በዘላለም ክብረት
በሰዎች የእድገት መሰላል በተለምዶ ‹ሃያዎቹ›
(twentysomethings) የሚባለው የዕድሜ ክልል እጅግ ወሳኝ እንደሆኑ ብዙ ጥናት መጥቀስ ይቻላል፡፡ ሰዎች ከልጅነት ጊዜያቸው
ወደ ጉልምስና የሚሸጋገሩበት ጊዜ መሆኑም ነው የወሳኝነቱ መነሻ፡፡ ይሄን ወሳኝ የዕድሜ ክልል ገና ሲጀምረው በ21 ዓመቱ ወደ እስር
የተወረወረው አፍላው ወጣት መረራ ጉዲና ከ7 ዓመታት እስር በኋላ የዛኔው የደርግ ምክትል ፕሬዝደንት ፍስሃ ደስታ ‹‹እንኳን ደስ
አላችሁ የኢትዮጵያ አብዮትን ለተወሰነ የታሪክ ወቅት አብረን ስንመራ ቆይተን ዛሬ አብዮታችን የላቀ ዘላቂ ድል ሲጎናፀፍ የደስታው
ተካፋይ እንድትሆኑ በምህረት ፈተናችኋል›› ብለው መስከረም 02፣ 1977 ከሌሎች መቶ የሚሆኑ የፖለቲካ እስረኞች ጋር ሲለቀቅ ዕድሜው
28 ደርሶ ነበር፡፡ ወሳኞቹ ‹ሃያዎቹ› እንደዋዛ በእስር አለፉ፡፡ የደርግን አብዮታዊ ድግስ ለማድመቅ ‹በምህረት› ከእስር የተፈታው
መረራ፤ ይህ ከሆነ ከ32 ዓመታት በኋላ ተመልሶ ‹ሃያዎቹን› ወዳሳለፈበት ወህኒ ከተወረወረ ይሄው አንድ ዓመት ሞላው፡፡ በእነዚህ
32 ዓመታት ውስጥ ያቋረጠውን ትምህርት አጠናቆ፣ ብዙዎችን አስተምሮ፣ እንዲሁም ‹ታሟል› የሚለውን የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከበሽታው
ያገግም ዘንድ የቻለውን ሁሉ፤ በመሰለው መንገድ አድርጓል፡፡ ለዚህ ልፋቱ ክፍያው እስር መሆኑ ደግሞ አሳዛኙ የአገሪቱ ምሥል ማሳያ ነው፡፡
መረራ ጉዲና |
መረራ አሁን እስር ቤት ነው፡፡ መረራ የታሰረበትን አንደኛ ዓመት አስመልክቶ
መረራ ላይ ከቀረቡበት ሦስት ክሶች አንዱን ከነማስረጃው ዘርዘር አድርገን በማየት የክሶቹን መነሻና ዓላማ ለመመልከት ብንሞክር የመረራን
ንጽሕና የበለጠ ለመረዳት እንዲሁም መረራን ለማሰር የተሄደበትን ረጅም ርቀት እንረዳለን፡፡
የፌደራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ዶ/ር መረራ ጉዲና ላይ ሦስት የተለያዩ ክሶችን
ያቀረበ ሲሆን የመጀመሪያው ክስ የፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉ እንዲህ እንደዛሬ የሁሉም የፖለቲከኛ እስረኞች የክስ መነሾ ከመሆኑ በፊት
ለብዙ የፖለቲካ እስረኞች የእስር ምክንያት ሁኖ የኖረው በወንጀል ሕጉ አንቀፅ 238 ላይ ‹‹ሕገ-መንግስቱንና ሕገ-መንግስታዊ ሥርዓቱን
በኃይል ለማስወገድ መሞከር›› ተብሎ የተደነገገው ነው፡፡ ዶ/ር መረራ ጉዲና ‹‹በአጠቃላይ በአለፉት ሦስት ዓመታት ውስጥ በኦሮሚያ
ክልል ውስጥ ሲካሔዱ የነበሩትን ተቃውሞዎች ሁሉ አስተባብሯል›› ተብሎም ነው ክስ የቀረበበት፡፡ ሁለተኛው የዶ/ር መረራ ክስ ከአስር
ወራት ትግበራ በኋላ ለተነሳው የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ መነሻ የሆነው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን የሚያጣቅስ ሲሆን፤ ዶ/ር መረራ ‹በጥቅምትና
ሕዳር 2009 አውሮፓ በነበሩበት ወቅት ቤልጅየም ውስጥ አዋጁን በመጣስ ‹‹ከአሸባሪዎች ጋር ተገናኝተዋል›› የሚልም ነው የክሱ
ፍሬ ነገር በአጭሩ፡፡ ‹‹ሕገ-መንግስቱን የሚያከብር ሕገ-መንግስታዊ ሥርዓት ብቻ ነው ለአገሪቱ መድኅን የሚሆናት›› እያለ የፖለቲካ
ዕድሜውን ለገፋው መረራ ጉዲና ‹‹ሕገ-መንግስታዊ ሥርዓቱን ለማፍረስ ሞክረኻል›› ብሎ ክስ ማቅረቡ የከሳሾን ማንነት ከማሳየት ባለፈ
በትንተና ጊዜ ሊጠፋበት የሚገባ ጉዳይ አይደለም፡፡ በተመሳሳይ በሁለተኛው ክስ ላይ ‹ተጣሰ› የተባለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከተሻረ
ወራት ቢያልፉትም ዶ/ር መረራ ግን ያለምንም ሕጋዊ መነሻ አስከአሁን ድረስ የተሻረው አዋጅ ተጠቅሶ የቀረበበት ክስ የዋስትና መብቱን
አስከልክሎት በእስር ላይ ይገኛል፡፡
ከእነዚህ ሁለት ክሶች ባለፈ ዶ/ር መረራ ላይ በሦስተኝነት የቀረበው ክስ
ነው ስለአጠቃላዩ የክሶቹ ዓላማ እና ሒደት የሚያስረዳን፡፡ ዶ/ር መረራ ከተከሰሰባቸው ሦስት ክሶች ውስጥ በሦስተኝነት የቀረበው
ክስ ብዙ ነገሮችን ወደኋላ ሒደን እንድናይ የሚያደርግና የመረራን አሳሪዎች ምን ያክል ርቀት እንደተጓዙ አመላካች ነው፡፡ በዶ/ር
መረራ ላይ የቀረበው ሦስተኛ ክስ ‹‹በ1996 ዓም የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀፅ 486/ለ ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ›› የሚል ሲሆን፤
ዝርዝሩም፡
ተከሳሽ ጥርጣሬን የሚፈጥር የሃሰት ወሬ ለማውራት በማሰብ የኢትዮጵያና የናይጄሪያ ብሄራዊ ቡድን ጥቅምት ወር 2ዐዐ6 ዓም በአዲስ አበባ ስታዲየም ከቀኑ በ1ዐ፡ዐዐ ሰዓት በሚያደርጉት ጨዋታ የአልሸባብ የሽብር ቡድን አባል የሆኑት እነ አብዱራህማን መሃመድ ጥቃት ለማድረስ በዝግጅት ላይ እያሉ የፀጥታ ሃይሎች በነበረው ጥብቅ ጥበቃ ምክንያት የሽብር ቡድኑ አባሎች ታጥቀውት የነበረውን ፈንጂ በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክ/ከ ቀበሌ ዐ1 ፈንድቶ የሽብር ቡድኑ አባሎች የሞቱ መሆኑ እየታወቀ ተከሳሽ በ21/2/2ዐዐ6 ዓም ለአሜሪካ ድምፅ ራድዮ ጣቢያ በሰጡት መግለጫ አሸባሪዎቹ አፈነዱ የተባለው የውሸትና የመንግስት ድራማ ነው በማለት የገለፁ በመሆኑ በፈፀሙት ሕዝቡ በመንግስት ላይ እምነት እንዳይኖረው የሚያደርግ የሐሰት ወሬዎችን ማውራት ወንጀል ተከሰዋል፡፡
የሚል ነው፡፡
ከዚህ ክስ ጀርባ ብዙ ነገሮች አሉና እያንዳንዱን የክሱን አንጓ መመልከት ስለአጠቃላዩ የክሶቹ መንፈስ ብዙ የሚለን ነገር
ይኖራል፡፡
በመጀመሪያ ክሱ የቀረበበት ጊዜ አስገራሚ ነው፡፡ ዶ/ር መረራ ጉዲና በጥቅምት 21/2/2006፤ ከሦስት ዓመታት በፊት
ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ተናገሩት የተባለው ሐሳባቸው ነው ‹‹ጥርጣሬን የሚፈጥር የሃሰት ወሬ ለማውራት›› የሚል ክስ ያስቀረበባቸው፡፡ ከሣሽ ከሦስት ዓመታት በላይ ምን
ሲጠብቅ ቆይቶ ክሱን እንዳቀረበባቸው የሚያውቀው ራሱ ከሳሽ ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን ይህ ሒደት የሚነግረን ከጀርባው ሲውጠነጠን የነበረው
ሐሳብ ነው፡፡ የጉዳዩ አመጣጥ ባጭሩ እንዲህ ነው፡፡
ጥቅምት 03፣ 2006 ከሰዓት በኋላ የኢትዮጵያ መንግስት የዜና ምንጮች አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በተለምዶ ቦሌ ሚካኤል
እየተባለ የሚታወቀው አካባቢ ሁለት ሶማሊያዊያን ‹አሸባሪዎች› የኢትዮጵያና የናይጀሪያን ጨዋታ ለመመልከት የወጣው ሕዝብ ላይ የአጥፍቶ
መጥፋት ፍንዳታ ለመፈፀም እየተዘጋጁ እያለ የአንደኛው ቦምብ ራሱ ላይ ፈንድቶ ሁለቱም ‹አሸባሪዎች› መሞታቸውን የሚገልፅ ዜና ይዘው
ወጡ፡፡ በወቅቱ መንግስታዊ የዜና ማሰራጫዎች ስለሽብርተኝነት አስከፊነት የተለያዩ ዘገባዎችን ከመስራታቸውም ባለፈ፤ የተለያዩ ተቃዋሚዎችን
በማናገር በዜናዎቻቸው ይዘው ወጡ፡፡ በወቅቱ አንዳንድ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ፓርላማው በአስቸኳይ ተሰብስቦ የፀረ-ሽብርተኝነት
ሕጉን የበለጠ ጥብቅ እንዲያደርገው ጠየቁ፡፡ እንደ አንድ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ዶ/ር መረራ በወቅቱ በመንግስታዊው የዛኔው ኢትዮጵያ
ቴሌቪዥን የዛሬው የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ስለጉዳዩ ጥያቄ አቀረበለት፡፡ ዶ/ር መረራም ተቆራርጦ በቀረበው መልሱ “ሰው
አንዳንድ ጊዜ የኢትዮጵያ መንግስት ለራሱ ፖለቲካ ብሎ የሚያደርገው ያው የለመደው ስራ ነው ይላል … አጥፍቶ ጠፊ አጥፍቶ ይጠፋል
እንጂ በሜዳ ዝም ብሎ አያጠፋም” የሚል ጥርጣሬ ያዘለ መልስ ሰጡ፡፡
በወቅቱ የዜናውን ተዓማኒነት የተጠራጠሩት ዶ/ር መረራ ብቻ ሳይሆን ብዙዎች ነበሩ፡፡ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ‹የአጥፍቶ
መጥፋቱን ሙከራ ሊያደርጉ ሲሉ ሞቱ› ያላቸውን በወቅቱ ስማቸው ያልተጠቀሰ (በኋላ በእነ መሐመድ አብዱራህማን እና የፌደራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ክስ መዝገብ ላይ አብዲና ሐሰን እንደሚባሉ የተጠቀሱ) ሁለት ግለሰቦች ሬሳ በደብዛዛው ያሳየ ሲሆን፤ የትግራይ ሕዝቦች
ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ትሕዴን) በበኩሉ ‹‹በአደረኩት ማጣራት በኢትዮጵያ በቴሌቪዥን ሟች ተብለው የታዩት ሁለት ግለሰቦች “ምክትል
ኢንስፔክተር ሞላ መላኩ የተባሉ የፖሊስ አባልና አቶ ሞገስ አስቻለው የተባሉ ሲቪል ናቸው” በማለት መንግስታዊ ሴራ እንደሆነ ገልጾ
ጉዳዩን አጣጥሎትም ነበር፡፡ በጉዳዩ ላይ ‹‹ተባብራችኋል›› በሚል ክስ ከቀረበባቸው አስር ግለሶች መካከል ቤት አከራይ በመሆን
የተጠቀሱት ሁለት ኢትዮጵያዊያን ተከሳሾች ቤታቸው ውስጥ የፈነዳው ጋዝ እንደሆነና ምንም አይነት የአጥፍቶ መጥፋት ሙከራ እንዳልነበር
ለፍርድ ቤት በተደጋጋሚ ማስረዳታቸውም ሌላው በጉዳዩ ላይ ጥርጣሬ የሚፈጥር ሁኔታ ነበር፡፡
ዶ/ር መረራ እንግዲህ በዚህ ሁሉ መሐል ነው በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ላቀረበላቸው ጥያቄ እንደ አንድ የፖለቲካ መሪ መልስ
የሰጠው፡፡ በዚህ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ንግግር መሰረት አድርጎ የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ (ቪኦኤ) የአማርኛው የስርጭት ክፍል ጥቅምት 21 እና
22፣ 2006 በሁለት ክፍል የቀረበ ቃለ-መጠይቅ አቅርቦለትም ነበር፡፡ ይህ የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ የአማርኛው የስርጭት ክፍል ቃለ-መጠይቅም
ነው ከሦስት ዓመታት በኋላ ዶ/ር መረራ ‹‹አሸባሪዎቹ አፈነዱ የተባለው የውሸትና የመንግስት ድራማ ነው›› በማለት የሃሰት ወሬን በማሰራጨት ክስ እንዲቀርብበት የሆነው፡፡ ፍንዳታው
ድራማ ነበር ወይስ አልነበረም? ለመሆኑ ዶ/ር መረራስ የተባለውን ነገር አሰራጭቷል ወይ? ቢናገር የግል አስተያየቱን መስጠቱ እንዴት
ወንጀል ይሆናል? የሚሉት ጥያቄዎች ተከትለው መቅረባቸው አይቀርም፡፡
በመጀመሪያ ዶ/ር መረራ ላይ በማስረጃነት ስለቀረበው የአሜሪካ ድምጽ የአማርኛ ስርጭትቃለ-መጠይቅን እንመልከት፡፡ ከቪኦኤ
የድምጽ ቋት ያገኘነው የዶ/ር መረራ በሁለት ክፍል የቀረበ (ጥቅምት 21 እና ጥቅምት 22፣ 2006) የ14 ደቂቃ ቃለ-መጠይቅ
ሙሉ ይዘቱ የሚከተለው ነው፡
የቃለ-መጠይቁ ርዕስ፣
‹‹የአዲስ አበባ ፖሊስ አንዳንድ ተቃዋሚዎች በቅርቡ
በአዲስ አበባ የደረሰውን ፍንዳታ አስመልክተው የጥርጣሬ አስተያየት ሰጥተዋል ሲል ተቃወመ››
የሚል ሲሆን፤ ቃለ-መጠይቁም፡
ቪኦኤ፡ እንደምን አመሹ ዶ/ር መረራ?
ዶ/ር መረራ፡ ደህና ነኝ፡፡
ቪኦኤ፡ እስኪ ለኢትዮጵያ መንግሰት የሰጡት ቃለመጠይቅ ምንድን ነው? በተለይ በፀጥታ ጉዳዮችና በሽብር ላይ አስመልክቶ፡፡
ዶ/ር መረራ፡ እኔ በዋናነት የኢትዮጵያ መንግስት ሽብርተኝነትንና የተቃዋሞ ፖለቲካን እያደባለቀ የሽብርተኝነት ሕጉን ተቃዋሚን ለማጥፋት ተቃውሞን ለማፈን የሚንቀሳቀስበት ሁኔታ እንጅ እውነተኛ ሽብርተኞችን መላጥቃት ለመከታተል እያደረገ አይመስልም፡፡ ብዙ ጊዜ ይደባለቅበታል፡፡ ተቃዋሚዎችን ሽብርተኞች ብሎ ብዙ ጊዜ ያስራል፡፡ ያምታታል፡፡ እንደዚህ ያለውን የተደባለቀ አድራጎቱን፡፡ ለምሳሌ አሁን የሙስሊም ማሕበረሰብ ተወካዮችን ሁለት ዓመትና ከዛ በላይ አንድ ሰው እንኳን ሳይገሉ፤ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የሚሳተፉበት እንቅስቃሴ ነው፡፡ ነገር ግን ‹‹እንዲህ አይነት ንብረት ጠፋ››፤ ‹‹አገሪቷ በሽብር ተናደች›› … የሚል ነገር አናይም፡፡ በሰላም ጥያቄዎቻቸውን ጠይቀው በሰላም አቤቱታቸውን አቅርበው መንግስት ጆሮ ባይኖረውም በሰላም መብታቸውን ጠይቀው የሚገቡበት ሁኔታ ነው፡፡ ሽብርተኛ ማለት ደግሞ ተደብቆ የሚያቃጥል የሚያሸብር እንጅ በሰላም መብቱን የሚጠይቅ፤ በሰላማዊ ሰልፍ መብቱ እንዲከበርለት የሚጠይቅ፤ በሰላም ‹‹መንግስት ችግሮቼን ይፍታልኝ›› ብሎ የሚጠይቅ አይደለም፡፡ እንዲያውም የኢትዮጵያ መንግስት ሽብርተኞች ናቸው ብሎ የሚመድባቸው፤ የሚፈርጃቸው በፓርላማ ሁሉ የሚወስንባቸው አንዳንዶቹ ሽብርተኝነትን በዋናነት እየተዋጋች ነው የምትባለው አሜሪካ ውስጥ በሰላም እየተንቀሳቀሱ ስብሰባዎችን እያደረጉ ፓርቲን እየሰበሰቡ የሚታገሉበት ሁኔታ ነው ያለውና አሜሪካኖቹ እንኳን (በዚህ በሽብር ዙሪያ የኢትዮጵያ መንግስት አጋር ናት የምትባለዋ) የኢትዮጵያ መንግስት ‹‹ሽብርተኞች ናቸው›. ብሎ የሚፈርጃቸውን ‹‹ሽብርተኞች ናቸው›› ብላ አልተቀበለችም፡፡
ቪኦኤ፡ እነዚህ በዝርዝር ኦነግ፣ ኦብነግና፣ ግንቦት ሰባት ናቸው አይደል?
ዶ/ር መረራ፡ አዎ! እና በተለይ ለተቀዋሚዎች ችግር የፈጠረው የኢትዮጵያ መንግስት ብዙ ነገሮችን ያደባልቃል፡፡ እያደባለቀ ተቃውሞን ለማፈን እየተንቀሳቀሰ በሰላም እንደሚታገሉ የምናቃቸው በቅርብ የምናቃቸውን ሰዎች መንግስትን በኃይል ለመገልበጥ ተንቀሳቅሰዋል፤ ሽብርተኝነት ውስጥ ተሳትፈዋል እየተባሉ ጋዜጠኞች ያለፕሬስ ምንም ነገር እንደሌላቸው የሚታወቁ ሰዎችን ያስራል፡፡ ዓመታትን ይፈጅባቸዋል፡፡ እና እነዚህ ደግሞ በአሜሪካ ተቋማት በነሲ.ኤን.ኤን (ሲ.ፒ.ጄ?) የሚሸለሙበት ሁኔታ ነው የሚያስራቸው፡፡ ሽብርተኞች ናቸው ወንጀለኞች ናቸው እያለ የሚያስራቸው፡፡ በዓለማቀፍ ደረጃ የሚታወቁ ተቋማት ሽልማት የሚሰጡበት ሁኔታ ነው ያለውና እኔ የኢትዮጵያ መንግስት እየገፋበት ያለው መንገድ የፀረ-ሽብር ትግሉን እንዳይጎዳ፤ ሽብርተኝነት ዙሮ ዙሮ ሁላችንም የሚጎዳ ነው እውነት ሆኖ ከመጣ፡፡ ስለዚህ ማደባለቁ ማንንም አይጠቅምም፡፡ አገሪቷን አይጠቅምም፤ መንግስትን አይጠቅምም፤ የኢትዮጵያ ሕዝቦችን አይጠቅምም፡፡ ተቃዋሚን ማሰር ከፈለገ መንግስት በሰራውና ተቃዋሚ በመሆኑ ማሰር ይሻላል፡፡ ከሽብርተኝነት ጋር እያደባለቀ የሐይማኖት መብታቸውን የጠየቁትን (እንደ እስላሞቹ አይነቱን) በሰላማዊ መንገድ እየጠየቁ እንዲያውም በርቱ ብሎ መሸለም እና ማመስገን ሲገባው፤ የኢትዮጵያ መንግስት ከሽብርተኝነት ጋር እያያያዘ የሚወስዳቸው እርምጃዎች እያስቸገሩ ነው ለወደፊቱም ትግሉን ይጎዱታል፡፡
በማለት የጥቅምት 21፣ 2006 ቃለ-መጠይቅ የተጠናቀቀ ሲሆን፤ በጥቅምት
22 የቀጠለው ቃለ-መጠይቅ ደግሞ እንደሚከተለው ነው፡
ቪኦኤ፡ ዶ/ር መረራ በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ተቃዋሚዎችን ማስጠንቀቂያ የሚመስል ንግግር ተናግረዋል፡፡ በእናንተ በኩል እነዚህ በመንግስት በኩል በተከታታይ የሚሰሙ በፖሊስም በሥራ አስፈፃሚውም በኩል የሚሰሙ በእናንተ ላይ ያነጣጠሩ ጥያቄዎች ላይ ምንድን ነው የእናንተ መልስ እንዴት ነው የምታዩአቸውስ፡፡
ዶ/ር መረራ፡ እኛ በግልፅ በአደባባይ ሰላማዊና ሕጋዊ ትግላችንን ከመቀጠላችን ውጭ ምርጫ የለንም፡፡ ‹‹ሠላማዊና ሕጋዊ ትግላችሁን ትታችሁ ቤት ተቀመጡ›› ከሆነ ከኢትዮጵያ መንግስትም ሆነ ከምርጫ ቦርድ ፈቃድ ወስደን ድርጅት ፈጥረን ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በኢትዮጵያ ውስጥ እንዲፈጠር የምንንቀሳቀሰው ለእዛ ነው፡፡ ሌላ ምክንያት የለንም፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ትልቁ ችግር ግን የሚናገረውና የሚሰራው እየተጋጨበት የተቃውሞ ፖለቲካንና ሽብርተኝነትን መለየት ያልቻለበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ በሰላማዊ ዜግነታቸው የሚታወቁ ከብዕር ውጭ ሌላ ነገር የሌላቸው ጋዜጠኞችን የፖለቲካ ድርጅት በተለይ ወጣት መሪዎችን የእኛንም አባላት ጭምር መንግስት ሲያስር ነበር፤ አሁንም እስር ቤት እየማቀቁ ነው፡፡ ለምሳሌ ከሁሉም በላይ የእስላሞችን ጉዳይ እንውሰድ፡፡ ከሁለት ዓመት በላይ በሽህዎች የሚቆጠሩ ብቻ ሳይሆን፤ በመቶ ሽህዎች የሚቆጠሩ ብቻ ሳይሆን፤ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የሙስሊም ማሕበረሰብ አባላት በአብዛኛው ኢትዮጵያ ሲንቀሳቀሱ፤ በሰላማዊ መንገድ በአዲስ አበባ ውስጥም ሆነ ውጭ (መብታቸውን) ሲጠይቁ፤ አቤት ሲሉ፤ ፍርድ ቤት ሔደው ሲጠይቁ፤ የሚመለከታቸውን የመንግስት አካላት ሲጠይቁ ሽብርተኝነትን ጎረቤታችን ኬኒያ እንደምናየው፤ ሶማሊያ እንደምናየው፤ በመካከለኛው ምስራቅ እየተደረገ ያለው ሽብርተኝነት በምናቅበት ደረጃ ሲንቀሳቀሱ አናይም፡፡ በሠላማዊ መንገድ መብታቸውን ከመጠየቅ ውጭ፡፡ የጠየቁት መብት ደግሞ በጣም ቀላል ነው፤ ‹‹መንግስት በኃይማኖታችን ውስጥ ጣልቃ አይግባ››፤ ‹‹መንግስት የፈለገውን የኃይማኖት አንዱን ክፍል ይዞ ሌላኛው በጉልበት እንዲንቀሳቀስ››፤ ‹‹መሪዎቻችን ቀበሌ ውሰጥ አንምረጥ፤ ቀበሌ ለምሳሌ የመንግስት ተቋም ነው›› … ስለዚህ የእስላም መሪዎች ቀበሌ ውስጥ የሚመረጡበት ምክንያት በሕጉም በምኑም መንገድ አላውቅም እኔ፡፡ ክርስቲያን ወንድሞቻችን መሪዎቻቸውን ቤተክርስቲያን እንደሚመርጡ እነዚህ ወንድሞቻችንም መስጊዶቻቸው ውስጥ መሪዎቻቸውን ከመረጡ ኃይማኖቱ የግላቸው ነው የራሳቸው ነው፡፡ መንግስት ግን እዛ ውስጥ ጣልቃ ገብቶ፤ ‹‹ቀበሌ ካልመረጣችሁ›› በማለት በቀጥታም ሆነ በእጅ አዙር ሲንቀሳቀስ እኮ እናውቃለን፡፡ በዚህ በኢትዮጵያ ሕዝብ ውስጥ እኮ ነው የምንኖረው፡፡ እናም ማን የት ጣልቃ እንደገባ ኃይማኖቶች መንግስትን ያስቸገሩበት ሁኔታ ሳይሆን፤ መንግስት እንዲያውም በራሱ ሔዶ … የእኔ ስጋትና በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የሰጠሁትም ምክር ሕዝብ ያላሰበውን እንዳያሳስብ ነው፡፡
ቪኦኤ፡ ዶ/ር መረራ በሰሞኑ ጉዳዮች ላይ እናተኩርና በተደጋጋሚም ከዚህ በፊትም እንደሚታወቀው፤ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በፓርላማ ቀርበው፤ እንዲሁም የፀጥታና የደህንነት ኃይሎችም በተለያዩ ቃለመጠይቆች የሽብር ስጋት እንዳለና ከተቃዋሚዎች ጋር እያያዙ በተናገሩ ጊዜ፤ እንደምናስታውሰው ከሁለት ዓመት በፊት ጋዜጠኞች እስክንድር ነጋ፤ ርዕዮት ዓለሙ፤ ውብሸት ታዬ ከተቃዋሚዎች ደግሞ እነ አንዷለም አራጌ ታስረዋል፡፡ እና አሁን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በፓርላማ እየቀረቡ እንዲሁም ደግሞ የፀጥታ ኃይሎች የሚሰጡአቸውን መግለጫዎች ስትመለከቱ፤ እንዲያው እርስዎ እንደመሪነቶ፤ እንዲሁም ደግሞ እርሶ በሚመሩት ፓርቲና በሚሰሩባቸው መድረኮች ሰሞኑን ስጋት የፈጠረበት ሁኔታ አለ?
ዶ/ር መረራ፡ በእኛ በኩል የኢትዮጵያ መንግስት ለአለፉት ዓመታት ይሄኑ ሲል ነበር አሁንም ያንኑ እያለ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ በሚያውቀው ደረጃ የዓለምአቀፍ ማሕበረሰብም በሚያውቀው ደረጃ አባሎቻችን ሰላማዊና ሕጋዊውን ትግል ከመግፋት ውጭ በሕገወጥ መንገድ በሴራ ውስጥ የተሳተፉበትና የሚሳተፉበት ምክንያት የለም፡፡ እኛ ሕጋዊና ሰላማዊ ትግላችንን እንቀጥላለን፡፡ የኢትዮጵያ መንግስትም እስከአሁንም እንደሚያደርገው አሁንም በብዛት አባሎቻችንን እንደ በቀለ ገርባ፣ ኦልባና ሌሊሳ፣ እነ አስፋው አንጋሱ፣ እነ ጉቱ ሙሊሳ የሚባሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ አባሎቻችን እኮ እስር ቤት አሉ፤ ‹‹ከሕግ ውጭ መንግስትን ለመገልበጥ አሲራችኋል›› ተብለው፡፡ እኛ ሕጋዊና ሰላማዊ ትግላችንን ከመግፋትና ከማካሄድ ውጭ ምርጫ የለንም፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ማድረግ የነበረበት ከኢትዮጵያ ሕጋዊ ተቃዋሚዎች ጋር የመደራደር ሁኔታ ብሔራዊ የመግባባት ሁኔታን የመፍጠር ሂደትን በሰላማዊ መንገድ ሁሉም የአገሪቱ የፖለቲካ ኃይሎች የሚንቀሳቀሱበት ሁኔታ የመፍጠሩ፤ የማመቻቸቱ፤ ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ ሊያካሂድ የሚችል ምርጫ ቦርድ የመፍጠሩ ነፃ ሚዲያ በአገሪቱ ውስጥ እንዲፈጠር የማድረጉ፤ የሕግ የበላይነት በዚህ አገር እንዲከበር፤ ሁሉም ዜጎች በዚህ ውስጥ እንዲሳተፉ የማድረግ ሁኔታ ይጠበቅበታል፡፡ ያንን ከማድረግ ይልቅ ‹‹በግድ መግዛት አለብኝ››፤ ‹‹ከህግ ውጭ መንቀሳቀስ አለብኝ››፤ ‹‹ሠላማዊ ትግል የሚያካሂዱትን ጉልበት ስላለኝ ለማፈን እንቀሳቀሳለሁ›› … ካለ እኛም ትግላችንን ከመቀጠል ውጭ ሌላ አማራጭ የለንም፤ የኢትዮጵያ መንግስት ግን ደጋግሞ ማሰብ ያለበት ደጋግሞ ይሄን በገፋበት መንገድ ዘላቂ ሰላም ሊያመጣ የሚችል አይመስለኝም፡፡ እንዲያውም ወጣቱን ወዳላሰበው አቅጣጫና መንገድ እንዳይገፋ እኔ ስጋት አለኝ፡፡ የኢትዮጵያ መንግስትን ደጋግሜ የምመክረው ሕጋዊና ሰላማዊ ትግሉን ከሽብርተኝነት ጋር አያይዞ፤ ዓለምም እያወቀ፤ የኢትዮጵያ ሕዝቦችም እያወቁ እያደባለቀ መጠቀም መሞከሩ ማንንም አይጠቅምም፡፡ ማስፈራራቱም ማንንም አይጠቅምም፡፡ አባሎቻችንን ከዚህ በፊትም ሲያድን ነበር ያንን መቀጠሉ፤ የፖለቲካ ምህዳሩን የበለጠ ለመዝጋት (አሁንም ተዘግቷል) እስከሄደ ድረስ እኛ ምርጫ የለንም ለማለት ነው፡፡ ሕጋዊና ሰላማዊ ትግልን እስከመጨረሻው ከመቀጠል ውጭ፡፡
ቪኦኤ፡ የኦሮሞ ፌደራሊስ ኮንግረስ ፓርቲ መሪ ዶ/ር መረራ ጉዲና ለሰጡኝ ማብራሪያ አመሰግናሁ፡፡
ዶ/ር መረራ፡ እኔም ለተሰጠኝ እድል አመሰግናለሁ፡፡
እንግዲህ ዶ/ር መረራ ተናገረ ተብሎ በተከሰሰበት ጥቅምት 21፣
2006ም ሆነ በጥቅምት 22 ቃለ-መጠይቅ ላይ ተናግሯል የተባለውን ‹‹አሸባሪዎቹ አፈነዱ የተባለው የውሸትና የመንግስት ድራማ ነው›› የተባለ ‹ሐሰተኛ› ወሬ አንድም ቦታ አናገኝውም፡፡ ነገር ግን የዚህ ክስ ይዘት ከሐሰተኛነቱ ይልቅ ሦስት ጉዳዮችን
መዝዞ ይነግረናል፡፡
የመጀመሪያው ዶ/ር መረራ ጥቅምት 15፣ 2006 የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ የአጥፍቶ መጥፋቱን ዜና አስመልክቶ ላቀረበለት
ጥያቄ “ሰው አንዳንድ ጊዜ የኢትዮጵያ መንግስት ለራሱ ፖለቲካ ብሎ የሚያደርገው ያው የለመደው ሥራ ነው ይላል›› በማለት የሰጠው
መልስ በክሱ ለማመልከት የተሞከረ ይመስላል፡፡ ነገር ግን የመረራ ከሳሽ በመንግስታዊው ቴሌቪዥን ‹‹የሐሰተኛ ወሬ›› ተሰራጨ ብሎ
መንግስትን ራሱን መክሰስ ሲያሳፍረው፤ ይቀራረባል በሚል ሐሳብ ከአሜሪካ ድምፅ ቃለ-መጠይቅ ላይ ወስዶ ክስ ለማቅረብ የሞከረበት
ርቀት አስገራሚ ነው፡፡
ሁለተኛው ምልከታ ደግሞ ወደ ክሱ ጥንስስ ይወስደናል፡፡ ዶ/ር መረራ ጉዲና
የተከሰሱበትን የአሜሪካ ድምፅ ቃለ-መጠይቅ ከሰጡ ከአስር ቀናት በኋላ መንግስታዊው አዲስ ዘመን ጋዜጣ በሕዳር 2006 ‹ኢብሳ ነመራ› በተባሉ ፀኃፊ አማካኝነት በአጀንዳ አምዱ
በተከታታይ “የአይነኬዎቹ ፍርሃት የጨመደደው ጋዜጠኛና ፖለቲከኛ” እና “መሠረት አልቦ አቋም” የሚሉ ሁለት ጽሑፎችን ያተመ ሲሆን፤
የጽሑፎቹ ዓላማም ዶ/ር መረራ የሰጡትን ቃለ-መጠይቅ ቃል በቃል እየነቀሰ መውቀስ፣ ማጣጣልና በመጨረሻ ‹ሕጋዊ ተጠያቂነት› እንዲኖር
ጥሪ ማቅረብ ነበር፡፡ እንግዲህ የመንግስታዊው ጋዜጣ የእስር ጥሪ ዘግይቶም ቢሆን ከሦስት ዓመታት በኋላ መረራን ለእስር አብቅቶታል፡፡
ሦስተኛውና ብዙ ሰዎች ለክሱ ምክንያት በሆነው ጉዳይ ላይ ተመሳሳይ አቋም ይዘው እያለ መረራ ላይ ብቻ ይህ ክስ እንዲቀርብ
የሆነበት ምክንያት አስገራሚነት ነው፡፡ ‹‹የኢትዮጵያ መንግስት የደኅንነት መስሪያ ቤት በዜጎቹ ላይ ጉዳት በማድረስ ተቃዋሚዎችን
የችግሩ አድራሽ አድርጎ እንዲወቀሱ ያደርጋል›› የሚለው ወቀሳ ለረጅም ጊዜያት የቆየ ቢሆንም ይህ ወቀሳ በጠነከረ መልኩ ከማስረጃ
ጋር መቅረብ የጀመረው የምስጢራዊ መረጃ አጋላጩ ዊኪሊክስ በጥቅምት 1999 በወቅቱ የአሜሪካ መንግስት ‘ሻርሼ ዴ ፌር (chargé
d'affaires) ቪኪ ሐድልስተን ለአሜሪካ መንግስት የሥለላ ማዕከል (ሲ.አይ.ኤ)ና ሌሎች የአሜሪካን የደኅንነትና የውጭ ጉዳይ
መስሪያ ቤቶች የላኩትን መልዕክት ይፋ ካደረገ
በኋላ ነው፡፡ ቪኪ በመልዕክታቸው መስከረም 06፣ 1999 በአዲስ አበባ ከተማ ካራ ቆሬ አካባቢ በሦስት የተለያዩ ቦታዎች የቦምብ
ፍንዳታዎች መከሰታቸውንና የኢትዮጵያ መንግስትም የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አባላት ቦንቦችን ለጥፋት ሲያዘጋጇቸው ራሳቸው
ላይ ፈንድተውባቸው ሁለት ግለሰቦች ወዲያውኑ ሲሞቱ ሦስተኛው ግለሰብ ደግሞ ወደሆስፒታል በመሄድ ላይ እንዳለ ሕይወቱ እንዳለፈ የመንግስትን
መረጃ ጠቅሰው ፤ የአሜሪካ መንግስት ባደረገው ማጣራትም ከፍንዳታዎቹ
ጀርባ የመንግስት እጅ እንዳለበት ገልፀዋል፡፡ አክለውም ሞቱ ተብለው በመንግስት የተጠቀሱት ግለሰቦች ከሳምንት በፊት በፖሊስ ተወስደው
በደረሰባቸው ድብደባ ምክንያት በመሞታቸው መንግሥት በራሳቸው ጥፋት እንደሞቱ ለማስመሰል ቦንቦቹን እንዳፈነዳቸው ዶ/ር መረራ ጉዲና
ያላቸውን መረጃ ለኤምባሲው እንዳካፈሉ አትተዋል፡፡ ኤምባሲው በራሱ ምርመራ አድርጎም ቦንቦቹ ከተጠቀሱት ቤቶች ውጭ በሦስተኛ አካል
ተዘጋጅተው እንደፈነዱ ለማረጋገጥ መቻሉን ጠቅሰው ቪኪ ሐተታቸውን ይጨርሳሉ፡፡
የሁለቱም የፍንዳታ ሁነቶች መመሳሰል አስገራሚ ሲሆን፤ የመረራ ከሣሽ ‹‹መረራ በጥቅምት 1999 የተደረገውን ሴራዬን
አጋለጡብኝ›› በሚል በቀል አዘል መንፈስ አስር ዓመታት ጠብቆ በሕዳር 2009 ከሦስት ዓመታት በፊት የሰጡትን አስተያየት እንደወንጀል
ቆጥሮ አስሯቸዋል፡፡ ይህ ድርጊትም የመረራ ከሣሽ እርሳቸውን ለመበቀል የሄደበት ርቀት አስገራሚነት ከመናገሩ ባለፈ ለመረራ ግን
የመንፈስ ‘ረፍት ነው፡፡ መረራን ለመበቀል አስር ዓመታትን ሲቆጥር የነበረ ሥርዓት የራሱን ሴራ ለመሸፈን ሲጥር የበለጠ ራሱን ማጋለጡ
ደግሞ ለታሳሪው መረራ ድል ነው፡፡ አሁን የመረራን ጉዳይ የያዘው ፍርድ ቤት ውሳኔ ለመስጠት ቀጠሮ ይዟል፡፡ ለዳኞቹ ንጹሁን መረራን
‹ነፃ› ከመልቀቅ የቀለለ ነገርስ ይኖር ይሆን?
Sweet blog! I found it while surfing around on Yahoo
ReplyDeleteNews. Do you have any suggestions on how to get listed in Yahoo News?
I've been trying for a while but I never seem to get there!
Appreciate it
Strong Women Quotes
ReplyDeletearticle submission free sites
ReplyDeletetop social bookmarking sites list
pdf submission site list 2019
free social bookmarking submission sites list in uk
free instant approval social bookmarking sites
high pr pdf submission sites
social bookmarking sites seo
quotes for 2019
instant approval social bookmarking sites list
motivational quotes for students
ReplyDeleteNice thanks for sharing…… love your blog.
ReplyDeleteVist your blog again and again.
akad attitude shayari
periyar quotes in tamil
karma quotes in tamil
Romantic sms in bangla
Love Failure quotes in tamil
Whatsapp status in tamil
birthday wishes in bengali
Family Quotes in hindi
Ms Dhoni Quotes in hindi
Liyana Anam This is nice
ReplyDeleteWebsite
Hello This is something, that's you can get here...
ReplyDeleteHeart Touching Sad whatsapp Status
I have been looking for this information for quite some times. Will look around your website.
ReplyDeletelucknow escorts service
Thanks for the post and effort! Please keep sharing more such blog.
ReplyDeleteShayari
Kaspersky free
Happy Republic Day Wishes in Gujarati
ReplyDeleteHappy Republic Day Messages in Gujarati
If you are one of those who don’t know how to update the Garmin map, below are some of the ways by which you can update it. You just need to use the Garmin Express application in the matter of getting the Garmin Map updates. With the help of Garmin Express, you will be able to update your Garmin Map by downloading it from the official website of Garmin.
ReplyDeletegarmin updates
garmin map updates
garmin gps updates
garmin nuvi updates
garmin express updates
When it comes to talking about its features, this Magellan device or Magellan GPS updates are loaded; with various sorts of exciting features. Once you start using this great device, you’ll learn about the traffic alerts, weather conditions, and a lot more. While using it, you’ll get to know which road route you should choose and which you should avoid. As many GPS devices are available in the market, one can opt for Magellan to make traveling easy and smooth. It will happen only just because of this advanced and modified device. But there is the thing about it that it needs updates from time to time. Simply put, you will need to update this device to have a comfortable experience of your journey.
ReplyDeletemagellan gps update
tomtom gps update
magellan gps updates
tomtom gps updates
https://bststatus.com/scam-1992-dialogues.html
ReplyDelete
ReplyDeletegarmin updates
garmin map update
garmin gps update
garmin nuvi update
garmin express update
Thanks For Sharing this information ! Keep Sharing
ReplyDeleteRomantic Song Lyrics in Hindi
Awesome Article ! This is really amazing and informative Blog. Thank you for sharing this wonderful information with us.
ReplyDeleteGet Fabulous Designer Sarees
ReplyDeleteIt really is a great article. Keep on going.
It's a wonderful post and very helpful, thanks for all this information.
ReplyDeleteYou made a blog with great information in an effective way. Thank you so much for sharing.
ReplyDelete
ReplyDeleteI have learn several good stuff here. Definitely worth bookmarking for revisiting.
this is very appealing, however , it is very important that will mouse click on the connection:
ReplyDelete
ReplyDeleteInteresting! I was thinking the same thing as you. Your article explains my vague thoughts very clearly
ReplyDeleteThank you. I have a lot of interesting ideas. I want you to look at the post I wrote
Such an amazing and helpful post. I really really love it
ReplyDeletesuch a great blog. Thanks for sharing.
ReplyDeleteI have learned lot of things from it concerning blogging.
ReplyDeleteYour way of telling the whole thing this post is
ReplyDeletein fact good
It is the best time to make some plans for the future and it is time to be happy.
ReplyDeleteI have read this post and if I could I desire to suggest you few interesting things or advice.
ReplyDeleteI wish for enjoyment, this web page contains truly nice funny data too.
ReplyDeleteThank you so much for your great information, It is too useful for me.
ReplyDeleteContinue sharing such an excellent post. Thankyou.
ReplyDeleteIt’s so good and so awesome. I am just amazed.
ReplyDeleteThis article is wonderful. I like it. Thanks for sharing.
ReplyDeletepossibility to read from this web site
ReplyDeleteI’ll come back often after bookmarking!
ReplyDeleteI am looking for some good blog sites for studying.
ReplyDeleteI love the efforts you have put in this, appreciate it for all the great content.
ReplyDeleteI gotta favorite this website it seems very beneficial extremely helpful
ReplyDeleteI could not refrain from commenting. Exceptionally well written!
ReplyDeleteJust what I was looking for, appreciate it for putting up.
ReplyDeleteI consider something genuinely special in this website.
ReplyDelete
ReplyDeleteThis is the perfect website for anyone who really wants to understand this topic.
ReplyDeleteIt's really pleasure to read your post. Thank you so much for writing such a nice post
I was seeking this particular info for a long time.
ReplyDeleteYou have a very good gloss. Thank you!
ReplyDeleteThanks for sharing this information.
ReplyDeleteThanks for the post and effort!
ReplyDeleteHi there, this is my first time commenting on the blog
ReplyDeleteso I think I have to tell you that keep doing it
ReplyDeleteNice article. I hope your blog guide would be helpful for me.
ReplyDelete
ReplyDeleteYou're so smart
ReplyDeleteyour views are in accordance with my own for the most part
ReplyDeletePretty good post
ReplyDeleteThis is the perfect website for anyone who really wants to understand this topic.
.
ReplyDeleteI want to read more things about here! thanks for the info.
ReplyDeleteIt's really pleasure to read your post. Thank you so much for writing such a nice post
ReplyDeleteReally appreciate you sharing this blog Much thanks again. Want more.
ReplyDeleteOh my goodness! Incredible article dude! I like the helpful info you supply to your articles
ReplyDeleteI like the valuable information you supply for your articles
ReplyDeleteFirst You got a great blog
ReplyDeleteI read your article very impressively I want to write something like this
ReplyDeletewow just what I was looking for
ReplyDeleteThank you , this is really useful information towards my assessment
Thank you for the good post.
ReplyDelete
ReplyDeleteKeep it on sharing
ReplyDeleteThank you for this excellent website.I am trying to read even more articles. Many thanks again!
ReplyDeleteThankyou for this wonderful article. I regularly read your article, all are very amazing
I appreciate you sharing such great information.
ReplyDeleteYour website is really awesome.
ReplyDeleteThe level of detail on your blog is impressive.
ReplyDelete