ዮሴፍ መርጉ የ25 ዓመት ወጣት ሲሆን፤ በኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ዘመን ተወልዶ
ያደገ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር አንዳንዶቹ ‘The EPRDF Generation’ የሚሉት ትውልድ አባል ነው፡፡ ዮሴፍ ብቻ ሳይሆን
ስልሳ አምስት በመቶው የኢትዮጵያ ሕዝብ ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ሥልጣን ከያዘበት ጊዜ ወዲህ የተወለደ ሲሆን፤ ይሄም ከአገሪቱ አጠቃላይ
ሕዝብ ሁለት ሦስተኛውን ይሸፍናል፡፡ ዮሴፍ “ከዚህ በኋላ በኢሕአዴግ
ተስፋ ማድረግ፤ በራሱ ተስፋ መቁረጥ እንደሆነ አድርጌ እወስደዋለሁ” በማለት መፍትሔ ይሆናል የሚለውን ሐሳብ ይሰነዝራል፡፡ አንብቡት፡፡
ከ1996
አንስቶ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ከስድስተኛ ክፍል ጀምሮ መሰጠት የጀመረው ‹የሥነ-ዜጋ›
ትምህርት በፖለቲካ ንቃቴ ላይ በቀላሉ የማይገመት አስተዋፅዖ አድርጓል፡፡ በአጋጣሚ ይሁን ሆን ተብሎ ባላውቅም መምህራኑ ሥነ-ዜጋንና የታሪክ ነክ ትምህርቶችን ደርበው እንዲይዙ በመደረጉ በመንግሥትና አስተዳደር ግንዛቤዬ ላይ ደማቅ አሻራን አሳርፏል፡፡ እንዲህ፣ እንዲህ እያለ እየዳበረ የመጣው የፖለቲካ ግንዛቤዬ ከፍ እያልኩኝ ስመጣ በተለያዩ መጽሐፍት ታግዞ፤ ብሎም የበይነ-መረብ እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ መናኘቱ ስሜቴን በአደባባይ የመግለጽ ድፍረቱንና አጋጣሚውን ፈጠረልኝ:: ብዙም ነገር እንዳውቅም ሆንኩኝ፡፡
ትምህርት በፖለቲካ ንቃቴ ላይ በቀላሉ የማይገመት አስተዋፅዖ አድርጓል፡፡ በአጋጣሚ ይሁን ሆን ተብሎ ባላውቅም መምህራኑ ሥነ-ዜጋንና የታሪክ ነክ ትምህርቶችን ደርበው እንዲይዙ በመደረጉ በመንግሥትና አስተዳደር ግንዛቤዬ ላይ ደማቅ አሻራን አሳርፏል፡፡ እንዲህ፣ እንዲህ እያለ እየዳበረ የመጣው የፖለቲካ ግንዛቤዬ ከፍ እያልኩኝ ስመጣ በተለያዩ መጽሐፍት ታግዞ፤ ብሎም የበይነ-መረብ እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ መናኘቱ ስሜቴን በአደባባይ የመግለጽ ድፍረቱንና አጋጣሚውን ፈጠረልኝ:: ብዙም ነገር እንዳውቅም ሆንኩኝ፡፡
1983
እኔ የተወለድኩበት ዓመት ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ.) ወደ ሥልጣን የመጣውም
በዚሁ ዓመት ነው:: ዘንድሮ በ2008 የብር ኢዮቤልዩውን የሚያከብረው የኢሕአዴግ መንግሥት፣ የእሱን መንግሥት ብቻ በማውቀው
በኔ እንዴት ይታያል የሚለውን እስኪ እንመልከት::
ማወቅ
ዕዳ ነው። አንድ ሰው በማወቁ የተለያዩ የስሜት ፈረቃዎችን ለማስተናገድ ይገደዳል። በትውልድ ዘመኔ አንድ መንግሥት ብቻ ማየቴና
በአንጻሩ ደግሞ የምዕራቡ ዓለም በነጻ ምርጫ የተለያዩ መንሥታትን ማየት መቻላቸው የፈጠረውን ነገር ማወቄ የተለያዩ ስሜቶችን
ሰጥቶኛል። አንድ መንግሥት ያለገደብ በሥልጣን ላይ መቆየቱ ‹የሥልጣን መባለግን› ከመፍጠር ውጭ ለአገሪቱ የሚፈጥረው ነገር
የለም። ይህንንም ለማረጋገጥ አፍሪካን ለረጅም ጊዜ ያስተዳደሩና እያስተዳደሩ ያሉ መንግሥታትን ማየት ብቻ ብቂ ነው። በሌላ
መልኩ ደግሞ የምዕራቡ ዓለም አገራት ነጻና ፍትሐዊ ምርጫ በማካሔድ ባሻቸው ጊዜ የፈለጉትን መንግሥት መቀያያር ይችላሉ፡፡።
በውጤቱም አንዱ መንግሥት የሰነፈበትን ተተኪው መንግሥት እየሠራ እንዲያልፍ፤ ይህም ብቻ አይደለም ተተክቶ ያለፈው መንግሥት
የጎበዘበትን አዲሱ መንግሥት በተሻለ ሁኔታ በማስቀጠል አልፏል። እያለፈም ነው።
ይህንንና
መሰል ሁነቶችን ሳስብ በትውልድ ዘመኔ አንድ መንግሥት ብቻ ማየቴ እኔም እንደ ዜጋ፤ አገሬም እንደ አገር የተለያዩ መንግሥታት፤
የተለያዩ ክኅሎቶችን የማጣጣም ዕድል ማጣት ከሚፈጥረው ቁጭት ጋር ጭምር ነው፡፡ የኔም ትውልድ ፖለቲካን በፍላጎት ሳይሆን
በቁጭት የሚገባበት ረመጥ ሆኖበታል:: እዚህ ድምዳሜ ላይ ያደረሱኝን የታሪክ አጋጣሚዎች እንመልከት::
በ1990
የኤርትራ መንግሥት የኢትዮጵያን ድንበር አልፎ መግባቱን ተከትሎ ‹ለኤርትራ መንግሥት ምን ዓይነት የአፀፋ ምላሽ ይሰጥ?›
በሚለው ላይ የሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕ.ወ.ሓ.ት) ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት በሁለት ጎራ በመሆን የተለያየ አቋም
ይይዛሉ:: ይኽም የአቋም ልዩነት በስየ አብርሃና በመለስ ዜናዊ በኩል የጎላ ከመሆኑም ባሻገር የእርስበርስ መተማመን ላይ
የማይናቅ ጥላሸትን ፈጠረ:: ጊዜ ሊያስታርቀው ያልቻለው የሁለቱ ግለሰቦች መቃቃር ፓርቲውን ለሁለት መሰንጠቅ የዳረገው ሲሆን፤ በሽኩቻው
መጨረሻም ‹የነስየ ቡድን› የፓርላማ አባልነት በዚያውም ያለመከሰስ መብታቸውን በመንጠቅ ተጠናቀቀ:: ይኽም አልበቃ ብሎ “ስየ አይተኛልኝ”
ብሎ ያሰበው መለስ እነስየ ከፓርላማ በተሰናበቱ በአራተኛ ቀን “ስየን እግር ተወርች ያስርልኛል” ያለውን የሙስና ‹ካርድ› በመምዘዝ
ያለበቂ ማስረጃ ዘብጥያ እንዲወርድ አድርጎታል:: ከዛ በኋላም ባለው የፓርቲው አባላት መጠየቅ ሲጀምሩና የሐሳብ ልዩነት ሲያሳዩ
ይኸው የሙስና ‹ካርድ› እየተመዘዘባቸው ለእሥር ሲዳረጉ ተመልክተናል:: ይኽም የታሪክ አጋጣሚ በፓርቲው ውስጥ አዳዲስ ሐሳቦችን
ማስተናገድ እንዳይቻልና ዴሞክራሲም ከውስጥ ይመነጫል ተብሎ እንዳይታሰብ አድርጓል:: ፓርቲው የውስጥ ቅራኔዎች የሚፈታበት
አግባብ ከውጪ ሆኖ ለተመለከተው፤ ፓርቲውን መቀላቀል ማለት በዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት ከመጠርነፍ ባለፈ አዲስ ሐሳብ ማመንጨት
መቻል እንዳልሆነ ይረዳል::




