Sunday, May 18, 2014

የዛሬው የጦማርያኑ የፍርድ ቤት ውሎ



ዛሬ በዋለው ችሎት ከተለመደው ሰአት ቀደም ብለው ከከባድ ጥበቃ ጋር ፍርድ ቤት የደረሱት የዞን 9 ጦማርያን በፍቃዱ ሃይሉ ማህሌት ፋንታሁን እና አቤል ዋበላ ላይ ፓሊስ ከትላንትናው ጋር ተመሳሳይ የሆነ 28 ቀን ጊዜ ቀጠሮ የጠየቀ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ 14 ቀን ፈቅዶለታል፡፡
ፓሊስ የጸረ ሽብር አዋጁን በመጥቀስ በሽብር ክስ ለማቅረብ ስላሰበ 28 ቀን እንዲሰጠው የጠየቀ ቢሆንም ዳኛዋ ያለምንም የተለየ ተጨማሪ ነገር ከመነሻ ጥርጣሬ ለመቀየር ፓሊስ አሳማኝ ምክንያት ባለማቅረቡ 14 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ብቻ ፈቅደዋል።
ጦማርያኖቹ ጓደኖቻችን ምንም አይነት የወንጀል ተግባር ላይ ተሰማርተው የማያውቁ መሆኑን እያስታወስን መንግስት እንዲፈታቸው አሁንም በድጋሚ ጥሪ እናቀርባለን

#‎FreeZone9bloggers #‎FreeTesfalem #‎FreeEdom #‎FreeAsemamaw #‎Ethiopia

3 comments: