Sunday, July 8, 2012

ጋዜጣና መጽሔቶቻችን ከሰኞ እስከ ሰኞ - አምስት

(ከሰኔ 25፣ 2004 እስከ ሐምሌ 1፣ 2004)

‹‹በኢትዮጵያ ሊትሩ 135ሺህ ብር የሚሸጥ ዘይት ሊመረት ነው›› የሚል ዜና ይዞ የወጣው መሰናዘሪያ ጋዜጣ ነው፡፡ ‹‹…ቴራ የተባለ የጀርመን ካምፓኒ [ባሕርዳር] ከነሐሴ ወር ጀምሮ ሊትሩ 7,500 ዶላር የሚሸጥ ዘይት እያመረተ ለውጭ ገበያ እንደሚያቀርብ አስታወቀ፡፡….››

** ** **
‹‹ዲግሪ ያላቸው ዜጎች የጎዳና ተዳዳሪዎች ሆነዋል››  የሚል አስደንጋጭ መርዶ ያስነበበው ሪፖርተር ጋዜጣ በረቡዕ እትሙ ነው፡፡ ‹‹ቁጥራቸው በውል የማይታወቁ የማስተርስና የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው ዜጎች አዲስ አበባ ውስጥ የጎዳና ላይ ተዳዳሪዎች ሆነው መገኘታቸው ተጠቆመ፡፡

‹‹የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ… የጎዳና ላይ ተዳዳሪዎች ወደ መልካም ሕይወት ለመመለስ፣ … በማድረግ ላይ ባለው እንቅስቃሴ መምህር፣ ነርሶችና በተለያዩ ሙያዎች የተመረቁ ዜጎች የጎዳና ላይ ተዳዳሪ ሆው መገኘታቸውን አረጋግጧል….››

** ** **

‹‹ይቅርታ›› የኢሕአዴግ ቃጭል? ወይስ… ያለው ተመስገን ደሳለኝ ፍትህ ጋዜጣ ላይ ነው፡፡ ‹‹…እነሆም ማሰር፣ ከአሰሩ በኋላ በይቅርታ መልቀቅ፣ ከለቀቁ በኋላ ደግሞ ይቅርታን አንስቶ መልሶ ማሰር…‹በይቅርታ ተቀባዩ አንገት ላይ ተንጠልጥሎ ቀሪ ዘመንን በሞላ ‹ኪሊ፣ ኪል…› የሚል ‹ቃጭል› ነው›…››

Saturday, July 7, 2012

የኪራይ ሰብሳቢ ማዕበል

በዘላለም ክብረት
“Rent-seeking may, indeed, impose costs to the economy as high, if not higher, than those arising from corruption.”
  Anthony Ogus , Corruption and Regulatory Structures.

ገንዘብን መግዛት (Rent seeking)

በስነ ምጣኔ ሳይንስ ከእያንዳንዱ ኢኮኖሚ ጀርባ ብዙ ጋሬጣዎች(Economic Inefficiencies) ሊኖሩ ይችላሉ ለምሳሌ እንደ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት፣ የገንዘብ እና የፊስካል ፖሊሲ ክፍተት፣ ሙስና ፣ ገንዘብን መግዛት (Rent seeking) ወ.ዘ.ተ ናቸው፡ ከነዚህ የኢኮኖሚ ማነቆዎች ውስጥ ገንዘብን መግዛት (Rent seeking) የተባለውን ስንመለከት፡፡በአጠቃለይ ኢኮኖሚስቶች ‹‹እሴት አልባ ትርፍ ወይም አሁን ያለው ገንዘብ በራሱ ያለምንም ዕሴት ማጎልበት ተጨማሪ ገንዘብ እንዲገዛ ለዛ መበርታት›› ብለው ይተረጉሙታል፡፡

John Mbaku የተባሉ ኢኮኖሚስት ‘Corruption and Rent-seeking’ ባሉት ፅሁፋቸው ገንዘብን መግዛትን ‹‹የመንግስት ፖሊሲዎችን ውጤት ለማስቀየር የሚደረግ እንቅስቃሴ›› ብለው ይተረጉሙታል ፡፡ የገንዘብን መግዣ ድርጊቶች ስንመለከት የተያዩ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

Anne Kruger የተባሉ የሚኒሶታ ዩንቨርስቲ ኢኮኖሚስትThe Political Economy of Rent-Seeking Economy’ ባሉት ፅሁፋቸው ‹‹ገንዘብን ለመግዛት የሚደረገው ውድድር አንዳንዴ ንፁህ እና ህጋዊ በሆነ መልኩ አንዳንዴ ደግሞ እንደ ሙስና፣ ጥቁር ገበያ እና ህገወጥ የዕቃ ማስተላለፍ ያሉትን ህገወጥ መንገዶች በመጠቀም ሊከናወን ይችላል›› ይላሉ፡፡ ይሄም ገንዘብን መግዛት ሁሌም ህገወጥ ተግባር ብቻ አይደለም ወደሚለው መደምደሚያ ያደርሰናል ማለት ነው፡፡

Wednesday, July 4, 2012

አባይን መልሱልኝ!

በሶልያና ሽመልስ

አባይ……. አባይ……..  አባይ…….. አባይ
የአገር አድባር  ያገር ኩራት ……..የአገር  ሲሳይ


ቲቸር ታደሰ ከማልረሳቸው  የአንደኛ ደረጃ መምህራን መካከል አንዱ ናቸው፡፡ ታዲያ የስድስተኛ ክፍልን የህብረተሰብ ትምህርት ለየት የሚያደርገው የቲቸር ታደሰ ከክፍል ሥራ እና ከንባብ በተጨማሪ ይዘዋቸው ይመጡ የነበሩት ከክፍለ ጊዜው ጋር የተገናኙ ጨዋታዎች እና የጠቅላላ እውቀት ጥያቄዎች ነበሩ፡፡ ታሪክ ቀመስ ትረካዎችን ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ሲያነቡልንም አስታውሳለሁ፡፡ (አዲስ ዘመንም የሚነበብ ታሪክ የሚጽፍበት ወቅት ነበረው ማለት ነው?) ታዲያ በአብዛኛዎቹ ክፍለ ጊዜዎች መጨረሻ ላይ ስለቀድሞ የኢትዮጵያ ስልጣኔ ታሪክ እና ስለተያያዥ ጉዳዮች ሲያወሩ የአባይ ጥቅም ላይ አለመዋልን  በቁጭት ማንሳታቸው አይቀርም ነበር፡፡
ከሚሽነሪ ት/ቤቱ ጥብቅ ሃይማኖታዊ ስነ ስርዓት  በመነሳት ምንም አይነት መንፈሳዊ ያልሆነ ሙዚቃ መዝፈን የሚያስቀጣ ቢሆንም ቲቸር ታደሰ ግን በኅብረተሰብ ትምህርት በሬድዮ  ክፍለ ጊዜ ማጠናቀቂያ ላይ በተደጋጋሚ የሚመጣውን፤
አባይ……. አባይ……..  አባይ…….. አባይ
የአገር አድባር ያገር ኩራት ……..የአገር  ሲሳይ

በጋራ እንድንዘምር ይፈቅዱልን ነበር፡፡ የኅብረተሰብ ትምህርት እና ልጅነት ሲነሳ አብሮኝ የሚከሰተው የአባይ ትዝታን የምጋራው እኔ ብቻ ነኝ ብዬ አላስብም፡፡ ዓይነቱ የተለየ ቢሆንም  ሰለአባይ ስንማር  እና ሲነገረን  የኖርናቸውን ነገሮች በማስታወስ የአንደኛ ደረጃ የህብረተሰብ ትምህርቱ  እና የአባይ  ትውስታ የሚቀላቀልበት የኔ ቢጤ ወዳጅ መቼም አላጣም፡፡


የአሁኑ አባይ የማን  ነው?

GTP የት አደረሰን?

በናትናኤል ፈለቀ

የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የሁለተኛው የ5 ዓመት የልማት ስልታዊ እቅድ (Plan for Accelerated Development to End Poverty, PASDEP) ጊዜ ገደብ መገባደዱን ተከትሎ በፈረንጆቹ አቆጣጠር በኖቬንበር ወር 2010 ዓም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን ይሁንታ ካገኘ በኋላ ነበር የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክሪያሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት ሦስተኛ የ5 ዓመት ስልታዊ ዕቅድ ሆኖ መተግበር የጀመረው:: የትግበራው ዋነኛ ግብ የተጀመረው በሁለተኛው የ5 ዓመት የልማት ስልታዊ ዕቅድ አተገባበር ላይ ለተከታታይ ዓመታት ኢኮኖሚው ያስመዘገበውን ፈጣን ባለሁለት አሃዝ እድገት በማስቀጠል የኢንደስትሪው ዘርፍ የኢኮኖሚውን መሪነት ሚና ከግብርና የሚረከብበትን ቅድመ ሁኔታ ማመቻቸት  ነበር::

ይህ ዕቅድ ይፋ ከሆነበት ጊዜ አንስቶ ከየአቅጣጫው የተቃውሞ ትችቶችን ለማስተናገድ ተገዷል:: ዕቅዱ ላይ የሚቀርቡት ትችቶች በዋነኛነት የሚያጠነጥኑት በሁለት አንኳር ጉዳዮች ላይ የነበረ ሲሆን የመጀመሪያው የትችቶች ማጠንጠኛ የመንግስትን ቅጥ ያጣ ጉጉነት የተመለከተ ሲሆን መደገፊያ መከራከሪያውም ዕቅዱ ውስጥ እንደሚተገበሩ የታቀዱትን ተግባራትን ለመከወን የሚያስፈልገውን ያህል ገንዘብ ለማግኘት እንደሚያስቸግርና ዕቅዱ የመንግስትን የመፈፀም አቅም በእጅጉ አጋኖ ያቀረበ ነው የሚል ነበር፡፡ ሁለተኛው ትችት ሆኖ የቀረበው ደግሞ የዕቅዱ አተገባበር ከፍተኛ የሆነ የመንግስት ወጪ ስለሚፈልግ ቀድሞውንም ቢሆን ለቁጥጥር ላስቸገረው ምጥቀ ግዥበት (Hyper Inflation) በዕንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ይሆናል ከሚለው ፍራቻ ነበር፡፡

Sunday, July 1, 2012

ጋዜጣና መጽሔቶቻችን ከሰኞ እስከ ሰኞ - አራት

(ከሰኔ 18፤ 2004 እስከ ሰኔ 24፤ 2004)

‹‹የኢሕአዴግ የስለላና የቁጥጥር መዋቅር ከ1 ለ 5 ወደ 1 ለ 11 አደገ›› የሚል ዜና ይዞ የወጣው ፍኖተ ነፃነት ነው፡፡ በዝርዝሩም ‹‹… ታማኝ ውስጥ አዋቂዎች እንደሚሉት ‹በቅርቡ ፖሊሶች፣ የመንደር ካድሬዎችና ደህንነቶችን የከተማውን ነዋሪ ቅጽ እያስሞሉ ናቸው፡፡ ከዚያም 1 ለ 11 በማደራጀት እያንዳንዱን የከተማ ነዋለሪ ለመቆጣጠር ታቅዷል፡፡›…››

* * *


ዕንቁ መጽሔት በለጠ ደምሴ ከተባለ ከፊል ከተሜ፣ ከፊል ገጠሬ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ስለራሱ እና ስለሚኖርበት ማሕበረሰብ ሥራ የማይሰራቸው በዓላት ሲናገር ‹‹…በ5 አቦን፣ በ7 ሥላሴን፣ በ12 ሚካኤልን፣ በ13 እግዚአብሔርአብን፣ በ16 ኪዳነ ምህረትን፣ በ19 ገብርኤልን፣ በ21 ማርያምን፣ በ23 ጊዮርጊስን፣ በ24 ተክለሃይማኖትን፣ በ27 መድኃኔዓለምን፣ በ29 ባለወልድ፣ በ30 ዮሐንስን አንሠራም፡፡…ቅዳሜ እና እሁድም አሉ፡፡ …›› ብሎ አስገራሚ ቃለ ምልልስ አድርጓል፡፡

* * *


ሪፖርተር ጋዜጣ ‹‹የመንግስት አመራሮች ለውጥን የመምራት ክህሎት አለማዳበራቸው ተገለጸ›› ባለበት የረቡዕ እትሙ