የዞን9 ጦማርያን አና ጋዜጠኞች ዛሬ ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት መቅረባቸው ተሰማ፡፡
የማእከላዊ ምርመራ ፓሊስ ዛሬ ያለምንም ቅድመ ማስጠንቀቂያ ዛሬ ጠዋት ታሳሪዎቹ ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ማቅረቡ ተሰማ፡፡ ጎብኚ ቤተሰቦችና ጓደኞች ጠዋት ማእከላዊ ምርመራ ሲሄዱ መግባት ያልተፈቀደላቸው ሲሆን ፓሊስ ውስጥ እያንዳንዱን ታሳሪ የሚጠይቅ ሶስት ሰው ስለዚህ መግባት አይቻልም በማለት በማከላከል አንዳይገቡ አድርጓቸዋል፡፡
ነገር ግን ሁሉም ታሳሪዎቸ ለፍርድ ቤቱ የህግ ጠበቃቸው በሌለበት መገኘታቸውን እና መብታቸው መጣሱን ስለዚህ ያለህግ ባለሞያ ምንም አይነት የፍርድ ቤት ሂደት ውስጥ ያለመግባት መብታቸው አንዲጠበቅ በጠየቁት መሰረት ፍርድ ቤቱ የህግ ጠበቃቸው በተገኘበት ችሎቱ ነገ አንዲሰየም ወስኗል፡፡
በመሆኑም 6 ጦማርያን እና 3 ጋዜጠኞች ነገ ጠዋት ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጠበቆቻቸው በተገኙበት ይቀርባሉ ፡፡
ጦማርያን ጓደኞቻችን በምንም ወንጀል ላይ ተሰማርተው አንደማያውቁና ክሱ ሃሳባቸውን በመግለጻቸው ብቻ የተመሰረተ ፓለቲካዊ አንደሆነ እንደሚያምን ለማስታወስ እንወዳለን::
No comments:
Post a Comment