Tuesday, December 16, 2014

የዞን9 ጦማርያን እና የጋዜጠኞች የ10 ደቂቃ ችሎት

በነሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ ዛሬ ጠዋት የተሰየመው 19ኛ ወንጀል ችሎት ጦማርያኑ እና ጋዜጠኞቹ ቀድመው ቢገኙም ለሰአታት ያህል ችሎቱ ሳይጀመር ቆይቷል፡፡ የተወሰኑ ወዳጆች እና የቤተሰብ አባላት ችሎቱን ለመታደም እድል ያገኙ ሲሆን የተለመደው የቦታ ጥበትን ተከትሎ ብዙዎች ውጪ ቆመው ሲጠብቁ አንደነበርም ተስተውሏል፡፡ 

ባልተለመደ ሁኔታ ዘግይተው የተሰየሙት ዳኞች የጠበቆች የተሻሻለው ክስ ላይ ያላቸውን አስተያት ማቅረባቸውን ሰምተዋል፡፡ የተከሳሽ ጠበቆች ክሱ ላይ የጽሁፍ አስተያየታቸውን ማቅረባቸውን ነገር ግን አቃቤ ህግ ክሱን አለማሻሻሉን በቃል ክርክር ለማቅረብ ቢሞክሩም ፍርድ ቤቱ የቃል ክርክር አስፈላጊ አንዳልሆነ እና መሻሻል አለመሻሻሉን አይቶ አንደሚወስን በማሳወቅ የጠበቆችን የቃል ክርክር ጥያቄ ውድቅ አድርጎታል፡፡ ከፍርድ ሂደቱ በኋላ አስተያየታቸውን የሰጡት ጠበቃ አምሃ የጽሁፍ ምልልሱ የፍርድ ሂደቱን እያጓተተው በመሆኑ በቃል ማስረዳትን አንደአማራጭ ለመጠቀም ፈልገው አንዳልተሳካ ገልጸዋል፡፡ 

ከሰአታት ጥበቃ በኋላ የተሰየመው የልደታው ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት የፍርድ ሂደቱን ለታህሳስ 27 በመቅጠር ተጠናቋል፡። በእለቱ የጦማሪ ዘላለም ክብረት የልደት ቀን መሆኑን አስመልክቶ ብዙዎች ወዳጆቹ የመልካም ልደት ምኞታቸውን ገልጸውለታል፡። ጦማርያኑ ሲገቡ በጀርባ በር በኩል አንዲገቡ በመደረጋቸው ከሚጠብቃቸው ቤተሰብ እና ወዳጅ ጋር በደምብ ሰላምታ ለመለዋወጥ ባይችሉም በጠንካራ መንፈስ ጥንካሬ እና ፈገግታ ታይተዋል፡፡ 

የጠበቆቹ የተሻሻለው ክስ ፡፡
#Ethiopia #FreeZonebloggers #FreeEdom #FreeTesfalem #FreeAsemamaw 


The bloggers and journalists outside at lideta court 
Edom Kassaye (journalist) and Mahilet Fantahun (bloggers) today outside court  
Birthday man, Zelalem Kibret with Zone9bloggers and Journalists
 

No comments:

Post a Comment