Saturday, May 28, 2016

ከዕድሜው በላይ ታሪክ የተሸከመው የኔ ትውልድ


ዓለማየሁ ደንድር የ25 ዓመት ወጣት ሲሆን፤ በኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ዘመን ተወልዶ ያደገ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር አንዳንዶቹ ‘The EPRDF Generation’ የሚሉት ትውልድ አባል ነው፡፡ ዓለማየሁ ብቻ ሳይሆን ስልሳ አምስት በመቶው የኢትዮጵያ ሕዝብ ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ሥልጣን ከያዘበት ጊዜ ወዲህ የተወለደ ሲሆን፤ ይሄም ከአገሪቱ አጠቃላይ ሕዝብ ሁለት ሦስተኛውን ይሸፍናል፡፡ ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ሲገባ የ8 ወር ልጅ የነበረው ዓለማየሁ “ኢሕአዴግ ላይ ያለንን ተስፋ አንጠፍጥፈን ወደ ልኂቃኑ ማንጋጠጥ ጀምረናል” ይለናል፡፡ አንብቡት፡፡

የአሪስጣጣሊስ "Man is by nature a Political Animal" የሚለው ሐሳቡ፤ሳቡን ብቻ ሳይሆን
ጥሬ ትርጉሙን (literal meaning) ለመረዳት በኢሕአዴግ የኔታነት ለተማርነው ሊከብደን ይችላል። ጥቅልሳቡ 'ወደድክም ጠላህም ከፖለቲካ አታመልጥም' እንደማለት ይመስለኛል።አንተ ልጅ ፖለቲካ ማውራት ይቅርብህ ኢሕአዴግ ያስርሃል" ብለው የሚጨነቁልን ወዳጆች፤ በዛው አፋቸውተው አንተ የኢሕአዴግ ፖለቲካ... ልጁ ላይ አትድረስ" ማለት ቢችሉ መልካም ነበር። ከፖለቲካ ጋር ያለንን ኑሮ ለመረዳት ጊዜ ይወስዳል፤ ፖለቲካ ሲገነድስ እንጂ ሲሸርፈንና ሲጨርፈን አይታወቅም።

ፖለቲካ ሲጨርፈን

የጨረፈን የጫካ ጓዶች ከተማ ሲጣሉ ነው፤ በአገር ሥም ተዋጉ፣ አብሮ የኖረ ጎረቤት ተላቅሶ ተበታተነ። ልጅ ስለነበርን ፖለቲካ መሆኑን ለመረዳት ጊዜ ወስዶብናል። ከተማ ሲገቡ 8 ወር ልጅ ነበርኩ፤ ሳንጎረምስ ተባሉ፤ ከልጅነት የጨዋታ ሚስቴዊንታ ለጋስ ጋር እንኳን የጉርምስና መተፋፈር ሳይሆን ፖለቲካ ነው የለየን ብል ማን ያምናል? እንደዛ ለመረዳት ግን ጊዜ ወስዷል። "ዳሕላክ ላይ ልሥራ ቤቴን ... ነጠለኝ ክፉ ዘመን ከምወዳት ባለቤቴ" ተብሎ ሲዘፈን እንኳን ፖለቲካ መሆኑን አልተረዳሁም ነበር።

ከስንት አንዴ ብልጭ ከሚሉት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተቃውሞዎች በኋላ 97 ምርጫ የማንንም ቀልብ ይዟል፤ የትምህርት ደረጃ ሲባል 'ማንበብና መጻፍ' የሚለው ሁሉ ጋዜጣ ይገዛል፤ እየተቀበልን እናነባለን፡፡ ሙቀቱ እንጂ ጉዳዩ ብዙም አይገባንም፡፡ ያኔ 9 ክፍል ነበርኩ። ሙቀቱ ይስባል፤ እነ ልደቱአንከራከርም” ብለው ረግጠው ሲወጡ፤እንነጋገርበታለን”፤ቅንጅት ፓርላማ አልገባም” ሲልልክ ናቸው” እንላለን፤ ፖለቲካው ግን አይገባንም፡ ሙቀቱ ነውሚስበን።አዲስ ከተማዎች ቀወጡት” ሲባልእንዴት እኛስ ተበለጥን?” ይባላል፤ ይቀወጣል፤ ፌዴራል ይመጣል፤ ፀጉሩን ፍሪዝ ያረገ ሲቪል ፖሊስ፣ ፍሪዝ ያረገውንና የጠቆረውን ተማሪ እያንበረከከ በጫማ ጥፊ ይላል፤ እንዲይም ሆኖ ስለ ፖለቲካ መመታታችን ይግባን አይገባን እርግጠኛ አይደለሁም፤ በአዲስ ከተማ ተማሪዎች መበለጣችን እንጂ ምርጫ መጭበርበር ማለት ምን እንደሆነምምንረዳም አይመስለኝም።

የሥልጣን ዘመኑ የአንድ ጎረምሳ (ሲሞት የሱ የሥልጣን ዘመንና የኔ ዕድሜ ዕኩል ነበር ማለት ይቻላል) ዕድሜ የነበረው መለስ ዜናዊ ሞተ፤ ነብሱን ይማረው። ከልጅነት እስከ ዕውቀት እሱ ነው የመራን፤ ከቴሌቪዝን በሚታይ ንግግሩየታችኞቹ እንጂ መለስማ ጎበዝ ነው” በሚል ማኅበረሰብ አድገን ከሥልጣን ሳይወርድ ታሞ ሞተ፤ አዘንን።አበበ ገላው እንዴት በአደባባይ ያዋርደዋል?” ሳንልም አልቀረንም። ፖለቲካውን ለመረዳት ሙከራ የጀመርኩት የዚህን ጊዜ ነው፤ ምናልባትም ፅንፍ የያዘው የሙሾ አውራጁና “እሰይ እንኳን ክልትው አለ” ባዩም ይሆናል ትኩረቴን የሳበው፡፡ የተመስገን ደሳለኝና የፍትሕ ጋዜጣ ውለታ ሳይዘነጋ፡፡

25ቱን የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ.) የሥልጣን ዓመታት ለመረዳት ለሞከረ የመጀመሪያው መረዳት ኢሕአዴግ ማለት መለስ ማለት እንደነበር ነው።ኢሕአዴግ ጨቋኝ ነው፡፡ ያስራል፣ ያሳድዳል፣ ይገድላል” ስንል መለስን ማለታችን ነው፡፡ በተለይ ከ’93 የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕ.ወ.ሓ.ት) ክፍፍል በኋላ መለስ የኢሕአዴግ የሥጋም የነብስም አባት ነበር። ፕሮፌሰር መድኃኔ ታደሰ እንኳን 'Meles Zenawi and the Ethiopian State' ባለው መለስን በሚያንቆለጳጵስበት መጣጥፉ እንዲህ ጽፏል፡-

The process of consolidation Right after the Ethiopia-Eritrea war and the split within his core political party the TPLF, Meles had concentrated power in his own hands and a tiny group of advisors. [...] Meles did not only withered away the threat to his power but he had slowly but steadily worked his way to a supreme position in the Ethiopian state

ፖለቲካውን በሥመብሔር ብሔረሰቦች› ስንረዳው

የአሜሪካና የኢሕአዴግ አለቆች ነጻነትበኋላ ስለብዝኃነት በማውራት ይመሳሰላሉ። የአሜሪካኖቹ አንባገነንነትን ለመንቀል "how we prevent tyranny?" በሚል እሳቦት/ጥያቄ በመነሳት ብዝኃነትን (pluralism) እንደ መፍትሔ ሲያቀርቡ፤ የኢሕአዴግ አለቆች አምባገነንነትን ለመትከል "እንዴት በሥልጣን መሰንበት እንችላለን?" በሚል ጥያቄ በመነሳትአገሪቷ በአጋጣሚ የታደለችውን (መታደል ከሆነ?) የብሔር ብዝኃነት በማስጮህ የከፋፍለህ ግዛ ዓላማቸውን አሳለጡ። እነ ጀምስ ማዲሰን የፍላጎት ግጭት (clash of interest) ለዴሞክራሲ ወሳኝ ነው ሲሉ፤ የኢሕአዴግ የጎበዝ አለቆች የብሔር ግጭትን የሥልጣን ማስጠበቂያ አደረጉት። ሁለቱም (የአሜሪካኖቹም የኢሕአዴጎቹም) ልኂቃን ዓላማቸውን ማስጠበቂያ ያደረጉት መፍትሔ ደሞ ፌደራሊዝም ነው።

ባለመታደል የእኔ ትውልድ አዲስ ስርዓት› መሞከሪያ ትውልድ ነው። ከዓመት በፊት ያነበብኩት የሌንጮ ለታ መጣጥፍ ላይ "ኢሕአዴግ ለብሔር ፌደራሊዝሙ (Ethnic Federalism) ሊወቀስም ሊወደስም አይገባም" (ቃል በቃል አልተቀመጠም) ይላሉ። እንደምክንያት ያቀረቡትም ብዙ ብሔሮች ነፍጥ ያነሱበት ዘመን በመሆኑ ከብሔር ፌደራሊዝም ውጪ አማራጭ አልነበረም የሚል ነው። ኦቦ ሌንጮ ልክ ሊሆኑ ይችላሉ። ጥያቄው ግን ‹“የዘውግ ፌደራሊዝም ነፍጥ ላነገቡ መፍትሔ ነው” ያለ ስርዓት፤ በራሱ (በዘውግ ፌዴራሊዝሙ) ላይ ነፍጥ ላነገቡትስሚሰጠው መፍትሔ ምን ሊሆን ይችላል?› ነው የፌደራሊዝም መሠረቱ የኃይል ክፍፍል (decentralization of power) ሆኖ ሳለ፤ ኢሕአዴግ አገሪቷን በብቸኝነት ፈላጭ ቆራጭ በሆነበት ሁኔታ ሥልጣኑን እነማን እንደሚያከፋፍሉት ግልጽ አይደለም። በዛ ላይ የፓርቲ መዋቅሩ ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት (Democratic Centralism) መሠረት ያደረገ ፓርቲ ራስ ገዝነትን (Autonomous power) ለክልሎች ይሰጣል ማለትማይታሰብ በመሆኑየዘውግ ፌዴራሊዝሙ የከፋፍለህ ግዛ ስትራቴጂ ጭምብል ነው” ለማለት ያስደፍራል። የፌዴራሊዝም ባሕሪ የሆነው የክልሎች (states)  ፉክክር (competitiveness) በኛገር በተለያ ዘውጎች መካከል መሆኑም ልብ ይሏል። (እዚህ ላይ የዘውግ ፌደራሊዝም የሚያመጣብን ጣጣ ለማሳየት እንጂ፤ በዚህ ሰዓት ፌደራሊዝሙ ይፍረስ የሚል አቋም እያራመድኩ እንዳልሆነ ይታወቅልኝ።)

የትውልዳችን ፈተና

ነገሮች ክርር እያሉ ነው፤ የጓደኝነት መሥፈርቱ የ‹ብሔር ተወላጅነት› እየሆነ ነው። በአንድ ወቅት በታሪክ የተከናወኑ ጥፋቶች ጠረጴዛ ላይ ተዘርግፈው የትውልዳችን መካሰሻ ሆነዋል። የ25 ዓመት ሸክሙ አልበቃ ብሎን የመቶ እና የሁለት መቶ ዓመቱን መደራረቡን መርጠናል፡፡ ስርዓቱም እነዚህን ያለፉ የታሪክ ችግሮች ያጦዛቸዋል። አብዛኞቹ ልኂቃን ጥጋቸውን እንደያዙም ናቸው። ወጣቱ ጫንቃ ላይ ካሉት የኑሮ ብሶቶች የሥራ ማጣት፣ የስርዓቱሎሌ› ባለመሆን የሚደርሰው የኢኮኖሚ መገለል፤ ከፖለቲካና ከኢኮኖሚ ስደተኝነት በላይ እየላሉ ያሉ የማኅበራዊ አንድነት እሴቶች በዚህ ፅንፍ ቀጥለውሚበጣጠሱ ከሆነ የትውልዳችንን መከራሚያበዛው ይመስላል፡፡ሚያሳዝነው ደግሞ ይሄን ማኅበራዊ እሴት አቅለው የሚያዩልኂቃን› ከሁሉም ጥግ አፍጥጠው መውጣታቸው ነው። የታሪክ ችግሮችና ስህተቶች ተድበስብሰው መታለፍ ባይኖባቸውም በሚያጠፋፋን መልኩ መካሰሱ ማናችንንም አይጠቅመንም፡፡

ምንም አንኳን የልኂቃኑ ዝምታ አደንቋሪ (deafening silence) ቢሆን፤ ተስፋችንን ከልኂቃኑ ላይ አናወርድም፡፡ ኢሕአዴግ ላይ ያለን ተስፋ ተንጠፍጥፎ በማለቁም ወደ ልኂቃኑ አሻግረን እንመለከታለን፤ እኔና ትውልዴ፡፡ ምናልባትም ዋለልኝ የ40 ዓመት ፖለቲካ የመተረበትን ዕድሜ አልፈነው ይሆናል፤ የዋለልኝ የዘመን አቻዎች ግን አሁንም ዋነኛ የአገሪቷን ዕጣ ፋንታ ወሳኝ ናቸው፡፡ እንደ አንዳንድ የትውልድ ጓዶቼ ተስፋ በማጣት “‹ያ ትውልድ› የተዋስኦ ሜዳውን ለቆ ይውጣ” የሚል አቋም ባይኖረኝም፣ የኔ (የአገሪቷም) ዕጣ ፈንታ በዛ ትውልድ ልኂቃን መስማማት ላይ የተመሠረተ በመሆኑ ኢሕአዴግን ከመንቀል በፊት የልኂቃኑ ስምምነት ጠባቂ ነኝ፤  ማን ያውቃል ብዙ አይርቅ ይሆናል፡፡

No comments:

Post a Comment