Thursday, January 30, 2014

የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ፎረም ጠቅላላ ጉባኤ ተካሄደ


በመቋቋም ላይ ያለው ‹‹የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ፎረም›› ትላንት፣ ጥር 21 2006 በአስታራ ሆቴል መሥራች ጠቅላላ ጉባኤ ተካሄደ፡፡ ጠቅላላ ጉባኤው ላይ በፎረሙ መተዳደሪያ ደንብ ላይ ተወያይቶ ያፀደቀ ሲሆን፣ የጠቅላላ ጉባኤ ሰብሳቢ፣  ሥራ አስፈፃሚ እንዲሁም ኦዲተር መርጧል።

ጠቅላላ ጉባኤው ጋዜጠኛ አያሌው አስረስን ሰብሳቢ፣ ጋዜጠኛ ጌታቸው ወርቁን ምክትል ሰብሳቢ፣ እንዲሁም ጋዜጠኛ ብሩክ ከበደን ጸሐፊ አድርጎ መርጧል።

በተጨማሪም፣ በጠቅላላ ጉባኤው ሰብሳቢዎች አስተባባሪነት ሰባት የፎረሙ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ተመርጠዋል፡፡ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ጋዜጠኛ በትረ ያዕቆብን ሊቀመንበር፤ ጋዜጠኛ ስለሺ ሐጎስን ምክትል ሊቀመንበር፤ ጋዜጠኛ ነብዩ ኃይሉን ጸሐፊ፤ ጋዜጠኛ ዘሪሁን ሙሉጌታን የሕዝብ ግንኙነት፤ ጋዜጠኛ ብስራት /ሚካኤልን ትምህርትና ሥልጠና፤ ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩን ሒሳብ ሹም፤ ጋዜጠኛ ሀብታሙ ስዩምን ገንዘብ ያዥ እንዲሆም ጋዜጠኛ ብዙአየሁ ወንድሙን የውስጥ ኦዲት አድርጎ በመምረጥ ቤቱ እንዲወያይበት ያቀረበ ሲሆን የጋዜጠኛ በትረ ያዕቆብን በሊቀመንበርነት መመረጥ ተከትሎ ጋዜጠኛ ዳዊት ሰለሞን ጠንከር ያለ ተቃውሞ ቢያነሳም የጠቅላላ ጉባኤውን ይሁንታ ሳያገኝ በመቅረቱ ተቀባይነት ድልድሉ በአብላጫ ድምፅ ሊፀድቅ ችሏል።

No comments:

Post a Comment