በብርካን ፋንታ
“ሁላችን ከሆንን የቋንቋ ፈላስፋ
በተግባር መስካሪ አንድም እንዳይጠፋ”
ይህ የእዮብ መኮንን ዘፈን ግጥም የዚህን ጽሑፍ ገዢ ሐሳብ ይገልፃል፡፡ ሲነገር ከንፈር የማያደናቅፍ፣ ሲደመጥ ጆሮ የማይኮረኩር፣ በአዕምሮ ሲሰላሰል የማይጎረብጥ በተግባር መሬት ላይ የማይተገብሩት የአፍ ፈሊጥ /leap service/ በከተማችን በርክቷል፡፡ በጊዜ ብዙ ሰዎችን ታዝበናል፡፡ “ድሮም ትልቅ ነበርክ” የሚል የግጥም ፉካሬ በጌትነት እንየው ከመስማት በላይ፣ በፍትህ ጋዜጣ “መንግስት መዶሻ ነው፤ ሕዝብ ደግሞ ምስማር” ሲለን ከነበረ አምደኛ “ግድቡ በአቶ መለስ ይሰይም”፣ “ምስላቸው በብር ይታተም” የሚል ጭብጥ የያዘን ተውኔት ድርሰት ከማየት በላይ፤ ወደ መልካምም ወደ ክፉም አገራችንን በሚመራው በዛች ቀውጢ ሰዐት ፍፁም ከሚያምኑት “Meles Zenawi is back in town” የሚል ዘገባ ከማንበብ በላይ፤ “አገር ማለት የኔ ልጅ” የሚል ውብና ጥልቅ መልዕክት ያለው ግጥም ገጣሚ ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ በፍትህ ጋዜጣ አምደኛ በሆኑ ማግስት ለጠ/ሚሩ መታሰብያ ግጥም መድረክ ላይ ሲያነበንቡ ከማየት በላይ ሌላ የመከዳት ስሜት የሚፈጥር ምን ነገር አለ?! ምንም የለም!
ይህ ጽሑፍ የአቶ መለስ ዜናዊን መልካም ያልሆነ አስተዳደር ለመተችት የተነሳ አይደለም፡፡ ወትሮም አቶ መለስ በሕይወት በነበሩበት ጊዜ የሚበጀንን ነው የሚያደርጉት ብለው ሲሞግቱ ለነበሩትም አይደለም፡፡ ክፉ ናቸው፤ በደለኛ ናቸው የሚል ወንጀል ሲያቀርቡ የነበሩት ሲሞቱ ደግሞ በተቃራኒው መላዕክትነታቸውን ሲሰብኩ ለከረሙት ታዝበናል፣ አይተናል ለማለት ነው፡፡ የቀድሞ ጠ/ሚ ተፈጥሯዊ ሞት የአንዳንድ ግለሰቦች ጭንብል አስወለቀ እንጂ ይህ ችግር በአደባባይ መታየት ከጀመረ ሰንበቷል፡፡ አቶ መለስ ዜናዊ ራሳቸው የተሳተፉበት “እንደገና” የተሰኝ ዘጋቢ ፊልም ላይ እንዲህም የሚል የአፍ ፈሊጦችን አድምጠን ነበረ፡፡
“ዋናው ሕሊና ነው… ሕሊና ደግሞ ከሁሉም በላይ ነው መሆን ያለበት! ፍትሕ፣ ስርዓት ሁል ጊዜ ፐርፌክት አካሄድ ከሄደ በዚች ምድር፣ በዚች አገር ምንም አይከሰትም፡፡”
(አትሌት ኃይሌ ገ/ሥላሴ)
ይህን የተናገረው በ1997 ምርጫ ምክንያት በታሰሩ የፓለቲካ እስረኞች እና መንግስት መሐል በሽምግልና የተሰየመው አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገ/ሥላሴ ነው፡፡ ወዳጄ እንደሚለው ኃይሌ እግረ ብርሃን እንጂ ልበ ብርሃን እንዳልሆነ አልዘነጋሁም፡፡ ሆኖም ግን በአፈጠጠ እውነት ላይ ተደራድሮ እስረኞቹን የ12 ዓመት ሕፃን ባንክ እንዲዘርፍ ልከን አሳስተን ነው ያስገደልነው የሚል የይቅርታ ሰነድ ሕሊናው እየተመለከተ ፈርመዋል፡፡ ያን ጊዜ ሕሊናውን ከወዴት ሰውሮት እንደነበረ አላውቅም፡፡ በየትኛው የሞራል እርከን ላይ ቆሞ ሰለሕሊና እንደሚሰብክም አይገባኝም፡፡ ዛሬ የስፖርት ጋዜጠኛ ፍስሐ ተገኝና የመሳሰሉት ሕሊና እያለን ያልተፈፀመውን የ11 ዓመት ታዳጊ ባንክ ሊዘርፍ ነበር የሚል ዜና አላነብም ሲሉ ከአገር ተሰደው እየኖሩ ነው፤ እነኃይሌ በአንፃሩ ዋናው ነገር ሕሊና ነው እያሉን ነው፡፡ ታዲይ ይህ ምንድን ነው… ይህ የአፍ ፈሊጥ ነው፡፡