(ከሐምሌ 16 እስከ ሐምሌ 22፤
2004)
Capital ጋዜጣ ‹‹Counting 20›› በሚል ርዕስ ባስነበበው የሽፋን ገጽ ታሪክ
ላይ አቡነ ጳውሎስ የጵጵስና ‹‹ስልጣን›› የያዙበትን 20ኛ ዓመት አከባበር ይተርካል፡፡ በዓሉ በሸራተን አዲስ ሆቴል ሲከበር የተለያዩ
ሃይማኖት አባቶች፣ የቢዝነስ ሰዎች እና የፖለቲካ ሰዎች ተገኝተዋል - ከነርሱም ውስጥ ቴዎድሮስ አድሃኖም እና ኃ/ማርያም ደሳለኝ
ይገኙበታል፡፡
**
** **
Fortune ጋዜጣ “Fineline”
በተሰኘው የሚስጥር አምዱ ላይ ሰማሁ ብሎ ካንሾካሾካቸው ምስጢሮቹ ውስጥ መለስ ጁላይ 20 አዲስ አበባ ስለመግባታቸው፣ በርሳቸው
ስም ተፈርመው የወጡ ዶክመንቶች ስለመኖራቸው እና እረፍታቸው ለአንድ ሳምንት ያህል የሚቀጥል መሆኑን ተናግሯል፡፡
**
** **
አዲስጉዳይ
መጽሔት
ቴዎድሮስ ተክለአረጋይ ከፖለቲካ ሳይንስና የታሪክ ምሁሩ ፕሮፌሰር ገብሩ ታረቀ ጋር ያደረገውን ቃለ ምልልስ ይዞ ወጥቷል፡፡ ከቃለምልልሱ
ውስጥ የተቀነጨበውን እነሆ፡-
‹‹…በእኔ አስተያየት ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ተቃዋሚ ፓርቲዎች አሉ ብሎ
ለመናገር ያስቸግራል፡፡ ድምጻቸው ጠፍቷል፡፡ አይታዩም፡፡ ግን አለን ይላሉ፡፡››
‹‹…እኛን ከሶቪየት ህብረትና ከዩጎዝላቪያ ጋር ማወዳደር ግድ ይሆንብኛል፡፡
በሁለቱም አገሮች የፌዴራል ስርዓቱ የተሳሰረው ከአውራው ፓርቲና ከአንድ ግለሰብ መሪ አውራነት ጋር ነበር፡፡ ሁሉቱም (ፓርቲውም
አውራ መሪውም) ከስልጣን ሲወገዱ በሁለቱም አገሮች ፌዴሬሽኑ ፈራረሰ፡፡…››
‹‹…ሙስና ለእኔ ዋናው በሽታ ሳይሆን የበሽታው አንድ ምልክት ነው፡፡ ችግሩ
(በሽታው) የዲሞክራሲና መልካም አስተዳደር መምከን፣ ስልጣን በአንድ ፓርቲ መዳፍ ውስጥ መግባት ነው፡፡››
‹‹…ህዝቡ በፍርሃትና በተለያዩ ምክንያቶች ዝም ሲል እንደተስማማ አድርጎ
መቁጠር ስህተት ነው፡፡ ከሚጮህ ዝም ያለ ሕዝብ አደገኛ ነው፡፡…››
ሌላም ሌላም
- እኛ የምንታገለው ለሥርዓት ለውጥ እንጂ ለመንግስት ለውጥ አይደለም - አቶ ጥላሁን እንደሻው ለፍኖተ ነፃነት
- መድረክ ወደግንባር መሸጋገሩን አበሰረ፤ አዲስ የአመራር አባላት መርጧል (ከዚህ በኋላ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ግንባር (መድረክ) ይባላል፡፡) - ፍኖተ ነፃነት
- የሙስሊሙ ጉዳይ ኢሕአዴግን ከፋፈለ፤ ግንባሩ ለድክመቱ ራሱን ወቅሷል - ሰንደቅ
- የኮንዶሚኒየም ቁጥሮች፤ 207ሺኅ 069 ቤቶች (እስካሁን የተገነቡት)፣ 119ሺኅ 431 ቤቶች (ለተጠቃሚዎች የተላለፉ)፣ 87ሺኅ 638 (የት እንደገቡ ያልተገለፁ) - ሰንደቅ
- ጠቅላይ ሚኒስትሩ በውጭ አገር እረፍት ላይ ናቸው፣... Weekly Fetehe remains in limbo፣…. የካሉብ የነዳጅ ልማት ስምምነት ተሰረዘ፣.... የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንትና ምክትላቸው ከኃላፊነት ተነሱ፣… ሐበሻ ሲሚንቶና ሐበሻ ቢራ ከአክሲዮን ድርሻቸው ለአፍሪካና ለአውሮፓ ኩባንያዎች አካፈሉ፣… ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ፍትሕ ጋዜጣን አላትምም አለ - ሪፖርተር (ረቡዕ፣ ቅዳሜ እና እሁድ)
- ፍትህ ጋዜጣ እንደታገደ ነው፤ አዘጋጆቹ ከማተሚያ ቤት ፍትሕ ሚኒስቴር ሲመላለሱ ዋሉ - አዲስ አድማስ
- የላሊበላ
ነዋሪዎች ሊነሱ ነው - አዲስ አድማስ
‹‹በአሥራ አንዱ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስትያናት ዙሪያ ለበርካታ ዓመታት ሲኖሩ የቆዩ ነዋሪዎች፤ ለቅርሱ ደህንነትና ለገፅታው ማማር ሲባል ሊነሱ እንደሆነ የጠቆሙት ምንጮች፣ ነዋሪዎቹን በተመረጡ ሦስት ቦታዎች ለማስፈር የ፹፼ ሚሊዮን ብር በጀት እንደተያዘ ታወቋል…›› - WHO TO WATCH? Ethiopia’s olymic medals bid – Fortune
ኢትዮጵያውያን በለንደን ኦሎምፒክ ለሜዳልያ የሚሻሙባቸው ውድድሮች ከመጪው አርብ ጀምሮ ቅዳሜ፣ እሁድ፣ ሰኞ፣ ማክሰኞ፣ ረቡዕ እና እሁድ ዕለት እንደሚካሄዱ ጋዜጣው አትቷል፡፡
ርዕሰ አንቀጾች
- ከመንግስት መረጃ የማግኘት መብት አለን - ፍኖተ ነፃነት
- የኮንዶሚኒየም አፈፃፀም ሳንካዎች በ40/60 የቤት ልማት ዕቅድ አንዳይደገም ጥንቃቄ ቢደረግ - ሰንደቅ
- ሳሩን አየህና ገደሉን ሳታይ - ሪፖርተር (ረቡዕ)
- ‹‹የመጣነው መንገድ›› ብቻ ሳይሆን ‹‹የምንሄደው መንገድም›› ያሳዝናል እንዳንል - አዲስ አድማስ
- አንድ ሰው ስንት ነው? - አዲስ ጉዳይ
- ያበረ
ድር ሁሉ አንበሳን ያስራል ማለት አይደለም - ሪፖርተር
(እሁድ)
‹‹…ነገር ግን ድር ካበረ ሲባል ባዶ መግለጫና የፌስቡክ ጨዋታ አይደለም፡፡ አስመራ ውስጥ ያበረ ድር ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን አንበሳ ያስራል ማለት አይደለም፡፡ የውስጥ ጥንካሬና አንድነት የሌለው ድር እንኳን አንበሳን ሊያስር ሲወጥሩትና ሲጠመዝዙት የሚቆራረጥና የሚበጣጠስ ይሆናል፡፡ ድሩ ጠንካራ ካልሆነ፣ የድሩ ጥንካሬ በሚገባ ካልተፈተሸና ካልተረጋገጠ ድር ስለተባለ ብቻ ያስራል ማለት አይደለም፡፡ በቀላሉ ይበጣጠሳል ማለት ነው፡፡…››
የሳምንቱ ጥቅስ
‹‹አጠገቡ
ካሉ ሰዎች እንደምሰማው ጤንነቱ በፍጥነት እየተሻሻለ ነው፡፡››
No comments:
Post a Comment