Sunday, November 18, 2012

ጋዜጦች እና መጽሔቶቻችን ከሰኞ እስከ ሰኞ (ከሕዳር 3 – 9፣ 2005)


አዲስ ታይምስ መጽሔት በቅፅ 2 ቁጥር 8 እትም የተመስገን ደሳለኝ ‹ኢህአዴግ ይስነጠቃል?› ጥያቄ እውነት ከሆነ የመሰንጠቁ ፍራሽ ዜጎች ላይ ወድቆ እንዳይፈነክተን መጠንቀቅ ይኖርብናል፡፡ የእኔ እምነት ሲጠናቀቅ ከኢህአዴግ ስንጥቅ ለወግ የሚበቃ ቡድን አይወለድም የሚል ነው፡፡ እስኪ እናንተም አስቡት የኢህአዴግ አባል መሆን አያሳዝንም?›› ‹‹ከኢህአዴግ መሰንጠቅ ተስፋ የለም!›› በሚል ርዕስ ከተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ የመጽሔቷ ዋና አዘጋጅ ቀደም ብሎ ላሳተመው ጽሑፍ የሰጡት መልስ፡፡
ይህቺው መጽሔት ‹የእስላም ኢትዮጵያውያን የትግል ስልት› በሚል ርዕስ የፕ/ሮ መስፍን ወልደማሪያምን ፅሑፍ ይዛ ወጥታለች፡፡ ፕ/ሮ መስፍን ጉዳዩን ለሁሉም ግልጽ እንዲሆን እነዚህን ጥያቄዎች አንስተዋል ‹‹…የኢትዮጵያ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን ምእመናን ከነገጀምሮ የሉተራን ቤተክርስትያንን ሥርዓት ተከተሉ ቢባሉ አንደኛ የኢትዮጵያ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን (ካለች) ምን ትላለች? ሁለተኛ የኢትዮጵያ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን ምእመናን ምን ይላሉ?››

‹‹የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች እና የመብት ተከራካሪዎች ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የሰብዐዊ መብት ጉባዔ አባል እንድትሆን መመረጧን ተቹ›› በሚል ርዕስ THE SUB-SAHARAN INFORMER ባወጣው ዜና የሰብዐዊ መብት ጉባዔ (የቀድሞ ኢሰመጉ) ዲያሪክተርን ጠቅሷል፡፡ ዲሪክተሩ አቶ እንዳልካቸው ሞላ ስለጉዳዩ ሲያብራሩ ‹‹ኢትዮጵያ የጉባዔው አባል መሆን አይገባትም፡፡ በሆነው ነገር ተደንቀናል፡፡ ኢትዮጵያ የተመድሰ ብዐዊ መብት ጉባዔ አባል እንድትሆን ተቀባይነት ማግኘቷ አስደንጋጭ ነው፡፡›› ብለዋል፡፡

‹‹…[ኦሮሞ ሕዝብ ኮንግረስ] ብትወስድ የኢሕአዴግ አባል ድርጅት ከሆነው ኦሕዴድ በጣም የተሻለፕሮግራም ነው ያለው፡፡ የመምረጥና የመወሰን ጉዳይ ግን የሕዝብ ብቻ ነው፡፡›› ዶ/ር መራራ ጉዲና ከሪፖርተር ጋዜጣ ‹‹ቅርበት ያላቸው ታዛቢዎች የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች አገርን ለመምራት የሚያስችል የአመራር አቅም፣ ግልጽ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ፕሮግራም የላቸውም ይላሉ፡፡›› በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ የሰጡት መልስ፡፡

የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና የአንዷለም አራጌ የንብረት ይወረስ ጥያቄ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠው - ሰንደቅ

‹‹ለትምህርት ስርዓታችን ህልውና ከፖለቲካዊ ብልጠት ይልቅ ብልህነት ያሻል›› - አቶ ሙሼ ሰሙ አዲስአድማስ

የዋልድባ መነኮሳት ኳሬዳ በተሰኘ ትልናምስጥ ተቸግረዋል - አዲስአድማስ

Norway refuses to grant Ethiopia’s fingerprint request of over 400 refugies – The Reporter

Zemen Bank Looking to Foreclose Holland Car - Capital

ርዕስአንቀጾች
የኢትዮጵያን ሕዝብ ለጨፈጨፈው ፋሽስት ግራዚያኒ መታሰቢያ መናፈሻና ሙዚየም መገንባቱን በመቃወም የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ድምፃቸውን ያስተጋቡ! - ሪፖርተር (ረቡዕ)
ምርጫ ቦርድ በሕግ በተሰጠው ኃላፊነት መሰረት የውድድር ሜዳውን ማስተካከል ይገባዋል - ሰንደቅ
The Melancholy Face of the Nile – The Sub Saharan Informer
ከመለስ ራዕይ ፈቀቅ እንበል! - አዲስ ታይምስ መጽሔት
አገርን መውደድና እውነቱን ማወቅ - አዲስጉዳይ
ይወልደዋል ከተባለይ መስለዋል ማለት አይገድም - አዲስአድማስ
ግልጽነትና ተጠያቂነት የመልካም አስተዳደር ወሳኝ መሣሪያዎች ናቸው - ሪፖርተር (እሁድ)
Creditism and Capitalism - Capital

No comments:

Post a Comment