አጥናፉ ብ
ሰሞኑን በኢንተርኔት ተጠቃሚ ዘንድ እያወዛገበ ያለው የቴሌኮም አዋጅ አቶ ሽመልስ ከማል በቴሌቭዥን መስኮት ብቅ ብለው ስካይፒን መጠቀም ይቻላል ካሉ በሗላ ጋብ ብሎ ቢቆይም አቶ በረከት ሰጡት በተባለው መግለጫ ደግሞ ስካይፒን እንዘጋለን ወይም “ስካይፕም ሆነ ሌሎች የቴሌን ገቢ የሚቀንሱ እና ለደህንነት ስጋት የሚሆኑ የኢንተርኔት አገልግሎቶችን እንዘጋለን” የሚል ግራ የሚያጋባ ንግግር በትነዋል፡፡
ለዚህም ይመስላል አቤ ቶክቻው ‹‹ሰዎቻችን ቋንቋቸው የተደበላለቀው ምን ተንኮል ቢያሴሩነው›› የሚል ሽሙጥ ከጦማሩ ያኖረልን፡፡
የሁለቱን ባለስልጣናት ግራ የሚያጋባ መግለጫ ግራ ያጋባው አቤ ቶክቻው ህጻን እያለን የተነገረንን አፈታሪክ ገላጭ ሆኖ አግኝቶታል ‹‹…ድሮ ድሮ አሉ የሰው ልጆች ቋንቋ ሁሉ አንድ ነበር። ታድያ ከእለታት በአንዱ ቀን ትልቅ ግንብ ገንብተው ፈጣሪያቸው ያለበት ሰባተኛው ሰማይ ላይ ደርሰው ምን እያደረገ እንደሆን ሊሰልሉት አሴሩ።
የሀሳባቸውን ለመሙላትም፤ አንድም የሰው ልጅ ሳይቀር ተሰባስበው በዚህ እኩይ ስራ ላይ ተጠመዱ። እግዜርም ይህ የማይሆን የቂል ሀሳባቸው እንደማይሳካ ያውቃልና፤ በሌሎች መልካም ስራዎች ላይጊዜያቸውን እንዲያሳልፉ፣ እንዲሁም በዚህ የተነሳ የሚደርስባቸውን አደጋ ለመታደግ ብሎ ይህንን ስራ ሊያቋርጥባቸው ፈለገ። ከዛም ቋንቋቸውን ደበላለቀው። ከዛስ…?
ከዛማ አንዱ ብሎኬት አምጣ ሲል ውሃ ሲያቀብለው፣ ሙገር ሲሚንቶን አቀብለኝ ሲል የቀበና አሸዋ ሲያመጣ ግንቡ በየት በኩል ይግባቡ በየት በኩልስ ይገንቡ!? ሀሳባቸው ከንቱ ሆኖ ቀረ።…››
ከዚህ ቀደም ‹‹ቪኦኤን ጃም ታደርጋላችሁ?›› ተብለው የተጠየቁት አቶ ሽመልስ ከማል ‹‹የለም የኢትዮጵያ መንግስት ቪኦኤን ጃም አያደርግም›› ብለው ነበር፡፡ ብዙም ሳይቆይ ጠቅላይ ሚንስትሩ ምን ታመጣላችሁ በሚል ድምጽ ‹‹አዎ! ጃም እናደርጋለን፡፡›› ብለው አምነዋል፡፡
ይህ የአቶ ሸመልስ ክህደትና የልሎቹ ባለስልጣናት እምነት ያናደደው አቤ ‹‹..እኔ የምለው አቶ ሽመልስ፤ የመንግስት ቃል አቃባይ ሆነው ሳለ ለምን ቃላባይ ሲያደርጉዎት ዝም ይላሉ!?...›› ብሎ ለሌላኛው አዛዥ አቤቱታ አቅርቧል፡፡ ሙሉ ሽሙጡን ለማንበብ እዚህይጫኑ፡፡
በሌላ ጦማር አቤ ‹‹ኢጃበና ወሬ ኢጃበና ወሬ፤ በእውቀቱ ስዩም ወደእንግሊዝ ተሸኘ!›› ይለናል፡፡ ሲቀጥል ‹‹ኢጃበና›› ማለት ኢንዲህ ሲል ምን ማለት እንደሆነ ይነግረናል፡፡ ‹‹ቃሉ ኦሮሚፋ ሲሆን የዓይን መክፈቻ! ማለት ነው። ብዙ ጊዜ ቃሚዎች ዋናውን ጫት “ቂማህ” ከመጀመራቸው በፊት ትንሽ ነከስ ነከስ የሚያደርጓትን ዓይን መክፈቻ ወይም ኢጃበና! ይሏታል።›› ይህ ርእስ አቤ በውቀቱ ስዩምን ወደ ሎንዶን ኦሎምፒክ ለሚያደርገው ጉዞ የተደረገለትን ሽኝት ቃኝቶበታል፡፡
በዚህ ዝግችት ላይ ንግግር ያደረጉት የደራሲያን ማህበሩ ሊቀመንበር አቶጌታቸው እንዲህ ብለዋል “ለበእውቀቱ የለንደን ጉዞ መሳካት የተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶችን እና መንግስትን ማመስገን እወዳለሁ…! በእውቀቱ በጉዞህ የሀገሪቱን መልካም ገፅታ እንድታስተዋውቅም አደራ እልሃለሁ!” ብለዋል፡፡ ይህ ንግግራቸው ነው አቤ ሰውዬውን ‹‹ካድሬ መሳይ›› ያላቸው፡፡
ለአቶ ጌታቸው መልስም በእውቀቱ ሰጥቷል “በመጀመሪያ አቶ ጌታቸው ባሉት አልስማማም። መንግስትም ሆነ የመንግስት መስሪያቤቶችን ምንም አላደረጉልኝምና አላመሰግናቸውም። ትብብር ያደረገለኝ የደራሲያን ማህበር መመስገን ካለበት እርሱን አመሰግናለሁ።›› አቤ ለበእውቀቱ መልካም ጉዞም ተመኝቶለታል፡፡ ሙሉ ሽሙጡን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ፡፡
‹‹ግርምት፣ትዝብት፣ፍርሃትእና ፀሎት!››
*ሽሙጥም መሰረት መብራቴ በተባበሩት አሜሪካ ጥገኝነት መጠየቋ
*ለጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ካልሻባብ ደብዳቤ እንደደረሰው ….እና ሌሎችም ቀሪውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ፡፡
ኢትዮ ቼንጅ የተባለው ብሎግ ደግሞ አቶ በረከት ስካይፒን መከልከላቸውን ኢሳትን ጠቅሶ ይህን ጽሁፍ አስነብቧል፡፡ እዚህ ይጫኑ፡፡
ዳንኤል ክብረት በጦማሩ ‹‹የመጀመርያዋን ኢትዮጵያዊት ሴት ደራሲ›› ተዋወቋት ይለናል፡፡ በዚህ ጽሁፉ እሌኒ መሃመድ ስለምትባል ሴትና በአስተዳደር፣ በእምነትና በፖለቲካ ያደረገችውን አስተዋጽኦ የተለያዩ መፅሀፍቶችን ጠቅሶ እንዲህ ያትታል፡፡
‹‹…..እሌኒ በኢትዮጵያ ታሪክ በአስተዳደር፣ በእምነትና በፖለቲካ ኃያላን ከሆኑ ጥቂት መሪዎች የምትመደብ ናት፡፡ ምናልባትም ከንግሥተ ሳባና ከሕንደኬ ቀጥላ ልትጠቀስ የምትችል ኃያል ሴት ትመስለኛለች፡፡ ማዕከላዊው መንግሥት እንዲጠናከር፣ በሙስሊሙና ክርስቲያኑ መካከል የነበረው ግንኙነትም የተሻለ እንዲሆን ጥረት አድረጋለች፡፡ ምንም እንኳን የአብራኳ ክፋይ ልጅ ባይኖራት በነገሥታቱና በሕዝቡ ዘንድ እንደእናት ትታይ ነበር፡፡ …..››
‹‹…..ንግሥት እሌኒ ከፖለቲካውና አስተዳደሩ በተጨማሪ በሃይማኖት በኩል ብርቱ ምእመን ነበረች፡፡ አልቫሬዝ እንደሚለው እሌኒ ዓመቱን ሙሉ የምትጾም ሰው ነበረች፡፡ ምግብ የምትመገበውም በሳምንት ሦስት ቀን ማክሰኞ፣ ሐሙስና ቅዳሜ ብቻ ነበር፡፡…..››
ሙሉ ፅሁፉን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ፡፡ መልካም ንባብ፡፡

***

No comments:
Post a Comment