Tuesday, July 29, 2014

የኢትዮጲያዊነት ውርስና ቅርስ ማኅበረሰብ በሰሜን አሜሪካ ለዞን9 ጦማርያን ሽልማት አበረከተ

#Ethiopia #FreeZone9Bloggers #FreeEdom #FreeTesfalem #FreeAsemamaw 

የኢትዮጲያዊነት ውርስና ቅርስ ማኅበረሰብ በሰሜን አሜሪካ ለዞን9 ጦማርያን ሽልማት አበረከተ 

በሰሜን አሜሪካ የሚገኘው ኢትዮጲያዊነት ውርስና ቅርስ ማኅበረሰብ በእስር ለሚገኙት የዞን 9 ጦማርያን እና ጋዜጠኞች ያልተዘመረላቸው ጀግኖች በሚል በአራተኛው አመታዊ ክብረ በአል ላይ ሽልማትን አበርክቶላቸዋል፡ 

 
በየአመቱ በሚደረገው በዚህ ክብረ በአል መዝጊያ ስነስርአት ላይ የማህበሩ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ አበበ የዞን9 ጦማርያን ከፍተኛ መስዋእትነትን የሚከፈልበትን ሃሳብን አገር ውስጥ ሆኖ እውነትን የመናገርን ሃላፌነት ወስደው እየከፈሉት ላሉት መስዋእትነት እውቅና መስጠት ማስፈለጉን ተናግረዋል።


ይህ ያልተነገረላቸው ጀግኖች በሚለው ምድብ የዞን9 ጦማርያን እና ጋዜጠኞች እውቅና የተሰጣቸው ሲሆን ከዚያ በተጨማሪ ሁለት ተሸላሚዎች ከአገረ አሜሪካን ሽልማት ወስደዋል፡፡

የዞን9 ጦማርያን በታሰሩ ጦማሪ ጓደኞቻችን እና ጋዜጠኞችን ስም ለተሰጠው እውቅና ሽልማት ከፍ ያለ ምስጋና እናቀርባለን፡፡

No comments:

Post a Comment