(ከሐምሌ
23 እስከ 29፣ 2004)
አቶ ጁነዲን
ሳዶ ኢትዮ-ቻናል እና ለሰንደቅ ጋዜጣ ያወሩብኝ ‹‹ከሰሞ የሐይማኖት
ችግሮ ጋር በፍፁም የማይያያዝና ተጣሞ የቀረበ ነው›› የሚል ደብዳቤ ለጋዜጦቹ ልከዋል፡፡ በደብዳቤያቸው ባለቤታቸው ይዘውት
ተገኙ የተባለው ገንዘብ የሚኒስትሩ እናት ሲሞቱ በተናዘዙት መሰረት እንደግለሰብ ከሳዑዲ መንግስት ለማሰሪያ ድጋፍ ጠይቀው ላስጨረሱት
መስጊድ የሰደቃ ፕሮግራም የታሰበ ነበር፡፡
** ** **
Capital ጋዜጣ “Hard currency shortage” በሚል ርዕስ ምንጮቹን ጠቅሶ
ባስነበበው ዜና በተለይም የንግድ ሰዎች የውጭ ንግዳቸውን የሚያካሂዱበት የውጭ ምንዛሬ እጥረት እንደገጠማቸው አትቷል፡፡
** ** **
Fortune ጋዜጣም “Saudi
Star begins to spit the advance for Abebo” የሚል ዜና በፊት ገጹ ይዞ ወጥቷል፡፡ በዝርዝሩም ሳውዲ
ስታር Abeboን ለመግዛት ለፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ መክፈል ከሚጠበቅበት 40.5 ሚሊዮን ብር የቅድሚያ ክፍያ ውስጥ 32 ሚሊዮን
ብሩን ጁላይ 18 ከፍሏል፡፡ Abebo በጋምቤላ 3000 ሄክታር መሬት ያለው ሲሆን 65000 ሜትር ስኩዌሩ የጥጥ ተክል ልማት ጀምሯል፡፡
** ** **
ሪፖርተር ጋዜጣ በእሁድ እትሙ ‹‹ጋምቤላ
የመሸገውን የደቡብ ሱዳን አማፂ ኃይል ለመቆጣጠር ኢትዮጵያ ጦ አሰማራች›› ይላል፡፡ በዝርዝሩም ‹‹… አማፂ ቡድኑ ሰርጎ ገብቷል የተባለው በጋምቤላ ክልል ኑዌር ዞን ሲሆን፣ ቡድኑ የደቡብ ሱዳንን መንግሥት ለመውጋት የጋምቤላን ወጣቶች እየመለመለ እንደሚገኝ ተጠቁሟል፡፡
ይህንን አማፂ ቡድን በቁጥጥር ሥር አውሎ ለደቡብ ሱዳን መንግሥት ለማስረከብ የጋምቤላ ክልል ከፌደራል መንግሥት ጋር በጋራ እየሠራ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል፡፡ …››
በተጨማሪም
ሪፖርተር ‹‹የኢትዮጵያ
ድል በንግሥቷ ወርቅ ተጀመረ›› ይለናል፡፡
ተመስገን ደሳለኝ ስለ ፍትሕ ጋዜጣ መታገድ
የፍትሕ ጋዜጣ
መታገድን አስመልክቶ፣ የጋዜጣው ዋና አዘጋጅ አቶ ተመስገን ደሳለኝ ከተለያዩ የሚዲያ አካላት ጋር ቃለምልልሶችን አድርጓል፣
- እኛ ሥራችንን ጨርሰናል፤ ከዚህ በኋላ ኃላፊነቱን መወጣት ያለበት ሕዝቡ ነው! - ፍኖተ
ነፃነት
‹‹... እስከዛሬ 140 ክሶ በላይ ተከስሻለሁ፣ ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ ፀረ ሽብር ግብረኃይል ጠርተው ደብድበውኛል፣ በቪዲዮ ቀርፀውኛል፣ ከዚህ በኋላ በሚል ከፍተኛ ማስጠንቀቂያ ሰጥተውኛል፣ ይህን እስከዛሬ አልተናገርኩም፣….›› - ጥያቄያችን መልስ እስኪያገኝ ድረስ ማንኛውንም ሕጋዊና ሰላማዊ መስመሮችን በመጠቀም እንታገላለን - ዕንቁ መጽሔት
- ፍትህ ጋዜጣ በመጪው አርብ ገበያ ላይ ትውላለች - አዲስጉዳይ መጽሔት
- ጋዜጣ ላይ ብንጽፍም ባንጽፍም ስጋቱ አለ - አዲስ አድማስ
- ፍትህ ጋዜጣ ወደህትመት እንዲመለስ መድረክ ጠየቀ - ሪፖርተር
ሌላም፣ ሌላም
- በሞያሌ ከተማ ውስጥ ከፍተኛ ውጊያ ተካሄደ (ፍኖተ ነፃነት)፣ በቦረናና በገሪ የጎሳ ግጭት 18 ሰዎች ሞቱ (ሪፖርተር)
- ‹‹አቶ መለስ አንድ ነገር ቢሆን ኢሕአዴግ ችግር ይገጥመዋል›› - ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ (ሰንደቅ)፣ ጠ/ሚ መለስ በቤተ መንግስት እያገገሙ ነው ተባለ፤ ከመኖሪያ ቤታቸው ሥራ ጀምረዋል ተብሏል፣ ሊሰጡት ታቅዶ የነበረው መግለጫ ተሰርዟል (አዲስ አድማስ)፣ ኢሳት መለስ አርፈዋል ማለቱን መንግስት ውድቅ አደረገ (ሰንደቅ)፣ ‹‹በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጤንነት ላይ ለያንዳንዱ አሉባልታ መልስ አንሰጥም›› - አቶ በረከት ስምዖን (ሪፖርተር/ረቡዕ)፣
- አምነስቲ ኢንተርናሽናል የኢትዮጵያ መንግስት የሙስሊሙን መብት ጥሷል አለ (ሰንደቅ)፣
- የጋዜጠኛና መምህርት ርዕዮት አለሙ መጽሐፍ ተመረቀ (ዕንቁ)፣ ርዕዮት አለሙ የ5 ዓመት እስር ተፈረደባት (አዲስ አድማስ)፣ Court reduces Reeyot’s 14 years to 5 (THE Reporter)፣ የጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ እስር ወደአምስት ዓመት ዝቅ አለ (ሪፖርተር)
- ቴዎድሮስ ካሣሁን 100ሺህ ብር ለአካል ጉዳተኞች ሰጠ (አዲስ አድማስ)
- የኢትዮ-ቻናል ጋዜጣ አሳታሚና ማኔጂንግ ዳይሬክተር ታሰሩ (ኢትዮ ቻናል)
- ኢትዮጵያዊቷ ዲፕሎማት በአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር ዘብጥያ ወረዱ (ኢትዮ ቻናል)፣ ኢትዮጵያዊቷ በሐሺሽ ዝውውር ተቀጣች (አዲስ አድማስ)
ርዕሰ አንቀጾች
- የተቋማት ውድቀት፤ የኢሕአዴግን ውድቀት አይቀሬነት አመላካች ነው! - ፍኖተ ነፃነት
- ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር አሁንም ይበልጥ የመንግስት ትኩረትን ይሻል - ሰንደቅ
- የኢንቨስተሮች አያያዝና መስተንግዶ ብልህነት፣ ሕጋዊነትና አበረታችነት ይጠይቃል - ሪፖርተር (ረቡዕ)
- የሕገመንግስቱ ክፍተቶች በማሻሻያ (amendment) ሊደፈኑ ይገባል - ዕንቁ
- የጨው ክምር ሲፈርስ ሞኝ ያለቅስ፣ ብልህ ይልስ - አዲስ አድማስ
- መንግስት ግጭቶችንና አለመግባባቶችን ለመፍታት ባሕላዊ የሽምግልና ዘዴዎችን ይጠቀም - ሪፖርተር (እሁድ)
No comments:
Post a Comment