ፍቃዱ አንዳርጌ
ዞን 9 በተባለዉ የመወያያ መድረክ ላይ ብዙ ጠቃሚ ሃሳቦች በተለያዩ ፅሃፊዎች እየተነሱ ሲብራሩና ለዉይይት ሲቀርቡ እከታተላለዉ ይበል የሚያሰኝም ነዉ :: እንደ አስተያየት ግን በየጊዜዉ የሚነሱ ሃሳቦች እንደ ቆዳ እየለፉ ማለፍ እንዳለበት ይሰማኛል፡፡
ዛሬ እኔም የማህሌት ፋንታሁን “የፍርሃት ዘመን” የሚለዉን መጣጥፍ አንብቤ ከሃሳቧ ላይ ሃሳቤን መጨመር ፈለኩ ፡- ማህሌት በፅሁፏ የዘረዘረቻቸዉ የህብረተሰብ ክፍሎች ማለትም “ተማሪዎች፣ሰራተኞች ፣አሰሪዎችና ባለሃብቶች ፍርሃት መር ኑሮ ለመኖራቸዉ ተማሪዉ ተመርቆ ስራ አጥ እንዳይሆን፣ ሰራተኞች የስራ ዋስትናቸዉን፣ እድገት እና የትምህርት እድል የሚያገኙት በመፍራት ስለሆነ፣ አሰሪዎች ከቀዳሚ አለቆቻቸዉ ሞገስን እና ጥቅማጥቅምን ያገኙ ዘንድ እነሱዉ እራሳቸዉ ፈርተዉ ሰራተኞችን የፍርሃት ሀሁ ማስቆጠር ስላለባቸዉ እና በቁስ ቀዳሚነትም ያመኑት ባለሃብቶችም ቢሆኑ ጣሪያ የሌለዉ ፍላጎታቸዉ ይሞላ ዘንድ የፍርሃት መንፈስ ይጠናወታቸዋል፡፡” ብላለች፡፡
እኔም ሁሉም ሳይፈልግ ወደ ፍርሃት ዓለም የሚያደረገዉ ጎዞ መነሻዉ የእዉቀት፣የምክንያት እና ፍላጎት ያለመመጣጠን እንደ ሆነ እና መጨረሻዉም “የፍርሃት ማህበረሰብ”(fear society) መፈጠር ሊሆን እንደሚችል አምናለሁ ፡፡ በፍርሃት እሳቤ የተከበበ ማህበረሰብ ደግሞ የተቃወሰ ማህበራዊ ስሪት ስለሚኖረዉ ለመጪዉ ትዉልድ ሊያስተላልፈዉ የሚችል ባዶ የፍርሃት መንፈስን ብቻ ነዉ፡፡ እዉቁ ፈላስፋ “ፕላቶ” የሰዉ ልጅ የተስተካከለ፣ ጤናማ እና ከፍርሃት የፀዳ ምክንያታዊ ስብዕና ይኖረዉ ዘንድ ሊሟሉ ይገባል ያላቸዉን ነገሮችን ዘርዝሯል፡፡ እኛም “ፍርሃት” ከስነ ልቦና ስሪታችን ጋር የተያያዘ ስለሆነ የሊቁን ስራ በከፊል እንመልከተዉ እንዲህም ይላል “የሰዉ ልጅ አካለዊና ስነ ልቦናዊ ስሪቱ የተስተካከለ ሊሆን ግድ ይለዋል፡፡ የሰዉን ልጅ የነፍስ ሁነት ከሶስት ከፍሎ ማዬት ይቻላል፡፡ የመጀመሪያዉ “ምክንያታዊ” ክፍል ሲሆን አንድ ሰዉ እንዲጠይቅ፣ እንዲያዉቅ ፣እንዲከራከር እና ሃሳቡን እንዲገልፅ የሚያደርግ ክፍል ሲሆን፤ ሁለተኛዉ “መንፈሳዊ ክፍል” የሚለዉ ሲሆን ደግሞ አንድ ሰዉ መልካም ፈቃዱን የሚሰጥበት እና የፍርሃት እና የድፍረት ስሜቱ የሚብላሉበት ክፍል ነዉ፡፡ ሶስተኛዉ ፍላጎትን መሰረት ያደረገዉ ፍላጎታችን የሚርመሰመስበት ክፍል ሲሆን የምግብ፣የመጠጥ፣የወሲብ፣ የሃብትና መሳሰሉ ፍላጎታችን ማንፀባረቂያ ክፍል ነዉ፡፡” ይቀጥልናም “የአንድ ሰዉ የተስተካከለ ስብዕና ይኖረዉ ዘንድ የእነዚህ ክፍሎች የተመጣጠናና የተስማማ አካሄድ ሊኖራቸዉ ግድ ነዉ” ይለናል፡፡