Sunday, May 13, 2012

እንኳን ወደዞን ዘጠኝ በደህና መጡ!

ይህ ዞን ዘጠኝ ነው! በዞን ዘጠኝ ኢትዮጵያ ሐሳቦች በጽሁፍ ይንሸራሸራሉ፡፡ ለኢትዮጵያ ፖለቲካ የሚበጁ ምክረ ሐሳቦች ይነሳሉ፤ ይጣላሉ፡፡ መንግስት ይወቀሳል፣ ይተቻል፣ ይከሰሳል፡፡ ለታላቂቷ ኢትዮጵያ የሚበጅ መልካም ሐሳብ ካልዎት - እባክዎ ከኛ ጋር በዞን ዘጠኝ ላይ ይጻፉ፡፡

1 comment:

  1. በአቤ ቶኪቻው መስኮት ላይ አድራሻችሁ ባናይና በአቤ አስተዋዋቂነት ባናውቃችሁ ኖሮ እነዚህ ደግሞ እነማን ናቸው ብለን ግራ እንጋባ ነበር፡፡ የወገን ድምጽ ናችሁ ብለን ተስፋ አድርገናልና እንኳን ደህና መጣችሁ፡፡ ድንቁርናን በሳንሱር፣ በጃሚንግ፣ በማስፈራራትና የሚናገሩን በስድብ ዝብ በማስባል የድንቁርና ዓለም በመፍጠር ባላዋቂቀዎች መካከል ጥበበኛ ሆነው ለመታየት የሚፈልጉ ገዥዎች በገነኑበት ጊዜ ሐቁንና ቁርጡን የሚነግር ሁነኛ ወዳጅ ማግኘት ከሰማይ የወረደ ከበረከት እንደማግኘት ይቆጠራል፡፡
    ከሰለሞን ተካልኝን ከለከፈው ቫይረስ ይሰውራችሁ፡ ያ ቫይረስ ወዮልህ ወያኔ ከማለት ቅንድቡ ያማረ ወያኔ ወደ ማስባል ያወርዳል፣ ያዋርዳል፡፡ ቫይረሱ የሚተላለፈው ከልክ በላይ ራስን አዋቂና ታጋይ አድርጎ ከማየት ነው ማለት ይቻላል፡፡ እንዲህ ዓይነት አመለካከት በሰው ላይ ካሰፈረ ያው አጋንንት የሰፈረበት ዓይነት ፍጥረት ይፈጠራል፡፡ ሌላው የቫይረሱ መተላለፊያ ገንዘብ ወይም ክብርን መውደድ፣ አገርና ሕዝብ እየተናደ ልጥገብ ማለት፣ አገርንና ሕዝብን ሸጨም ቢሆን ገንዘብ ላግኝ ማለት ወዘተ ናቸው፡፡
    አቤ ገላጋይ የሚያሸልም ስራ አልሰራም፡፡ አበበ ያኔ የተናገረው ለአቶ መለስ ብቻ አይደለም፡፡ ጥሪ ላደረጉት ሰዎችም እንጅ፣ እዚያ ተሰባስበው ስለ ምግብ ለማውራት ነፃነትን ችላ ላሉ መሪዎች ሁሉ እንጅ፡፡ አበበ ገላጋይ ለአገሩና ለወገኖቹ ማድረግ የሚችለውን በከፍተኛው ቦታ አደረገ፤ አበበ ከዚህ በኋላ በተመሳሳይ ቦታና ሁኔታ ለመገኘት ከአሜሪካ መንገስት ጥሪ እንዳይደረግለት የሚያደርግ ስራ ሰርቶ ሊሆን ይችላል፡፡ ኋይት ሃውስ ውስጥ ዓመድን ቡን የሚያደርግ ጥያቄ ሰንዝረው ወደ ኋይት ሃውስ ዝር እንዳይሉ የተከለከሉ ብዙ ናቸው፡፡ አበበ ገላጋይም ለኢትዮጵያና ለሕቧቿ ሲል ይህን መስዋዕትነት ከፍሎ ሊሆን ይችላል፡፡ አቤ Meles is a dictator ሲል ለመለስ እየተናገር አልነበረም ለኦባማ እንጅ፡፡ አቤ ስለ ነፃነትና ስለ ምግብ ሲናገር ረሃባችንን በሚገባ ለሚያውቀው ለገዥአችን እየተናገረ አይደለም፣ ለአፍሪካ ዳቦ እንጅ ነፃነትና ዲሞክራሲ ምን ያደርግለታል ለሚሉ ፖለቲከኞች እንጅ፡፡ ከ1997 ዓም ምርጫ ተከትሎ በመጡት ቀናት ከኛ ገዥዎች ጋር መሞዳሞዳቸውን ሕጋዊ ለማድረግ ያሰቡ የአሜሪካና የአውሮፓ ባለስልጣናት በአፍሪካ ዲሞክራሲን ማንገስ ከባድ ነው፣ ሕዝቡ ለዚህ ዝግጁ አይደለም፣ አፍሪካ በቀጣዩ 100 ዓመት ዲሞክራሲን በሙሉ ዓይኗ ላታይ ትችላለች ሲሉን ነበር በኋላ፡፡ እናም የአበበ መልዕክት ለነዚህ ሁሉ ነው፡፡ እናንተም ምንም ነገር አያንበርክካችሁ፣ በምታገኙት አጋጣሚ ቢያንስ ቢያንስ አንድ የማያልፍ ስራ ለመስራት ቆርጣችሁ ተነሱ፡፡ ከቻላችሁ ደጋግሙት፡፡

    ReplyDelete