቲካው ግን አይገባንም፡ ሙቀቱ ነውሚስበን።አዲስ ከተማዎች ቀወጡት” ሲባልእንዴት እኛስ ተበለጥን?” ይባላል፤ ይቀወጣል፤ ፌዴራል ይመጣል፤ ፀጉሩን ፍሪዝ ያረገ ሲቪል ፖሊስ፣ ፍሪዝ ያረገውንና የጠቆረውን ተማሪ እያንበረከከ በጫማ ጥፊ ይላል፤ እንዲይም ሆኖ ስለ ፖለቲካ መመታታችን ይግባን አይገባን እርግጠኛ አይደለሁም፤ በአዲስ ከተማ ተማሪዎች መበለጣችን እንጂ ምርጫ መጭበርበር ማለት ምን እንደሆነምምንረዳም አይመስለኝም።