Monday, August 19, 2013

ጋዜጦች ባሳለፍነው ሳምንት

ኢትዮ-ምኅዳር ማክሰኞ ነሐሴ 8/2005 ዓ.ም
 • በእነ ኤልያስ ክፍሌ መዝገብ በሽብርተኝነት ክስ ተፈርዶባቸው በማረሚያ ቤት ከሚገኙት አራቱ ኢትዮጵያውያን መካከል ይቅርታ ጠይቀው የነበሩት ሶስቱ፤ ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ፣ ወ/ሮ ሂሩት ክፍሌ እና አቶ ዘሪሁን ገ/እግዚአብሔር፤ ጥያቄያቸው ከቀረበ ከአንድ ዓመት ቆይታ በኋላ ሐምሌ 25/2005ዓ.ም የይቅርታ ቦርድ ጽ/ቤት ማህተም አርፎበት ለወ/ሮ ሂሩት ክፍሌ በተላከ ደብዳቤ የይቅርታ ጥያቄቸው ለፕሬዝዳንቱ ቀርቦ ውድቅ መደረጉን እንደተገለፃለቸው ነገር ግን የጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ እና የአቶ ዘሪሁም ገ/እግዚአብሔር ግን ምላሽ እንዳልደረሳቸው
 • የአምስት ፓርቲዎች ጥምረት የሆነው የኢትዮጵያ ፌደራላዊ አንድነት መድረክ ቅዳሜ ነሐሴ 1 ቀን 2004ዓ.ም ባካሄደው ጉባዔ ዶ/ር መራራ ጉዲናን ሊቀመንበር አድርጎ መምረጡን እና ለሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት መድረክን እንደሚመሩ
 • አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የፀረ ሽብር ህጉን እንዲሰረዝ የሚያካሂደውን የ3ወር የሚሊዮኖች የነፃነት ድምፅ ንቅናቄ የመጀመሪያው ምዕራፍ ማጠናቀቂያ አስመልክቶ መስከረም 5 ቀን 2006ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ሊያደርግ እንዳቀደ
 • ሁለት የሬድዮ ቢላል ጋዜጠኞች ክስ ሳይመሰረትባቸው ከሣምንት በላይ ታስረው መቆየታቸው እንዳሳሰበው የጋዜጠኞች ተንከባካቢ ቡድን (CPJ) ባለፈው ሳምንት ባወጣው መግለጫ ማሳወቁን
 
የኛ ፕሬስ ማክሰኞ ነሐሴ 8/2005 ዓ.ም
 • ነሐሴ 14/2004ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት የተነጠሉት የጠ/ሚ መለስ ዜናዊ በሥላሴ ካቴድል ቅጥር ግቢ ውድ በሆነ የእምነበረድ አይነት የታነፀው የተቀማጠለ መካነ መቃብር ተጠናቆ በመጪው ሳምንቶች ይመረቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ
 • የወሲብ ድረገፆችን በማሰስ ኢትዮጵያ፤ ስሪላንካን ተከትላ ሁለተኛ መውጣቷን ጎግል የተሰኘው እውቅ ዓለም አቀፍ ተቋም ይፋ ማድረጉን እና ኢትዮጵያ ከቀዳሚዎቹ ተርታ እንድትቀመጥ በዘንድሮ ኣመት በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ ባለው የቢግ ብራዘር አፍካ ውድድር ተሳፊ የነበረችው ቤቲ አበራ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳበረከተች
 • ከስምንት ወር በፊት ለተለያዩ ስልጠናዎች ወደ ደቡብ ኮሪያ ካመሩ 59 ኢትዮጵውያን መካከል 38 ኢትዮጵያውያን የኮርያን መንግስት ጥገኝነት መጠየቃቸውን


ሪፖርተር ነሐሴ 8/2005 ዓ.ም
 • ነሐሴ 2 ቀን 2005 ዓ.ም. 1434ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በእስልምና እምነት ተከታዮች በተለይ በአዲስ አበባ ብሔራዊ ስታዲየም ሲከበር፣ ከፖሊሶች ጋር በተፈጠረ ግጭት በቁጥጥር ሥር ውለው ከነበሩ በርካታ ሰዎች መካከል፣ አብዛኛዎቹ በምክርና በከባድ ማስጠንቀቂያ መለቀቃቸውን ፖሊስ ማታወቁን እና ፍርድ ቤት የቀረቡት የምርመራ ጊዜ እንደተጠየቀባቸው
 • እስከ ነሐሴ 17 ድረስ የሚቆየው የ40/60 ቤቶች ምዝገባ ባለፈው ሰኞ ነሐሴ 6 ቀን 2005 ዓ.ም. አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኙ 116 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎችና መገናኛ አካባቢ ከአምቼ ፊት ለፊት በሚገኘው የአዲስ አበባ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት መጀመሩን

ሠንደቅ ነሐሴ 8/2005 ዓ.ም
 • የመብት ጥያቄ ያነሱ የሙስሊሙ ማኀበረሰብ አካላት ላይ መንግሥት እየወሰደ ያለው የኃይል እርምጃ አጥብቀው እንደሚቃወሙት ሶስት የተቃዋሚ ፓርቲዎች ማለትም የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ)፣ የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ እና የመላ ኦሮሞ ሕዝብ ድርጅት ነሐሴ 5 እና 6 ቀን 2005 ዓ.ም በተናጠል መግለጫ መስጠታቸውን (እና የመግለጫቸውን ሙሉ ቃልም ተካቷል )
 • በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር የሆኑት፤ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ፓርቲ (ኦፌኮ)ሊቀመንበር እና በቅርቡ መድረክ ባካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ የመድረክ ሊቀመንበር ሆነው የተመረጡት ዶ/ር መረራ ጉዲና “የኢትዮጵያ ፖለቲካ ምስቅልቅል ጉዞና የህይወቴ ትዝታዎች” በሚል ርዕስ አዲስ መፅሐፍ ማሳተማቸውን እና ገበያ ላይ መዋሉን 

አድማስ ነሐሴ 11/2005 ዓ.ም

 • ድምፃዊ ኢዮብ መኮንን፣ “ስትሮክ” ተብሎ በሚታወቀው ህመም ቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል ስለመግባቱ እና ለተጨማሪ ህክምና ወደ ኬንያ ስለሚኖረው ጉዞ (ይህ ዜና በአድማስ ጋዜጣ ከወጣ በኋላ ትላንት ማታ ላይ ድምፃዊ እዮብ ኬንያ ሄዶ ህክምናውን እየተከታተለ እያለ ከዚህ ዓለም በሞት  መለየቱ ተሰምቷል፡፡ ነፍስ ይማር!)
 • የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ መምህራን በተማሪዎችና በአስተዳደር መካከል የነበረው ውጥረት እንዲረግብ ጥረት በማድረጋችን በኮሌጁ ቅጽር ግቢ ከሚገኙ መኖርያዎቻችን አለአገባብ ልቀቁ ስለመባላቸው
 • በሳምንት አንድ ቀን ውሃ ማግኘት ብርቅ የሆነባቸው ሰፈሮች፣ በውሃ እጦት አካባቢያቸውን በመጥፎ ጠረን የሚበክሉ የኮንዶሚኒየም መኖሪያዎች፣ ለተደጋጋሚ አቤቱታ ምላሽ ሳያገኙ በርካታ ወራት እየተቆጠሩ  ስለ ሚማረሩ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች
 • አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ፣ በመቀሌና በወላይታ ሶዶ ከተሞች ሠላማዊ ሠልፍና ህዝባዊ ስብሠባ ለማካሄድ የነበረው እቅድ በተለያዩ ጫናዎች መጨናገፉን የፓርቲው ሊቀ መንበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ መግለፃቸውን

የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሽመልስ ከማል ከአድማስ ጋዜጠኛ ጋር ያደረጉት ቃለመጠይቅ ተካቷል፡፡
ለአቶ ሽመልስ ከማ የቀረቡት ጥያቄዎች እና ከምላሹ ውስጥ የተወሰዱ በጥቂቱ፡-

በተቃዋሚ ፓርቲዎች እየተካሄዱ ስላሉ ሰላማዊ ሰልፎች የመንግስት አቋም ምንድነው?

“ተቃዋሚዎች ባይቃወሙና ባይሰባሰቡ ነው እንጂ የሚደንቀው ይህን ማድረጋቸው ብዙም የሚያስደንቅ አይደለም፡፡ ነገር ግን ከሚያነሷቸው ጉዳዮች ውስጥ የበርካታ ዜጐች ስጋት የሆኑ ጉዳዮችም አሉ፡፡ በተለይ ከአክራሪ ጽንፈኛ ሙስሊም ቡድኖች ጋር አንዳንድ ፓርቲዎች የፈፀሙት ያልተቀደሰ ጋብቻ አሳሳቢ ነው፡፡ በሀገራችን ህገመንግስትም ፖለቲካ እና ሃይማኖት የተለያዩ ናቸው፡፡ የፖለቲካ ስብሰባዎች፣ የፖለቲካ ሰልፎች እንኳን ሃይማኖተኞችን ሊቀላቅሉ፣ የሃይማኖት ተግባራት ከሚፈፀምባቸው ቦታዎች በተወሰነ ርቀት መሆን አለባቸው፡፡ አሁን ግን ሁለቱ መቀያየጥ የሌለባቸውን ነገሮች ሲያካሂዱ እያየናቸው ነው፡፡”

“በየአደባባዩ የጠሩትና ሚሊዮኖችን እናስከትላለን ብለው የለፈፉለት ሰላማዊ ሰልፍ፣ በመቶዎችና በአርባዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ይዞላቸው ሲመጣ ያዩ ተቃዋሚዎች፣ ሌላ ሃይል እናገኝበታለን ብለው የገቡበት ስሌት አደገኛ ስሌት ነው፡፡ ከሽብርተኝነት ጋር የተፈጠረ ድሪያ ነው የሚሆነው፡፡ እንዲህ አይነቱን ነገር ሊጠነቀቁ ይገባቸዋል፡፡ መጥፎ አካሄድ ነው፡፡ ካለፈው ስህተታቸው ትምህርት መውሰድ አለባቸው፡፡ ህገመንግስቱ ሲጣስ ዳር ቆሞ የሚመለከት መንግስት አይደለም ያለው፡፡”

በሠልፎቹ ከሚጠየቁት ጉዳዮች መካከል መንግስት ምላሽ ያሻቸዋል ብሎ የተቀበላቸው የሉም? በተለይ ከሰብአዊ መብት አያያዝ ጋር    የሚነሱ ጥያቄዎች ላይ?

“ዝም ብሎ ለፕሮፖጋንዳ ፍጆታ የሚያነሷቸው ካልሆነ በቀር፣ በሰብአዊ መብት አያያዝ በኩል መንግስት የዜጐችን የሰብአዊ መብት አያያዝ አተገባበር በጣም በተጠናከረ መልኩ እያሻሻለና አድማሱን እያሰፋ በመሄድ፣በቅርቡ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት አያያዝ መተግበሪያ (አክሽን ፕላን) ያወጣ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በዚያ ላይ የእያንዳንዱን ዜጋ ዲሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብት ጥበቃ ለማስተግበር የሚያስችሉ ዝርዝር መርሃ ግብሮችን ነው ያወጣው፡፡”

በተለያዩ ከተሞች እየተካሄዱ ያሉት ሰላማዊ ሰልፎች እና ህዝባዊ ስብሰባዎች በመንግስት ላይ ጫና የመፍጠር አቅም የላቸውም?
“እንዴት ነው የሚፈጥሩት! ጐንደር በጠሩት ሰልፍ ላይ 200 የሚሆን ሰው ነው የተገኘው፡፡ በሌሎችም ቦታዎች ተመሳሳይ ነው፡፡ እነሱ “ለምንድነው ስብሰባችን ባዶ የሆነው?”፣ “አዳራሻችን ባዶ የሆነው?” ብለው መጠየቅ አለባቸው፡፡ ጣታቸውን ወደ ውጪ ከመደንቆር ይልቅ የህዝቡን ፍላጐት ማየትና ወደ ውስጣቸው መመልከት አለባቸው፡፡”

“ነገር ግን ይህን ለመሸፋፈን መንግስት ጫና በማድረጉ ሰው ሊወጣልን አልቻለም ሲሉ ነው የሚደመጡት፣ ይሄ መሠረት የሌለው ውንጀላ ነው።”

አንድነት ፓርቲ የፀረ ሽብር አዋጁን በማሰረዝ የሚሊዮኖችን ድምጽ እያሰባሰበ ነው፡፡ የሚሰባሰበው ድምጽ አዋጁን ሊያሰርዘው ይችላል?

“የፀረ ሽብር ህጋችን ከተለያዩ የአለም ሀገራት ተጠንቶ የተቀረፀ ነው፡፡ የዜጐቻችንን ደህንነት ከሽብር ጥቃት ለመከላከል የህግ ከለላ ያስፈልግ ነበር፡፡ በዚህ መሠረት ህጉ ተቀርጿል፡፡ በህጉም እስካሁን ሊከሰቱ ይችሉ የነበሩ አያሌ ሙከራዎችን ማክሸፍ ችለናል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ስጋት የሚገባቸው ወገኖች እነማን እንደሆኑ ጥርጥር የለውም፣ ዜጐች ግን ስጋት ላይ አይወድቁም፡፡ ህጋዊ ፓርቲዎችንም ስጋት ላይ አይጥልም፡፡ ተገቢ የሆነውንና ያልሆነውን አጣቅሶ ለመሄድ ያሰበ ካለ ግን ድንጋጌው ስጋት ላይ ሊጥለው ይችላል፡፡ ዜጐች ግን ሙሉ ድጋፍ የሰጡት ህግ ነው፡፡”

ህጉን ድምጽ በማሰባሰብ ማሰረዝ አይቻልም ማለት ነው?

“ህግ የሚወጣው በህግ አውጪ አካላት ነው። እነዚህ አካላት ከማውጣቱ ባሻገር ህጉን መሻርም ማሻሻልም ይችላሉ፡፡ እነዚህ ድርጅቶች የህግ የበላይነት ለማክበርና ለህገመንግስታዊ ስርአት እውቅና ለመስጠት የሚያንገሸግሻቸው ተቋማት እንደሆኑ እናውቃለን፡፡ ህገመንግስታዊ ተቋማትንና ህጋዊ አሠራሮችን ለመቀበል የማይፈልጉ ፓርቲዎች ናቸው ይህን የሚያደርጉት፡፡”

ሪፖርተር ነሐሴ 12/2005
 • የአክሰስ ሪል ስቴት የቦርድ ሊቀመንበርና ዋና ሥራ አስኪያጅ የነበሩት አቶ ኤርሚያስ አመልጋ በዚህ ወር መጨረሻ ስለመምጠታቸው እና ለአክሰስ ሪል ስቴት 40 ከመቶ ድርሻውን የሰጠውና 60 በመቶ የሚሆነው ከፍተኛ ባለድርሻ የሆነው ፓስፊክ ሊንክ ኢትዮጵያ ሪል ስቴት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ‹‹ከአክሰስ ሪል ስቴት ጋር በመሆን ቪላና አፓርትመንት እገነባላችኋለሁ በማለት ውል ካስገባን በኋላ ውላችን ሳይፈጸምልን ገንዘባችንን ከወሰደ አንድ ዓመት ሞልቶታል፤›› በሚል፣ 137 ደንበኞች የ73,388,844 ብር ከ50 ሳንቲም ክስ መመስረት 
 • የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በቅርቡ በሕግ በተፈቀደለት የፋይናንስ ኪራይ (ፋይናንስ ሊዝ) አገልግሎት መሠረት፣ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ አገልግሎት ወይም ለምርትና ለአገልግሎት የሚውሉ ማሽኖችንና ተሽከርካሪዎችን ለማከራየት ለሚፈልጉ ኩባንያዎች ፈቃድ ለመስጠት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን
 • የህንዱ ኩባንያ ካራቱሪ አግሮ ፕሮዳክትስ፣ የሼክ መሐመድ አል አሙዲ ሳዑዲ ስታርን ጨምሮ ሰፋፊ የግብርና መሬት ወስደው ያላለሙ ኩባንያዎችን መሬት መንግሥት መንጠቅ ሊጀምር መሆኑን

No comments:

Post a Comment