Friday, July 17, 2015

‹‹ፓቬል ኢትዮጵያዊ ቢሆን ኖሮ….?››

በናትናኤል ፈለቀ
ከቂሊንጦ

ወዳጄ በፍቃዱ ኃይሉ በደጉ ዘመን በዞን ፱ ላይካስነበባቸው እና አስደማሚ ከነበሩት ጽሁፎቹ መካከል ግብጻዊው የማኅበራዊ ድረ ገጽ ‹‹አብዮተኛ››  ዋኤል ጎኒም ካሳተመው “Revolution 2.0”  ከሚለው መጽሀፍ ውስጥ ከኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታና የገጠሙትን ሃሳቦች ዋኤል ጎኒም ኢትዮጵያዊ ቢሆን ኖሮ...?   በሚል ርዕስ የግብጻዊውን ሀሳቦች ‹‹በኢትዮጵያኛ›› ተርጉሞ የፃፈው ይገኝበታል፡፡

አሁን ከዚህ በታች የምታነቡት ጽሁፍ ደግሞ በ19ኛውከፍለ ዘመን መጨረሻና በ20ኛው ክፍለዘመን መጀመሪያ አካባቢ በሩሲያ የነበረው ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ እውነታዎች ላይ ተመስርቶስለአንድ ፓቬል ስለተባለ ወጣት ሩሲያዊ አብዮተኛ እውነተኛ ታሪክ ከሚተርከው ‹፣እናት›› በሚል ርዕስ ወደ አማርኛ የተተረጎመ የማክሲም ጎርኪ መጽሀፍ ውስጥ አሁን እየገጠመን ካለው እውነታ ጋርአንድያ የሆኑት ሃሳቦች ተመርጠው የቀረቡበት ነው::

‹‹ፓቬል ኢትዮጵያዊ ቢሆን ኖሮ….?›› ፓቬልን በምናብ ኢትዮጵያዊ አድርገን እንጠይቀዋለን

ስምህ ማነው?

ስሜ በፍቃዱ ኃይሉ ነው

ዕድሜህ ስንት ነው?

ወጣት ነኝ፤ እንደኔ ወጣት የሆኑ ኢትዮጵያውያንወንድሞቼ በሀገራቸው ጉዳይ ያገባኛል የሚል ስሜት እንዲኖራቸው ጥቂት በመሞከሬ ያለስራዬ ስም ተሰጥቶኝ በአሸባሪነት ተከስሼ የወጣትነትዕድሜዬንበእስር እየገደልኩ ነው፡፡

ሊይዙህ ሲመጡ አስደነገጡህ?

ምንም የሚየስደነግጥ ነገር አልነበረውም፤ እንደውምየሚያሳዝነው መሳሪያቸውን በወገባቸው የታጠቁ የሚጋልቡትን ፈረሰ ይመስል ጫማቸው ላይ የፈረስ መኮርኮሪያ ፣ የብረት ጉጥ የለጠፉእና በዕድሜ ትልልቅ የሆኑ ሰዎች ይህንን በመሰለ …ድርጊት ጊዜያቸውን የሚያባክኑ መሆኑ ነው፤ ቢሮ እና ቤት አንዳችም ነገር ሳይቀራቸውያለ የሌለውን በማመሰቃቀል ይበረብራሉ፤ አልጋው ስር ገብተው ፈተሸ ሳጥኑ ውስጥ መጽሀፍ መደርደሪያዎቹን ፈተሸ ጣራ ስር ያለውንቦታ ሳይቀር ፈተሸ ከወዲያ ወዲህ እየተሯሯጡ ሲበረብሩ ፊታቸው የሸረሪት ድር ያደራበት መሰለ፡፡ ከዚያም በመከፋት ተውጠው ደነፉ፣አስፈሪዎች እና ቁጡዎች ለመምሰል….

ማዕከላዊ የነበረውን ነገር እስኪ አጫውተን?

በመጀመሪያ ብዙ የሚደረግ ነገር አልነበረም ቁጭብሎ መጠባበቅ ብቻ ነበር፤ ከዚያም ተጠርቼ በወታደር ታጅቤ ወደ አለቆቻቸው ዘንድ እቀርብ ነበር፡፡ መርማሪዎቹ እና ሹማምንቶቹ ብልሆችአይደሉም፡፡ ብዙ ይለፈልፋሉ፣ በምርመራው ወቅት ከጥፊ አንስቶ እስከ ውስጥ እግር መገረፍ አለ፣ ራቁት ሆኖ መመርመርም ነበር፡፡ከዚያም እንደገና በወታደር ታጅቤ ወደ ማረፊያ ቤት አንድመለስ ይደረጋል፡፡ ምርመራዎቹ ሰዓት አይመርጡም፡፡ በንዲህ አይነት ሁኔታከወዲያ ወዲህ መመላለስ ነበር፡፡

ከባድ በደል ነው የደረሰብህ?

ለመሆኑ በዚች ዓለም ላይ ያልተበደለች ነብስ ትኖራለችእነርሱ እኔን ክፉኛ የበደሉኝ በደል እጅግ የከፋ በመሆኑ ምክንያት ዳግመኛ አላስታውሰውም፤ ሰዎች ይህንን ዓይነት እስከሆኑ ድረስምን ማድረግ እችላለሁ የደረሰብንን በደል የማስታውስ ከሆነ መሥራዬ መሃል ትውስቱ ጣልቃ እየገባ ያውከኛል፡፡ ከዚህም በላይ ልብንበሃዘን ማስተከዝ ጊዜ ማባከን ነው፡፡ ኑሮ አንደሆነ እንደዚህ ነው፡፡ በሰዎች ድርጊት እበሳጭ ነበር፤ በኃላ ሳስተውለው ግን ፋይዳየለውም፡፡

በመታሰር የሚገኝ ነገር አለ?

እደሚመስለኝ ሰው ከእስር ቤት ሲወጣ ይበልጥ የተሻሻለሰው ሆኖ ይወጣል፡፡ እስር ቤት ውስጥ ጥሩ ዕረፍት ይገኛል፡፡ ለማጥናት ለመመራመር ዕድል ይኖራል፡፡ እንደኛ ዓይነት ሰዎች ደግሞከእስር ውጪ እነዚህን ሁለት ጉዳዮች ለማሟላት ጊዜ አይኖረንም፡፡…ምንም እንኳን እስር ቤት መግባት አስደሳች ነው ብዬ ባናገርም…ከእስር ቤት ስወጣ ልቤ እና አእምሮዬ በመርካቱ ደህና እጠቀማለሁ፡፡

የበደሉህ መርማሪዎች የክፋታቸው ምንጭ ምንድንነው?

…የተለዩ ክፉዎች አይደሉም፤ ሕዝብ አዳን ለመቀጥቀጥየተሰሩ መዶሻዎች ናቸው፡፤ እንደኛ የመሳሰሉትን ሰዎች ጸጥ ለጥ በማድረግ እደሚመች አድርጎ ለመግዛት እንዲቻል የሚሰረስሩን እናየሚቦረቡሩን መገዝገዣና መሞረጃ መሳሪያዎች ናቸው፡፡ እነሱ እራሳቸውም ቢሆኑ ለበላይ አለቆቻቸው እንዲመች ተደርገው ተቦርቡረዋል፡፡መለስ አድርፈ,ገው ባለማሰብና ለምን ይህንን አደርጋለሁኝ ብለው እራሳቸውን ባለመጠየቅ የታዘዙትን ሁሉ ይፈፅማሉ፡፡

የምትወዳቸው ሰዎችን ሚስትህ ወላጆችህ ጓደኞችህበመረጥከው የሕይወት መስመር ምክንያት የሚደርስባቸው ሰቆቃና እንግልት አያሳስብህም?

ወደፊት ለመራመድ ከፈለግን አንዳንድ ግዜ ራሳችንን መቃወም አለብን፡፡ ልባችንን በሙሉለመስጠት የምንችል መሆን አለብን፡፡ ሕይወታችንን ለቆምንለት ዓማ መስጠቱ ቀላል ነው፡፡ ከሕይወታች ይበልጥ ውድ የሆነው ለመስጠትምየምንዋጋለት ሐቅ እናጠናክራለን፣ በዓለም ላይ ካለው ነገር ሁሉ እጅግ ተወዳጅ የሆነው ሃቅ እናጠናክራለን፤ የቆምንለት ዓላማ ሲሳካየምንኖርባት ዓለም የተሻለች ቦታ ትሆናለች፡፡ የምንወዳቸው ሰዎች መሻሻል ያለበት ዓለም ላይ መኖራቸው የበለጠ የዓላማ ፅናት ነውየሚሰጠው፡፡

የሚመረምሩህን ፖሊሶች የከሰሳችሁን አቃቤ ሕግደህንነቶቹን ብታገኛቸው ምን ትላቸዋለህ?

… እናንተ ከኛ ይልቅ እንደ ግዞተኞች ማለት ናችሁ፤በላያችሁ ላይ የመንፈስ ባርነት አድሮባችኋል፡፡ እኛ ግን ስጋዊ ባርነት ብቻ ነው ያለብን፡፡ መንፈሳችሁን አኮላሽቶየገደለው አጉል ልምድ እና አጉል አመለካከት ከላያችሁ ላይ አሽቀንጥራችሁ ማስወገድ አትችሉም፡፡

ጉዳያችሁን የያዙት ዳኞችስ?

አንዳቸውምን በግል ማስቀየም አልሻም እንደውም በተገላቢጦሽ፤ እናንተ የፍርድ አፈፃፀምብላችሁ የምትጠቅሱት ይህንን ቅጥፈት እዚህ ቆም ብየየ ሳስተውል ከእናንተ ጋር አብሬ የሃዘናችሁ ተካፋይ ለመሆን ምንም አይረኝ፤ምንም ቢሆን እናንተም ሰብዓዊያን ፍጡሮች ናችሁ፡፡ እኛ ደግሞ፤ ምንም እንኳን እኛ የምንቆምለትን ዓላማ የምትቃወሙ ብትሆኑም ጨካኝለሆነ አገዛዝ እንደዚህ ከሰብዓዊ ክብራችሁ ዝቅ ብላችሁ በመውረድ ተዋርዳችሁ ሰብዓዊ ክብራችሁ ተገፍፎ ስለመለከት ሁልጊዜም ያሳዝነኛል፡፡
Befeqadu Z Hailu and Natnael Feleke Drawings by Melody Sundberg

No comments:

Post a Comment