አጭር የፍርድ ቤት ውሎ
የሁለቱ ሴት ታሳሪያንን አያያዝ እስመልክቶ ዛሬ ለ22ተኛ ግዜ የተሰየመው ችሎት ለመጋቢት 10 ሌላ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቶ ተጠናቋል ፡፡
የመጀመሪያው ጉዳይ የሆነውና የማህሌት ፋንታሁን እና የኤዶም ካሳዬን አያያዝ አስመልክቶ የተነሳው አቤቴታ ላይ መልስ የሰጡት የማረሚያ ቤቱ ተወካይ ዋና ሱፕር ኢንቴንዳንት ለተእግዜር ገ/ እግዜያብሔር ምንም አይነት የመብት ጥሰትና የጎብኚ ክልከላ እየተደረገባቸው አይደለም አንደማንኛውም ታራሚ በማንኛውም ሰው ይጠየቃሉ ሲሉ ሽምጥጠው ክደዋል፡፡
ሁለተኛው የሆነው አቃቤ ህግ በእጁ ያሉትን 12 የኦዲዬ ቪዲዬ ሲዲዎች ለጠበቆች አንዲሰጥ የጠየቁበት ቢሆንም አቃቤ ህግ መመልሱ በችሉት ወቅት ያዩታል እንጂ ፓሊስ ኤግዚቢት ለጠበቆች የመስጠት የሚያስገድደን ህግ የለም ብሏል፡፡ ( የአቃቤ ህግ ምላሽ ከስር ተያይዞ ይገኛል)
ሁለቱም ጉዳዬች ላይ ብይን እሰጣለሁ ያለው ፍርድ ቤቱ በሚቀጥለው ቀጠሮ ወንዶች ተከሳሾችም ተገኝነተው ብይኑን እንዲሰሙ አዟል፡፡
የዞን9 ማስታወሻ
የቀረበብንን ማስረጃ አይተን የመከላከል ህገ መንግሰታዊ መብታችን መጣሱን አጥብቀን እየተቃወምን መሰረታዊ ከፓለቲካ ነጻ ውሳኔ መስጠት መቻሉ የሚያጠራጥረው ፍርድ ቤት ቢያንስ በስነስርአት ጉዳዩች ላይ አንኳን ስልጣኑን እንዲጠቀምበት እናሳስባለን ፡፡
ስለሚያገባን እንጦምራለን!
በነገው እለት የ 26 ተኛ አመት የልደት በአልህን ለምታከብረው ጦማሪ አጥናፍ ብርሃኔ አንወድሃልን፡፡ አንኮራብሃለን
ዞን9
No comments:
Post a Comment